TG Telegram Group Link
Channel: FŰŇ_ŽØÑĘ 😂😱
Back to Bottom
⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷

˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ●•٠·˙
.
ደራሲ ሲራክ
.
⚀ ክፍል አንድ ⚀ 1⃣

➲ .... የሀምሌን ሰማይ እንደ እኔ ከፍቶታል።ቀኑ ገና በንጋቱ ድብስብስ እያለ ነው የነጋው። ሀምሌ 1 ቀን 2010 ዓ.ም እለተ እሮብ ጅማ መድሃኒያለም ሰፈር!
የሰኔ ሰላሳውን ግፊያ ፣ ትዝታ እና ናፍቆቱን አፈር ምሼ የቀበርኩበት እለት ከአስራ አንደኛ ክፍል ወደ አስራ ሁለተኛ ክፍል የመግባቴን ብስራት የሰማውበት ማግስት።
በእለቱ የእለቷ ፀሀይ ገና በሰበካው የተራሮችን ግርዶሽ ቀዳ ብቅ አላለችም።
እኔ አልጋዬ ላይ እንዳለሁ ድብርት ተጫጫነኝ። ከክፍል ጓደኞቼ በመለየቴ ክፍት ፣ ጥብብ ፣ ጭንቅ አለኝ።
ገና በጅማሬው ጠቁሮ እንደ አባቴ ቁጣ የሚያጉረመርመው ሰማይ በላዬ ላይ የወደቀ እስኪመስለኝ ድረስ ድብርት ተጫጫነኝ።
በአስቀያሚ ድብርት ውስጥ እንዳለሁ የክፍሌ በር ሲደበደብ ሰማው፤ እናቴ ናት።
መልሴን ሳትጠብቅ "ግሩም አባትህ ከሰል አምጥቷል ተነስና ከዘበኛው ጋር አስገባልኝ ዛሬ ውሎህን ተጋድመህ መዋልህ እኮ ነው! ግሩም!" አለች
ዝም አልኩኝ
" አንተ ግሩም " አለች ድምጿን ከፍ አድርጋ የበሩን ኳኳታ መጠን እየጨመረች " አቤት " አልኩኝ ድምፄን ከፍቶታል። "ግሩም! ምነው ልጄ አመመህ እንዴ? ድምፅህም ልክ አይደለም " አለች በሩ ላይ ጆሮዋን ልጥፍ አድርጋ።
"ደህና ነኝ" አልኳት በአጭር ቃል።
"ተነስ ቁርስህንም ብላ አባትህም መንገድ ላይ ከሰል አውርዷል እሱንም አስገባልኝ ጎሽ" አለች
"እሺ መጣሁ" አልኩኝ
ከእናቴ አጉል ውትወታ ለመትረፍ ብቻ! እናቴ ብዙም ሳትቆይ እንደሄደች የተረዳውት የኮቴዋ ዳና ከክፍሌ እየራቀ መሆኑን ስረዳ ነው።
አባቴ ልምድ ያለው የNGO ሹፌር ነው። የበርካታ አመታት የአሽከርካሪነት ልምድ አለው። በብዛት የመስክ ስራዎች ላይ ይሳተፋል።
ለመስክ ስራ ወደሌላ አከባቢ ሲሄድ ሲሄድ በርከት ያሉ ከሰሎችን ይዞ ይመጣል።
ዛሬም ለሰባት ቀናት ከቆየበት የመስክ ስራ መመለሱ ነበር። መምጣቱን ሳውቅ እና ወደ አስራ ሁለተኛ ክፍል መግባቴ ትዝ ሲለኝ በዚህ የድብርት ስሜት አባቴን መቀበል አልፈለግኩም።
የታዘዝኩትን ከሰል አስገብቼ ከቤት ወጥቼ ልውል ወስኜ ከአልጋዬ ወረድኩና እንደነገሩ ለባብሼ ከክፍሌ ወጣሁ።......


ክፍል ሁለት ምሽት 2:00 ይቀጥላል........

Any comment @abdsewanted


መልካም አዳር!!

"SHARE" @onlyzeget
ፍሌም🗒🗒📃📃

#YETEMECHEW
⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷

˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ●•٠·˙
.
ደራሲ ሲራክ
.
⚀ ክፍል ሁለት ⚀ 2⃣



.....የታዘዝኩትን ከሰል አስገብቼ ከቤት ወጥቼ ልውል ወስኜ ከአልጋዬ ወረድኩና እንደነገሩ ለባብሼ ከክፍሌ ወጣሁ። በጣም እንደነጋ ያወቅኩት በሳሎኑ በኩል ወደ ውጪ እየወጣሁ የግድግዳ ሰዓታችንን ተመልክቼው ነበር። ቀኑ ድፍንፍን ያለ ነው። ማታ ዘንቦ ማደሩን የመሬቱ እርጥበት ያሳብቃል። የግቢውን በር ከፍቼ ስወጣ ጭራሽ ሰፈሩ በጉም ተከቧል።መጣ የተባለውን ከሰል ከዘበኛው ጋር አስገብተን ስንጨርስ የከሰሉን ማዳበሪያ የሸፈኑትን ቅጠሎች ከግቢ ውጪ ለመጣል ወጥቼ ጥዬ ወደ ቤት እየገባው የግቢያችን በር ላይ ስደርስ "ወንድም!" የሚል የሴት ድምፅ ሰማው።
ዞር ስል የሙስሊሞችን ሂጃብ የጠመጠመች ቀይ ባለሰልካካ አፍንጫ ፤ ውብ ፀዓዳ መሳይ አይኖችን የታደለች ፤ ቀይ ባለ ትንሽ ክብ ፊት ፤ ባለ ድንቡሽቡሽ ጉንጭ ሴት ቆማለች።
ድንግጥ አልኩኝ! ልቤ ትርክክ ፣ ስንጥቅ አለ። ድንገተኛ መባርቅ የመታኝ ያህል ክው አልኩኝ።
የማሪያምን ምስል የመሰለች ፤ የመላዕክታንን ውበት የታደለች ቆንጆ ልጅ ናት።
ልቤ የደም ዝውውሯን አፈጠነችው ትርታዬ ትር ትር ትል ጀመር።ቃል ሳላወጣ በድንጋጤ ውስጥ ሆኜ አየዋት። እሷም ፍዝዝ ብላ ታየኝ ጀመር። ደፍሮ ቃል የሚያወጣ ጠፋ።
"ይቅርታ ሱቅ ተልኬ ጭቃ ነካኝ ውኃ..." አለች
እጇ በጭቃ ተበላሽቷል።ዝቅ ስል የለበሰችው ቢጃማም በጭቃ ደክርቷል። ለማየት የሚያሳሱ ውብ የአድማስ ዋልታ፣ የከዋክብት ፍንጣቂ የመሳሰሉ አይኖቿን አንከራተተችብኝ።
ውኃ ላመጣላት ተጣድፌ ወደ ቤት እየገባው ተገረምኩኝ 'ምን አይነት መሬት ቢሆን ነው እቺን ልዕልት የመሰለች ልጅ የጣላት? አይ የምድር ክፋት!' አልኩኝ በልቤ። ውኃውን በጆግ ቀድቼ ስመለስ ልጅቷ ግቢ ገብታ ነበር።
ውኃውን እያፈሰስኩላት እጇን እየታጠበች ልክ እጇ ጥርት ማለት ሲጀምር የቀኝ እጇ መሀከለኛው መዳፍ ላይ ትኩስ ትኩስ ቁስል አየሁኝ።
"እንዴ በእግዚአብሔር እየደማ እኮ ነው!" ብዬ ጆጉን ጣልኩና እጇን ለቀም አድርጌ ያዝኩት እጇን ስይዘው መላው ሰውነቴ በኤሌክትሪክ ሞገድ የተቀጣጠለ ይመስል አንዳች ሀይል መላው ሰውነቴን ነዘረኝ። እሷም ድንግጥ አለች!
ከአይኔ እየሸሸች "አ..ይ ....ትንሽ ነው ማለቴ..እእእ ዝም ብሎ ነው....ማለቴ አለ አይደል .. እእ" አለችና ቀና ብላ ውብ አይኗን አንከራተተችብኝ።
የሲኦል ፍም የመሰለው ፀዓዳ ከንፈሯ ይንቀጠቀጣል። ከገነት ቅርንጫፎች የተመዘዙ ጭራሮ የመሳሰሉት የውብ አይኗ ሽፋሎች በፍጥነት ይርገበገባሉ።በዚህ ሁነት ውስጥ እንዳለን "ግሩሜ"የሚል ድምፅ ሰምቼ ዞር ስል እናቴ ናት። "እንዴ ምን እየሰራህ ነው ልጄ!? ደግሞ እሷ ማናት?" አለችኝ ፊቷን ኮስተር ቅጭም አድርጋ የታዛውን ደረጃ ወርዳ ወደ እኛ እየተጠጋች።.........




ደራሲ C-ራክ
comment ፦ @abdsewanted

ገና ማረፌ ነው ሥላረፈድኩኝ ይቅርታ ይደረግልኝ 🙏

"SHARE" @Onlyzeget
⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷

˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ●•٠·˙
.
ደራሲ ሲራክ
.
⚀ ክፍል ሶስት ⚀ 3⃣




....."እንዴ ምን እየሰራህ ነው ልጄ!? ደግሞ እሷ ማናት?"አለችኝ ፊቷን ቅጭም አድርጋ የታዛውን ደረጃ ወርዳ ወደ እኛ እየተጠጋች።
እናቴ ደርብ ያለች የሴት ወይዘሮ ነች። እድሜዋ ወደ ሀምሳዎቹ እየሮጠ ነው።አባቴ ሲያገኛት ጠየም ያለች ወይዘሪት ስለነበረች አባቴ"ከአሳ የተቀዳ ውበት እያለ እንደሚያሞካሻት ሁሌም ይነግረን ነበር።
ግን አባቴ ይበልጥ ቀልቡን የሚስበው የጉንጮቿ ስርጉድ(ዲምፕሏ ) እና የጥርሷ ጉራማይሌ ነበር።
"እእ..ማ..ለት ውኃ .." ተንተባተብኩኝ እናቴ ልጅቷን ማናት ላለቻት ጥያቄ!
"ፍሌም እባላለሁ ሱቅ ተልኬ ጫማዬ አንሸራቶኝ ወድቄ ውኃ ስጠኝ ብዬው ነው ይቅርታ" አለች ልጅቷ ቅልጥፍናን በተላበሰ ትሁት አንደበት!!
ቅልጥፍናዋን እና ድፍረቷን ወደድኩት አንዳች ነገር እንደተናገረች ገምቻለሁ! ማለት ምንም የሰማው አልመሰለኝም። ፍሌም እባላለሁ ያለችውን ብቻ ነው በጥራት የሰማውት። ስሟ ውስጤ ቀረ እንደ ገደል ማሚቶ በጭንቅላቴ ውስጥ አስተጋባ! እናቴ ስትመጣ ደንግጬ እጇን ከለቀቅኩኝ ወዲህ ሙቀቷ ዘላለማዊ ይሆነኝ ዘንድ በእጄ ውስጥ የማሰርፀው ይመስል እጄን በእጄ አፋትጋለሁ።
....ዛሬ ግን ምን ነካኝ??
ለዚህች ልጅ ይህን ያህል መሆን ምን አስፈለገ ?
በዛ ላይ በዛሬ ያውም አሁን በአሁን!
ሆሆሆሆሆ ወይ ነዶ!
"ቲዲያ ምን ችግር አለው የኔ ልጅ ! የማነሽ ቆንጆ ደግሞ ነይ ሳሚኝ እስኪ " ብላ እናቴ ተጠጋቻት። ፍሌም ወደ ኃላ ሸሸት እያለች "ልብሴ ጭቃ ብቻ ነው እንዳላበላሽዎት "አለች። እናቴ ተጠግታት ግንባሯን ሳመቻት እና ወደ እኔ ዘወር ብላ"ግሩሜ እስኪ ከሚሚዬ ክፍል የሚሚዬን ቢጃማ አምጣላት! "አለችኝ እሩጬ ትርሃስ ክፍል ስገባ ከኮመዲኖ ላይ ተጣጥፎ የተቀመጠ ቢጃማ አግኝቼ ተመለስኩ።
እናቴ እና ፍሌም ቆመው ያወጋሉ። እናቴ እኔን ስታየኝ
" ጎሽ ግሩሜ ሻወር ቤቱን አሳያትና ሻወር ትውሰድ!"አለች
"አይ እንዲሁ እቤት ብሄድ ይሻላል ለሀገሩም አዲስ ስለሆንኩ አጎቴ ይሰጋል"አለች ፍሌም አንደበቷ ይጣፍጣል።የድምጿ ቅላፄ እንደ ወፍ ዜማ ለጆሮ ይስማማል!!
ከእናቴ ጋር አውግተው ሌላ ጊዜ መጥታ እንደምትጫወት ተነጋግረው ሸኛት ተብዬ ይዣት ከግቢው ወጣሁ።
የጅማ መድሃኒያለም ሰፈር በነጭ ጋቢ ተደርቶ የሚቆዝም ሽማግሌ ይመስል የጉም ጢስ ተከናንቦ ፀሀይ መውጣት፤ወገግ ማለትን ዳባ ልበስ ያለ ይመስላል።......


ክፍል አራት ይቀጥላል........


comment ፦ @ABDSEWANTED


"SHARE" @ @Onlyzeget
ወንድ ልጅ ግን አይገርማችሁም? የእናቱን ጡት እየጠባ ያድጋል የሚስቱን ጡት እየጠባ ይኖራል😜😂
⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷

˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ●•٠·˙

ደራሲ ሲራክ
.
⚀ ክፍል አራት ⚀ 4⃣



🤚 የጅማ መድሃኒያለም ሰፈር በነጭ ጋቢ ተደርቶ የሚቆዝም ሽማግሌ ይመስል የጉም ጢስ ተከናንቦ ፀሀይ መውጣት፤ወገግ ማለትን ዳባ ልበስ ያለ ይመስላል።
ከፍሌም ጋር ምንም ሳናወራ ረጅም መንገድ ተጓዝን በጅማ መድሃኒያያለም የመቃብር ስፍራ በኩል ባለው ወደ ዲፖ ቀበሌ ሶስት መታጠፊያ ቅያስ ጋር ስንደርስ ፍሌም ቆም አለች "በዚህ ነኝ "አለችኝ መታጠፊያውን በግራ እጇ እየጠቆመችኝ በገሚሱ መሬቱን በገሚሱ እኔን ገርመም አድርጋ እያየችኝ።
"እሺ ቻዎ " አልኳት እና ወደ ኃላ ተመልሼ ጥቂት እርምጃዎችን እንደተራመድኩ "ግሩም" አለችኝ
ዞር ስል ድብስብስ ባለ ጎህ በሚመስል የንጋት ወሰን ላይ የፈነጠቀች ፈዘዝ ያለች የፀሀይ ብርሃን የፈካባት ትንሽዬ ከተማ የመሰለች ደስታን በክብ ፊቷ ላይ አስተዋልኩ ፤ ለዘብ ባለ ድምፀት "ወዬ "አልኳት
"አመሰግናለሁ " ብላኝ ይበልጥ ፈገግ ብላ፤ በአጭሩ ፈገግታዋን መግባኝ ምላሼን ሳትጠብቅ ፍሌም ነጎደች ....ሄደች .......ራቀች.....ታጠፈች.....ጠፋች።
ቀኑ መሽቶ ነጋ አባቴ ባመጣሁት ውጤት ደስ ብሎት አደረ። ቤታችን ውስጥ ያለነው ሶስት ልጆች ነን።
ትንሹ ወንድሜ ቅዱስ፣ታናሽ እህቴ ትርሃስ እና እኔ ነን።የቤቱ ታላቅ እኔ መሆኔ ነው። አባቴ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ለሽልማት ላውቶፕ ኮምፒውተር እንደሚሸልመኝ ቃል ገባልኝ።ደስም አለኝ!!
ጠዋት ላይ ፍሌም መጥታ ከእኛ ጋር ስትጫወት ዋለች።ፍሌምን እኔ በአንድ አመት በትምህርት እበልጣታለሁ። የምትኖረው ድሬዳዋ ነበር።ያውም ከዚራ ውስጥ እዚህ ጂማ መድሃኒያለም ሰፈር አጎት አላት። የህንፃ ተቋራጭ ሀላፊ ነው።
እኔ ከምምጣቷ ይልቅ ስትሄድ መሸኘቱ ነው የልቤን የሚያደርሰው። ልክ አመሻሽ ላይ ልሸኛት ተዘጋጅቼ እየጠበቅኳት እያለሁ ትርሃስ "ፍሌሜ ነይ እንሂድ በዛውም ካርድ ገዝቼ ልመለስ!" አለቻት። ይሄኔ ትርሃስን ማነቅ ዳዳኝ፣ ተቃጠልኩኝ። ተሰናብቻት ክፍሌ ገብቼ የአልጋው ጫፍ ላይ ተቀምጬ በሃሳብ እብከነከን ገባሁ። በዚህ ፍጥነት ለዚህች ልጅ ያለኝ ምልከታ ግራ አጋባኝ።
አይኗን፣ ከንፈሯን ይበልጥ ደግሞ ዲምፕሏን እያሰብኩ እንቅልፍ ይዞኝ ጭልጥ አለ። ይሄ ከሆነ ከሁለት ሳምንት በኃላ የሆነ ቀን አመሻሽ ላይ ሀሳብ ጭንቅንቅ ሲያደርገኝ አየር ለመቀበል ብዬ ኮት ደርቤ ኤርፎኔን ከስልኬ ጋር ይዤ ወጣሁኝ። በመድሃኒአለም ቤተክርስቲያኑ አድርጌ ሽቅብ ወደ መንደራ ትምህርት ቤት አቅጣጫ አቀናሁ።
በስልኬ በሻሸመኔ እና በሀዋሳ ከተማ መካከል ጥቁር ውኃ ተብላ በምትጠራበት ቦታ የበቀለውን ተወዳጁን የሙዚቃ ንጉስ የድምፃዊ ታምራት ደስታን ውብ ትዝታ እየሰማሁ ወደ መናፈሻው ተቃረብኩ።.....


ክፍል አምስት ነገ ምሽት ይቀጥላል........


comment ፦ @ ABDSEWANTED


"SHARE" @Onlyzeget
⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷

˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ●•٠·˙

ደራሲ ሲራክ
.
⚀ ክፍል አምስት ⚀ 5⃣



......➲ በስልኬ በሻሸመኔ እና በሀዋሳ ከተማ መካከል ጥቁር ውኃ ተብላ በምትጠራበት ቦታ የበቀለውን ተወዳጁን የሙዚቃ ንጉስ የድምፃዊ ታምራት ደስታን ውብ ትዝታ እየሰማሁ ወደ መናፈሻው ተቃረብኩ።
የሙዚቃው ስሜት በለሆሳስ በውስጤ እየተርመሰመሰ ከንፋሱ ጋር በትዝታ ሰረገላ ላይ በደመና ክምር ውስጥ ይዞኝ እየነጎደ ነው።
ድምፁ በልጅነታችን በተረት የምናውቃትን የተረት ከተማ ኩልል አድርጎ ያስቃኛል። የግጥም እና የዜማው ቁርኝት የልቤን በር ከፍቶ አንድን ሰው እንዳስብ እያደረገኝ ነው።በሌላ በኩል ክረምቱንም በግጥሙ ከትቦታል።
.......🎶 የደጃፌን መዝጊያ ክፍት አድርጌው ነበር
ዛሬም አልተዘጋም ሳትመለስ ስትቀር
አይኔ በእምባ ጭጋግ እንደተጋረደ
ስንት ሰኔ ጠብቶ ስንት ክረምት ሄደ
🎶
እየቆረቆረኝ እያሰረኝ ከእግር እስከ ራሴ
አጎዛው ሊጥለኝ ሲታገለኝ ተረበሸች ነፍሴ..🎶
🎶
እያለ ይቀኛል።ግጥም እና ዜማው እንደ ድር እና ማግ ከድምፁ ጋር ተሰፍቷል ማለት ይቻላል። ሙዚቃውን እናጣጣምኩኝ መናፈሻው ጋ ደረስኩኝ። ሁሌም መናፈሻው ጋር ስደርስ ማዘውተሪያው ፊት ለፊት የድንች ጥብስ ከሚሸጡት ሰዎች ድንች ገዝቶ እየበሉ መሄድ ወደቤት መመለስ ልምዴ ነው። ሙዚቃው ከስሜቴ ጋር ዘለአለማዊ ህያው ምጥቀትን ያላበሰኝ ያህል ከደም ዝውውሬ ጋር የተዋሃደ መሰለኝ።
...🎶 አንቺው ጋር ይቀመጥ እባክሺ የፍቅሬ ትዝታ
የማትመጪ እንደሆን ምን አጥቼ እኔ ልንገላታ 🎶
🎶
ማዘውተሪያውን ተሻግሬ የጅማ ሙዚየሙ በር አከባቢ ስደርስ ከፊት ለፊቴ ያየውትን ማመን አቃተኝ። ልቤ በደስታ ይሁን በድንጋጤ ቶሎ ቶሎ ትመታ ጀመር። ጭንቀት የመከነበት ፤ ደስታ የተንጠፈጠፈበት ፊት አስተዋልኩ። ስታየኝ ፈገግ አለች። እኔም ፈገግኩ። ፍሌም ናት።
በዚህ የመልዓከ ሞት ፈረስ መጋለቢያ ሜዳ በመሰለው ጭጋጋም ምሽት እሷን ማግኘት መታደል ነው ስል አሰብኩኝ።
አንዳች ደስታ ውርር ሲያደርገኝ ይሰማኛል።
የፍሌም ፀዓዳ መሳይ ቀይ ፊቷ እና የሲኦል የፍም ገላ የመሰለው ከንፈሯ ሸሽቶ ጥርስዋ ብቅ ሲል ጉራማይሌዋ በምሽቱ ጭላንጭል ብርሃን ሲታየኝ አለማንም ከልካይ ተንደርድሬ ሄጄ አቀፍኳት። ምንም አላለችም ይልቁንም አፀፋዋን በማቀፍ መለሰች።
"ግሩሜ እንዴት ነህ?" አለችኝ ፈገግታዋ ከፊቷ ሳይረጋ ከለበሰችው ኮት ጋር ትልቅ ሰው መስላለች።..............


ክፍል ስድስት ነገ ምሽት በዚህ ሰዓት ጠብቁን........

ደራሲ C-ራክ
comment ፦ @ABDSEWANTED


"SHARE" @ONLYZEGET
⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷

˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ●•٠·˙

ደራሲ ሲራክ
.
⚀ ክፍል ስድስት ⚀ 6⃣


"ግሩሜ እንዴት ነህ?" አለችኝ ፈገግታዋ ከፊቷ ሳይረጋ ከለበሰችው ኮት ጋር ትልቅ ሰው መስላለች።
"ደህና ነኝ ከየት ነው በዚህ ሰዓት?"አልኳት
"ባሌ ሰለቸሽኝ ሲለኝ ለአንዷ ሰጥቼው መመለሴ ነው አልገርምም?" አለችኝ ይበልጥ ፈገግ እያለች፤ ፈገግታዋ ልብ ያሞቃል በዚህ ብርዳም ምሽት እሷን በማግኘቴ ተደሰትኩ።
"ይገርምሻል እኔም ሚስቴ የሆነ ሰውዬ ጋ አየናት ያውም የሆነች ቆንጅዬ ሴት ናት አሉ 'ባሌን ውሰጂው ብላ የሰጠችው' ብለውኝ እኮ ጉድ ብዬ ስልኬን ስዘጋ ተገናኘን ወይ መገጣጠም!" አልኳት።
ከት ብላ ስቃ ስታበቃ "አቦ በአላህ ደስ ትላለህ አሳከኝ!" አለች በልስልስ ጥዑም አንደበቷ።
"ይልቅ ከየት ነሽ?" አልኳት ውብ አይኗ ላይ አይኔን ተክዬ
"አጎቴ ከጉዋደኞቹ ጋር አስተዋውቆኝ እቆያለሁ አንቺ ብሎኝ መመለሴ ነው። አንተስ ግሩሜ?" አለች።
አይ እኔማ ወክ እያደረኩ ነበር ካልቸኮልሽ ለምን ተቀምጠን አናወራም ?" አልኳት የመናፈሻውን ግቢ በአይኔ እየጠቆምኳት።
ጭንቅላቷን በመነቅነቅ እሺታዋን ገለፀችልኝና ገብተን የመናፈሻው ወንበር ላይ ተቀምጠን ስለብዙ ነገር አወራን። ወሬያችን ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ፍሌም በሳቅ ትንከተከት እንደነበር አስታውሳለሁ!።
ጥቂት የማይባል ጊዜ እንዳወራን የሰዓቱን መንጎድ ተመልክታ እንድንሄድ ጠየቀችኝ። ተያይዘን ከመናፈሻው ቅፅር ግቢ ስንወጣ ሰዓቱ ሁለት ሰዓት ከሰላሳን አጋምሶ ለሶስት ሰዓት ግስገሳውን አፍጥኖታል።
ታክሲም ሆነ ባጃጅ ጥድፊያ ነው። በእግራችን አዘገምን በጉዞአችን በበረደኝ ሰበብ ከፍሌሜ ጋር እየተጠጋጋን እየተጠጋጋን በስተመጨረሻ ተቃቅፈን ጉዞአችንን ባጀነው።
የእሷ መታጠፊያ ጋ ስንደርስ ይበልጥ ተቃቅፈን ትንሽ ከቆየን በኃላ "ደህና እደር ግሩሜ " አለችኝ "ደህና እደሪልኝ" ብዬ አፀፋውን መልሼ ወደ ቤት አዘገምኩ።
አልጋዬ ላይ በጀርባዬ ተንጋልዬ ያፈራነውን እያመሰኳሁ እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ።

🔅🔅🔆🔆🔆🔅🔅🔅🔆🔆🔆🔆🔆

ከዛች ምሽት ወዲህ ከፍሌም ጋር በሰፊው መገናኘት መቀራረብ ቻልን። ፍሌም ከድሬ በበለጠ እዚህ ከመጣች ወዲህ ደስታዋ እንደጨመረ ዘውትር ታወሳኛለች። አጎቷ ለፊልድ ወጣ ካለ መናፈሻው አይቀረን ሲኒማው አይቀረን የወንዝ ዳር ደፎች አይቀሩን ፣ በየመንገዱ ላይ ስንፈስ ነው የምንውል የምናመሸው!?።
እንዲህ እንዲህ እያልን ክረምቱን ለመባጀት ተቃረብን ሀምሌን ሸኝተን ነሀሴን አጋምሰነዋል። ይሄኔ እኔ ክፉኛ ጨነቀኝ ፍሌሜን ማጣት አልፈለኩም እሷን ማጣት ሞትን የመቀበል ያህል ከበደኝ። ስቀርባት እንደምትርቀኝ አልታወቀኝም ነበር መሰል።
ያን ሰሞን ቁዘማ ስራዬ ሆነ። ቤት ውስጥ ንጭንጭ አበዛለው ብቻዬን መዋል ማደርን አዘወትራለው። ፍሌም ስታስጠራኝም የለም አስብል ጀምሬያለሁ።

​​

ክፍል ሰባት ነገ ምሽት ይቀጥላል........

ደራሲ Cራክ
comment ፦ @ABDSEWANTED

"SHARE" @ONLYZEGET
⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷

˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ●•٠·˙
.
ደራሲ ሲራክ
.
⚀ ክፍል ሰባት ⚀ 7⃣



ያን ሰሞን ቁዘማ ስራዬ ሆነ። ቤት ውስጥ ንጭንጭ አበዛለው ብቻዬን መዋል ማደርን አዘወትራለው። ፍሌም ስታስጠራኝም የለም አስብል ጀምሬያለሁ።
ስትሄድ ደግሞ ይከፋኛል። ውስጤ ፍሌሜን ይራባል።ትኩስ እምባዬ እንደሳማ ጉንጬን እየለበለበኝ ይወርዳል። ምን መወሰን እንዳለብኝ ግራ ገባኝ የማዋየው ጓደኛም ሆነ ወዳጅ የለኝም። የነበሩትንም ክረምቱ ወስዷቸዋል።
ከፍሌም አንደበት 'እዬዳለሁ አልሄድም 'የሚሉትን አቁሳይ ፈዋሽ ቃላቶችን ከአንደበቷ ሳልሰማ ልቤ፤ ልቤ ከራሱ ጋር ግብግብ ገጥሞ ሰርክ ያስጨንቀኝ ጀምሯል።
ማንን የውስጤን አዋይቼው ከልቤ ሀገር ዘልቆ ባማለደኝ እላለሁ። ግን ማለት ብቻ ነው። ወኔ እንደ ኳስ ተጫዋች ቁምጣ ካጠረኝ ሰነባብቷል።
ቤት ውስጥ ጠዋቱን ቁርስ ሳልበላ ስቆዝም እውላለሁ። በእናቴ ልመና እና ግዝት ትንሽ ነገር ቀማምሼ ፍሌሜን ብዙ ነገር ወዳዋየሁባት የጋራ ቦታችን እሄዳለሁ።
ጅማ ፉርስታሌ ሰፈር አዌቱ ወንዝ ዳር ዋርካው ስር ተቀምጬ በመሬቱ ላይ እየተጥመለመለ ሲሄድ በልዩ ፍቅር የማየውን የአዌቱን ወንዝ እየተመለከትኩ ፍሌሜን በጥልቅ ተመስጦ እና ጥልቀት የሀሳብ ባህር ውስጥ ሆኜ አሰላስላታለሁ።
በማሰላሰሌ ውስጥ አንድ ሃሳብ ከተፍ አለልኝና የቁዘማዬን ልጓም ከአዌቱ ዳር ካለው ዋርካ ሸብ አድርጌ በትዝታ ሰረገላ ተሳፍሬ አድማሱን እየቀደድኩ ነጎድኩኝ።

ቀኑ አንድ እሁድ ከሰዓት ነው።
የአዌቱ ወንዝ ዳር እና ከባቢው ጭር ብሏል። ውሃው እና ድንጋዮቹ ተጋጭተው ከሚፈጥሩት ድምፅ በቀር ምንም የሚሰማ ነገር የለም።
እኔ ግዙፉን የአዌቱን ዳር ዋርካ ተደግፌ የሆነ ወቅት ከፍሌም ጋር ሲኒማ አይተን ስላየነው ሲኒማ የተጠያየቅነው ነገር ትዝ አለኝ።
........ ቀኑ ደመናማ ነበር። ማንም በቤት ውስጥ የለም አልነበረም። እናቴ ሰርግ ብላ ጠዋት እንደወጣች አልተመለሰችም። ቅዱስ መንደር ሊጫወት ሄዷል። ትርሃስ ክፍሏ ተኝታለች። ፍሌም ቤቷ ደብሯት እኛ ጋ ልትጫወት መጣች። እኔ ትርሃስ የተከለቻቸውን አበባዎች እየነቀልኩላት ነበር። የቤታችን ድባብ ጭር እንዳለ ነው። ፍሌሜ ሰላም ብላኝ ደረጃዎቹ ላይ ተቀመጠች። ከቧንቧው ላይ በቱቦ ውሃው ቀድቼ እያጠጣሁኝ ተንኮል አስቤ ፍሌሜን ጠራዋት መጣች። በቱቦ ውስጥ እየተንፎለፎለ የሚመጣውን ውሃ ወደ እሷ መልሼ ዝም አልኩ። ውሃው ሲነካት ፍሌም ጮኸች።
ልታስቆመኝ ታገለች። ውሃው ሁለታችንም ላይ ወረደ ተረጫጨን ሁለታችንም በሰበስን ኃላ ላይ ፍሌሜን ሳያት ደስ ብሏታል። ጥቁሩ ዞማ ፀጉሯ በፊቷ ላይ ተበታትኗል።
ፈገግ አለች። ጎትቼ እቅፌ ውስጥ ወሸቅኳት። እንደተራራ የተገተሩ አጎጠጎጤ ጡቶችዋ ደረቴን እንደ አድዋ ጦር ወግተው በሰራ አካላቴ ላይ ሙቀት ለቀቁብኝ።........



ክፍል ስምንት ነገ ምሽት ይቀጥላል........

ደራሲ C-ራክ
comment ፦ @ABDSEWANTED

"SHARE" @ONLYZEGET

አንብባችሁ ለወዳጆ ሼር ያድርጉት!
ፍሌም🗒🗒📃📃

#YETEMECHEW
⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷
.
ደራሲ ሲራክ
.
˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ●•٠·˙

⚀ ክፍል ዘጠኝ ⚀ 9⃣


ፍሌሜ ሁለቱ እጇቿን በአንገቴ ላይ አቆላልፋየጎመራ ፖም በሚመስለው ስስ ከንፈሯ ትመጠምጠኝ ገብታለች።
ሁለታችንም ራሳችንን ውጠን ለሌላ አለም ለመውለድ የምናምጥ ተስፈኞች ነን ስል አሰብኩ።
እጆቿ አንገቴን ለቀው በፀጉሬ ዘለላዎች ውስጥ ይርመሰመሱ ጀመር። ጦርነቱ መጀመሩ ነው።
እኔም እጄ ስራ አላስፈታሁትም። እንደ እንቁሉል በስስት ይዣት እንደ ጣፋጭ ማንጎ ከናፍሯን መጠጥኩት። አየር ለመሳብ ብለን እረፍት አደረግን ትንፋሻችን እንደ ሲኦል ወላፈን ይጋረፋል።አንገቷ ስር ገብቼ እየሳምኳት በጆሮዋ ውስጥ አንሾካሾኩ።
እሷም ከጥልቁ ስሜት አፋፍ ላይ ሆና አንሾካሾከች።
ጊዜ ሳላጠፋ ወደ ከንፈሯ ተመልሼ እያካለብኩ ወደ አልጋው ላይ ጣልኳት። አብሬያትም ወደቅኩ።
እጆቼን በመላው አካላቷ ላይ አርመሰመስኩት እንደ ተራራ ተቀስሮ ሲወጋኝ የነበረው ጡቷን አለከልካይ እንደፈትል ፈተልኩት።
የትንፋሿን ሙቀት አልቻልኩም። ተነስቼ በሩን ቆልፌ ወደቅኩባት።ከዛ እንጃ ዙሩ ከረረ።
የሆነ ሰመመን ውርር አደረገኝ።ፍሌም ስታቃስት በጆሮዬ ስታንሾካሹክ ይታወቀኝ ነበር።
የሆነ ብቅ ጥልቅ የሚል ባህር ላይ ተጥለን የምንዋኝ አላዋቂ ዋናተኞች እንደሆንም ይሰማኝ ነበር።
......ደስስስ የሚል የስቃይ አለም....
በመሰንበት እና በመንቃት ወሰን የታጠረ ሽቦ።
የፍሌም ማቃሰት እየበዛ እየበረታ ሄዶ ብቅ ጥልቅ የሚለው ባህር ማዕበሉን አናውፆ ፀጥ አለ።ረጭ።
እየተንቀለቀለች የነበረች መከረኛ ነፍሴ ሰከነች።
ፍሌሜም እርግት አለች።አለምን በግዛቴ ስር ያኖርኳት ያህል እርካታ ተሰማኝ።አለሜን ሸመትኳት ፤ ህይወትን ከረጋ ምንጯ ተጎነጨዋት።
የባህሩ ተናውጦ እኛ ዋናተኞቹን ወደ ዳር ሲያወጣን ጨፍኜ እርካታዬን እያጣጣምኩ ነበር። አይኔን ገለጥኩኝ ፍሌሜ ክንዴን ተንተርሳ በጎን ደረቴ ላይ ተንታለች።
ስስ አልጋ ልብስ ለብሰናል። ፍሌምም ሆንን ባዶ ራቁታችን ነን። እቅፍ አድርጌ ሳምኳት። አጥብቃ አቀፈችኝ።
በዚህ ሰዓት በሩ በሀይል ተንኳኳ በድንጋጤ የምገባበት ጠፋ ፍሌም አይኗ ፈጠጠ።
"ማነው?" አልኩኝ ድንጋጤ በሸበበው ድምፀት።
"ግሩሜ ማነው ያስቀመጥኩትን ልብስ የወሰደው? ቆይ በእግዚአብሔር እዚህ ቤት የሚረዳኝ የለም ማለት ነው?"አለች ትርሃስ ንጭንጯን ጀመራት አልኩኝ በልቤ።
"የምን ልብስ ነው ማለቴ ምን የሚደረግ?" አልኳት ድንጋጤው አለቀቀኝም።......


ክፍል አስር ይቀጥላል........

ደራሲ C-ራክ
comment ፦ @ABDSEWANTED

"SHARE" @ONLYZEGET
⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷

˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ●•٠·˙
.
ደራሲ ሲራክ
.
⚀ ክፍል ስምንት ⚀ 8⃣


ጥቁሩ ዞማ ፀጉሯ በፊቷ ላይ ተበታትኗል።
ፈገግ አለች። ጎትቼ እቅፌ ውስጥ ወሸቅኳት። እንደተራራ የተገተሩ አጎጠጎጤ ጡቶችዋ ደረቴን እንደ አድዋ ጦር ወግተው በሰራ አካላቴ ላይ ሙቀት ለቀቁብኝ።
በጥፍሯ ተንጠራርታ ግምባሬን ሳመችኝ።አፀፋውን ለመመለስ ጉንጭ እና ጉንጯን አጥብቄ ይዤ ከንፈሯን ጎረስኩት። ቀና ብላ አይታኝ አይኗን በሀፍረት ሰበር አድርጋ በፊቷ ላይ ላይ የወደቁትን የፀጉሯን ዘለላዎች እየሰበሰበች ወደቤት ገባች።ተከተልኳት። ክፍሌ እንድትገባ ፈልጌያለሁ። ተንኮል ፈለግኩ። ሳሎኑን አልፋ በኮሪደሩ ወደ ቀኝ ታጥፋ ወደ ትርሃስ ክፍል ስትገሰግስ እጇን ያዝ አድርጌ " ትርሃሴን ዛሬ አሟት ተኝታለች" አልኳት በለሆሳስ።
"ልብሴን ልለውጥ ነው አልረብሻትም" አለች አይኗን በአይኔ ላይ ተክላ።
"ግድ የለሽም እኔ ክፍል ግቢ እኔ ይዤልሽ ልምጣ " አልኳት ዞማ ፀኑሯን እየሰበሰብኩኝ።
"የኔ ቆንጆ የትርሃሴን ነገር ታውቂው የለ ከተነሳች ንጭንጯን አልችለውም!" አልኳት ደግሜ በልመና አኳኋን።አይኗን በአይኔ ላይ እያንከራተተች በእሺታ አንገቷን ነቅንቃ ወደ ክፍሌ ገባች።
ትርሃስ ክፍል ስገባ አጣጥፋ ያስቀመጠቻቸውን ምርጥ ምረጥ ልብሶቿን ትራስጌዋ ላይ አገኘውት።
ፀጉሯን በትና ግራና ቀኝ እጆቿን ወዲያና ወዲህ ወርውራ ተኝታለች። አስተኛኘቷ አስቀናኝ በጥልቅ ስሜት ውጥ ተዘፍቃ እንቅልፏን ትለጥጠዋለች።
በመስኮት በኩል የከሰዓቱ የደመና ግርዶሽ እየተቀደደ ፀሀይ እየወጣች ስለመሆኑ ጮራው በመስኮቷ በኩል አልፎ ኮመዲኖዋ ላይ አርፏል።
የሲሳይ ንጉሱ ሰመመ ፣ የአቤ ጉበኛ አልወለድም ፣ የይስማዕከ ወርቁ ተከርቸም መፅሀፍቶች አንዱ በአንዱ ላይ ተደራርቦ ተቀምጧል።
የከሰዓቱ ድባብ ቤቱን ወርፎታል።
ከትርሃስ ክፍል ወጥቼ ወደ ክፍሌ አቀናው ፍሌም ከክፍሌ ደቡባዊ ጫፍ ላይ ቆማለች። አይኔን ከአይኗ ላይ ሳልነቅል ያመጣሁላትን ልብስ አልጋው ላይ ወርውሬ ተጠጋዋት።
እጄን ትከሻዋ ላይ አድርጌ ጎትቼ ከንፈሬን ከከንፈሯ ጋር አዋሃድኩት።
ትንፋሽ እና ትንፋሻችን ጠፋ። ህይወት ዳናዋን አጥፍታ በህቡዕ መሰስ እያለች የምትበረው ይህን ጊዜ መሰለኝ።
ሰመመን በመሰለ የህይወት ጉዞ አለከልካይ በጥልቅ ተመስጥኦ ከደፉ ወረደን ወደ ጥልቁ ህይወት ዘለቅን።
በዚህ ጥልቅ ረቂቅ አለም ተስፋ እንጂ ውድቀት ፤ ገነት እንጂ ገሀነም አይታይም። ፍሌሜ ሁለቱ እጇቿን በአንገቴ ላይ አቆላልፋየጎመራ ፖም በሚመስለው ስስ ከንፈሯ ትመጠምጠኝ ገብታለች።
ሁለታችንም ራሳችንን ውጠን ለሌላ አለም ለመውለድ የምናምጥ ተስፈኞች ነን ስል አሰብኩ።.......


ክፍል ዘጠኝ ይቀጥላል........

ደራሲ C-ራክ
comment ፦ @ABDSEWANTED

"SHARE" @ONLYZEGET
#FlAME
👍YKETEL 👎AYKTEL
⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷
.
ደራሲ ሲራክ
.
˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ●•٠·˙

⚀ ክፍል ዘጠኝ ⚀ 9⃣


ፍሌሜ ሁለቱ እጇቿን በአንገቴ ላይ አቆላልፋየጎመራ ፖም በሚመስለው ስስ ከንፈሯ ትመጠምጠኝ ገብታለች።
ሁለታችንም ራሳችንን ውጠን ለሌላ አለም ለመውለድ የምናምጥ ተስፈኞች ነን ስል አሰብኩ።
እጆቿ አንገቴን ለቀው በፀጉሬ ዘለላዎች ውስጥ ይርመሰመሱ ጀመር። ጦርነቱ መጀመሩ ነው።
እኔም እጄ ስራ አላስፈታሁትም። እንደ እንቁሉል በስስት ይዣት እንደ ጣፋጭ ማንጎ ከናፍሯን መጠጥኩት። አየር ለመሳብ ብለን እረፍት አደረግን ትንፋሻችን እንደ ሲኦል ወላፈን ይጋረፋል።አንገቷ ስር ገብቼ እየሳምኳት በጆሮዋ ውስጥ አንሾካሾኩ።
እሷም ከጥልቁ ስሜት አፋፍ ላይ ሆና አንሾካሾከች።
ጊዜ ሳላጠፋ ወደ ከንፈሯ ተመልሼ እያካለብኩ ወደ አልጋው ላይ ጣልኳት። አብሬያትም ወደቅኩ።
እጆቼን በመላው አካላቷ ላይ አርመሰመስኩት እንደ ተራራ ተቀስሮ ሲወጋኝ የነበረው ጡቷን አለከልካይ እንደፈትል ፈተልኩት።
የትንፋሿን ሙቀት አልቻልኩም። ተነስቼ በሩን ቆልፌ ወደቅኩባት።ከዛ እንጃ ዙሩ ከረረ።
የሆነ ሰመመን ውርር አደረገኝ።ፍሌም ስታቃስት በጆሮዬ ስታንሾካሹክ ይታወቀኝ ነበር።
የሆነ ብቅ ጥልቅ የሚል ባህር ላይ ተጥለን የምንዋኝ አላዋቂ ዋናተኞች እንደሆንም ይሰማኝ ነበር።
......ደስስስ የሚል የስቃይ አለም....
በመሰንበት እና በመንቃት ወሰን የታጠረ ሽቦ።
የፍሌም ማቃሰት እየበዛ እየበረታ ሄዶ ብቅ ጥልቅ የሚለው ባህር ማዕበሉን አናውፆ ፀጥ አለ።ረጭ።
እየተንቀለቀለች የነበረች መከረኛ ነፍሴ ሰከነች።
ፍሌሜም እርግት አለች።አለምን በግዛቴ ስር ያኖርኳት ያህል እርካታ ተሰማኝ።አለሜን ሸመትኳት ፤ ህይወትን ከረጋ ምንጯ ተጎነጨዋት።
የባህሩ ተናውጦ እኛ ዋናተኞቹን ወደ ዳር ሲያወጣን ጨፍኜ እርካታዬን እያጣጣምኩ ነበር። አይኔን ገለጥኩኝ ፍሌሜ ክንዴን ተንተርሳ በጎን ደረቴ ላይ ተንታለች።
ስስ አልጋ ልብስ ለብሰናል። ፍሌምም ሆንን ባዶ ራቁታችን ነን። እቅፍ አድርጌ ሳምኳት። አጥብቃ አቀፈችኝ።
በዚህ ሰዓት በሩ በሀይል ተንኳኳ በድንጋጤ የምገባበት ጠፋ ፍሌም አይኗ ፈጠጠ።
"ማነው?" አልኩኝ ድንጋጤ በሸበበው ድምፀት።
"ግሩሜ ማነው ያስቀመጥኩትን ልብስ የወሰደው? ቆይ በእግዚአብሔር እዚህ ቤት የሚረዳኝ የለም ማለት ነው?"አለች ትርሃስ ንጭንጯን ጀመራት አልኩኝ በልቤ።
"የምን ልብስ ነው ማለቴ ምን የሚደረግ?" አልኳት ድንጋጤው አለቀቀኝም።......


ክፍል አስር ይቀጥላል........

ደራሲ C-ራክ
comment ፦ @ABDSEWANTED

"SHARE" @ONLYZEGET
⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷
.
ደራሲ ሲራክ
.
˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ●•٠·˙

⚀ ክፍል አስር ⚀ 🔟



"ማነው?" አልኩኝ ድንጋጤ በሸበበው ድምፀት።
"ግሩሜ ማነው ያስቀመጥኩትን ልብስ የወሰደው? ቆይ በእግዚአብሔር እዚህ ቤት የሚረዳኝ የለም ማለት ነው?"አለች ትርሃስ ንጭንጯን ጀመራት አልኩኝ በልቤ።
"የምን ልብስ ነው ማለቴ ምን የሚደረግ?" አልኳት ድንጋጤው አለቀቀኝም።
"የሚጠጣ ልብስ ምን አይነት ገገማ ልጅ ነው በእግዚአብሔር አንተ አመዳም ማነው ክፍሌ የገባው?"አለች። ትንሃስ በምትሰድበኝ ስድብ ፍሌም ትስቃለች።
"አንቺ ቆይ ግሩም በትርፍ ጊዜው የትርሃስን ልብስ ይለብሳል አሉሽ እንዴ? በቃ እኔ አላውቅም ያቺ ፍሌም መጥታ ነበር እሷ ቀይራ ይሆናል አልኳት።ፍሌም ድምፅ እንዳታወጣ እያስጠነቀቅኳት።
"ቆይ ይህቺ አይጥ የሆነች ልጅን ምን አባቴ ባደርጋት ነው የምትተወኝ ኧረ በእግዚአብሔር ታዲያ ምን ለብሼ ልሄድ ነው?" አለች ምርር ብሏታል።
"እኔጋ የግምበኞች ቱታ አለ። አተመቸሽ ላውስሽ ንፁህ ነው!።"አልኳት ካላናደድኳት ስትነጫነጭብኝ ነው የምትውለው።
"አንተ አመዳም ድሮስ ከአንተ ምን ይገኛል ኡፍ!....."እያጉረመረመች ሄደች።
ድምጿ እየራቀ እየራቀ ጠፋ ትንሽ ቆይተን ትርሃስ ስትወጣ ሰራተኛችን መጣች። ቤቱን ለሰራተኛዋ ትተን ሲኒማ ገባን።
....ከሲኒማ ስንወጣ መንገዱ በከተማ መብራቶች አሸብርቋል። የከድር ሰተቴ ሀገር ጅማ በሰፊው ሜዳ ላይ የበቀለች የአደይ አበባ ማሳ መስላለች።
ጅማ በጥንቱ ዘመን ገሙ ተብላ ትጠራ ነበር። ጅማ በ1960ዎቹ አከባቢ በንግድ የጦፈች ከተማ ነበረች። እንዲህ ባላደገች ጊዜ ፈረንጆች ተቆፍራ የወጣች ሀገር ናት ይሏት ነበር። ጣሊያን ሊለውጣት ብዙ ለፍቷል።ትንሿ ሮም እያለ ይጠራትም ነበር። በብዙ የጅማ ክፍሎች አይረሴ አሻራውን ጥሎባት ሄዷል ማለት ይቻላል። በተለይም በፈረንጅ አራዳ ፣ በመንቲና እና በፉርስታሌ ሰፈሮች።
ጅማ ብዙ ታሪክ ያላት ጥንታዊት ከተማ ከመሆኗም ባሻገር አባ ጅፋርን የመሰሉ ለአፍሪካ ስለ Relation ship ያርታወቁ እና ያስተማሩ ቀደምት እና ታላቅ ንጉስ የበቀለባት ፣ ከድር ሰተቴን የመሳሰሉ እልፍ ሀቀኛ ዶሰኞች ለእውነት ሟች የሆኑ ጀግኖች የበቀሉባት በዘመናችንም እነ አህመዲን ጀበልን እነ ዶ.ር ኤልያስ ገብሩ አእምሮን እና ሌሎች እልፍ ጀግኖችን ያበቀለች ከተማ ነች ጅማ ወይም ገሙ።....


ክፍል አስራ አንድ ይቀጥላል........

ደራሲ C-ራክ
comment ፦ @ABDSEWANTED

"SHARE" @ONLYZEGET
⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷

˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ●•٠·˙
.
ደራሲ ሲራክ
.
⚀ ክፍል አስራ አንድ ⚀ 1⃣1⃣


ከድር ሰተቴን የመሳሰሉ እልፍ ሀቀኛ ዶሰኞች ለእውነት ሟች የሆኑ ጀግኖች የበቀሉባት በዘመናችንም እነ አህመዲን ጀበልን እነ ዶ.ር ኤልያስ ገብሩ አእምሮን እና ሌሎች እልፍ ጀግኖችን ያበቀለች ከተማ ነች ጅማ ወይም ገሙ።....
ፍሌም ክንዴን እየጎተተች፤
"ግሩሜ ፍቅር ማለት ለአንተ ምን ማለት ነው?" አለችኝ
"እኔ እንጃ! ሲወራ እራሱ ይከብደኛል የሆነ ቀፋፊ ነገር ነው።" አልኳት ፊቴን ጨምደድ አድርጌ እንግሽግሽ እያደረግኩ።
"አትቀልድ ግሩሜ!"አለች ቆም ብላ ጎንተል እያደረገችኝ።
የሆነ ጊዜ ክፍል ውስጥ ቤዛዬ የምላት ቅመም የሆነች ልጅ ነበረች እና ስትነግረኝ 'ፍቅር ማለት አንድ ሴት እና ወንድ የሚሰክሱት ሳክስ ነው' ብላኝ ነበር።እሷንም ከፌስ ቡክ ላይ መንትፋት ነው!" አልኳት እና ፈገግ አልኩ።
"ደረቅ ነህ ግሩሜ ሙት። ምን አለበት ብትነግረኝ ለምሳሌ ፊልሙ ላይ እየወደደችው እና እያፈቀረችው ጨክና መለየቷ ጨካኝ እንጂ አፍቃሪ ያሰኛታል? ፍቅር የልባችንን ሀገር መፈለጊያ ነው ትካዜያችንን መሸሸጊያ?
የልባችን መሻት እንዲሳካ እና ከተፈጥሮ ጋር እንድንታረቅ እኛ ነን ወደ ፍቅር የምምቀርበው ወይስ እሱ ነው ያለንበት ድረስ የሚመጣው?" አለች።ፍሌም ስታመር እፈራታለሁ አነጋገሯ ይከብደኛል።ለህይወት ያላት ግንዛቤ እና ትርጉም ይደንቀኛል።
አሁን እየተናገረች ያለው ነገር ልቤን ወጋኝ።
"የኔ ቆንጆ ፍቅር እኮ በአፋችን እንደቀለለ የአፍ እዳ አይደለም። ይልቅ ይልቅ የልብ እውነት ነው። ፍቅር እኮ ጥበብ ነው በግርድፍ አማን እና አርነት ያልታበየ ህቡዕ አማን!
ፍሌሜ ስለፍቅር ተዘፍኗል ፣ ተገጥሟል ፣ በመፅሀፍ ተፅፏል ግን ከንቱ ነው። ልብን አሙቆ ከማቀዝቀዝ ባለፈ ምንም ፋይዳ የለውም።
በእብሪት ከአጠላን መንፈስ ጋር ተፋተን በሰከነ እኛነታችን እኛነታችንን አጭተን እና ድረን ካልሆነ ፍቅር በልባችን አይገባም። እኛም ከወደቅንበት አንነሳም።
ስለክርስቶስ በመስቀል ላይ ለፍቅር ስለመሰቀል በአንደበታችን ያወራነውን ያህል በልባችን መች ኖረነው እናውቃለን?
ሰው ስለፍቅር ይህን አደረገ ያን አደረገ እያሉ ፊልም ይሰራሉ መፅሀፍ ይፅፋሉ ሙዚቃ ይዘፍናሉ። ታዲያ ሰው ለፍቅር መሰዋዕት ካልሆነ ለምን መሰዋዕት ሊሆን ነው?
ፍቅር እኮ የእያንዳንዳችን የምሉዕነት መለኪያ ነው። በፍቅር ቤት የጎደለ በምንም ቤት ምሉዕ ሊሆን አይችልም።
እነዚያ እገሌ ለፍቅር እንዲህ ሆነ እንዲያ ሆነ እያሉ የሚሰብኩት ከንቱ ውዳሴ የትም አያደርሰንም።ፍቅር ኑረት ነው ሊያውም እንደ አለት በጠነከረ ቃፊር የታጠረ ኑረት።
አንዳንዴ ሰው መሆናችን በራሱ እያወቅን እየመሰለን የሚያደድበን አባዜ አለው።.....


ክፍል አስራ ሁለት ይቀጥላል........

ደራሲ C-ራክ
comment ፦ @ABDSEWANTED

"SHARE" @ONLYZEGET
⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷

˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ●•٠·˙
.
ደራሲ ሲራክ
.
⚀ ክፍል አስራ ሁለት ⚀ 1⃣2⃣



ፍቅር ኑረት ነው ሊያውም እንደ አለት በጠነከረ ቃፊር የታጠረ ኑረት።
አንዳንዴ ሰው መሆናችን በራሱ እያወቅን እየመሰለን የሚያደድበን አባዜ አለው።
ቆይ እኔ ያየሁትን ካላያችሁ እሞታለሁ ብሎ መደስኮር ምኑ ነው ጉብዝና???
ስለ ክርስቶስ መሰዋዕትነት ዘመንን ሙሉ መደስኮር ጀግንነት አይደለም። ይልቁንም ከክርስቶስ ባልተናነሰ መንገድ ስለፍቅር መሰዋዕት መሆኑ ነው ጀግንነት።
ክርስቶስማ የህይወት አሸናፊ ድርብርብ ጀግና ነው። ስለክርስቶስ አላወራሽም ማለት ፍቅርን አታውቂም ማለት አይደለም።ስለክርስቶስ ሁሌ አወራሽ ማለትም ፍቅርን ታውቂያለሽ ማለት አይደለም። አመንም አላመንም ከክርስቶስ መሰዋእትነት ባልተናነሰ መልኩ በሁላችንም ልብ ውስጥ ታላቅ ፍቅር አለ። አንደበታችን ሊገልፀው የማይችለው ትልቅ እውነት! ግድንግድ ሀቅ።
በእኛና በልባችን መካከል የወደቀው ዋርካ አላሻግር አለን እንጂ።
ፍሌሜ ይሄ በእኛና በልባችን መካከል የወደቀው ዋርካ መቆየቱ ሲበረታ አረም እያረባ አላስፈላጊ ፍሬ አፍርቶ የልባችንን ሀገር ጋርዶታል።
እኛም አረሙን ከመንቀል ይልቅ ተስማምቶን እየኖርን ነው።
የኔ ፍሌም ፍቅር እኮ የሞት መድሃኒት ናት። ሰው የሞት ሞቱን የሚሞተው ነብስ እና ስጋው ስትለያይ ሳይሆን ፍቅርን ሲያጣ ነው።"አልኳት አይኗን ቡዝዝ አድርጋ በፅሞና ስታዳምጠኝ ከቆየች በኃላ እምባ በአይኗ ሞልቶ የአይን ሽፋሏን አረጠበው።
"ግሩሜ እዚህ የሚደርስ ፍቅር አለኝ ብዬ አስቤ አላውቅም! እወድሃለሁ ግሩሜ"አለች።
ከትርሃስ ጋር ሁሌ የምንነታረካት ነገር ዛሬ ቦታዋን አገኘች አልኩኝ በልቤ። አባብያት መንገዳችንን ቀጠልን።
,,,,,,,,,,,,,, ►►►►►►►►►►►►► ,,,,,,,,,,,,

የሰው ኮቴ ዳና እና ኮሽታ ሰምቼ ዘወር ስል ፍሌም ናት። በዚህ ሰዓት እዚህ ወንዝ ዳር ትመጣለች ብዬ አልገመትኩም።ተነስቼ ቆምኩ ሰላምም ሳትለኝ ዋርካው ስር አጠገቤ ቁጭ አለች።
ድብርብር ብሏታል። ሳቋ እንደ ጉም በኗል። ፍዝዝ ብላለች።ከፍሌም ጋር ሁሌም ዋርካው ስር ስንቀመጥ "ሀደኮ" የምንላት የልጅ እናት ሁሌም እኛ በተቀመጥንበት ቀጥታ መጥታ ውኃ ትቀዳለች።
ውኃ እየቀዳች አይኗን ሰበር አድርጋ ትመለከተናለች። ደስ እንዲላት ፍሌሜን እስማታላሁ። ደስ እያላት አይኗን ሰበር አድርጋ በሀፍረት እጇን በአፏ ጭና እየሳቀች ትሄዳለች።
ሁሌም መጥተን እንደተቀመጥን ትመጣለች። እድስማት እየደጋገመች ታየናለች እስማታለሁ።እጇን በአፏ ጭና እየሳቀች ትሄዳለች።
ዛሬም ልክ ፍሌም ተክዛ መጥታ አጠገቤ ቁጭ እንዳለች መጣች። ውሃውን እየቀዳች ተመለከተችን።....


ክፍል አስራ ሶስት ነገ ምሽት ይቀጥላል........

ደራሲ C-ራክ
comment ፦ @ABDSEWANTED

"SHARE" @ONLYZEGET
⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷

˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ●•٠·˙
.
ደራሲ ሲራክ
.
⚀ ክፍል አስራ ሶስት ⚀ 1⃣3⃣


እጇን በአፏ ጭና እየሳቀች ትሄዳለች።
ዛሬም ልክ ፍሌም ተክዛ መጥታ አጠገቤ ቁጭ እንዳለች መጣች። ውሃውን እየቀዳች ተመለከተችን።
ፍሌሜን ለማውራት እጎተጉታታለሁ ዝም ትላለች። ሁኔታዋ አላማራትም ፊቷ ላይ የድብርት ድባብ አጥልቷል።
ሀደኮ ውሃውን ቀድታ ጨርሳ ፍሌሜን እስክስማት ትጠብቃለች። ደስ እንዲላት ወደ ፍሌሜ ጠጋ ብዬ ሳምኳት።ፍሌሜ ትካዜዋ አልለቀቃትም።ሀደኮ አይኗን በሚጥመለመለው የአዌቱ ወንዝ ላይ ተክላ ፍዝዝ ብላለች። ሀደኮ እንደዚህ ቀደሙ ደስ አላላትም። ትክዝ ብላ ውሃ መቅጃዋን ውሃው ውስጥ እየነከረች እያወጣች ትጫወት ገባች።ፍሌሜን ስስማት አይታለች ግን ስሜት አልሰጣትም።
እኔም ትካዜ ገባኝ፤ ሀደኮም የፍሌም ሀዘን እና ቁዘማ ተጋባባት። ሶስት ነፍሶች በአዌቱ ዳር በጥልቅ ተመስጥኦ ውስጥ ሰጥመዋል።ሁለቱ በዋርካው ስር አንዲቷ ከወንዙ ማዶ።
እንዳቀረቀርኩኝ የጩኸት ድምፅ ሰማው።ቀና ስል ሀደኮ ናት።እራሷን በሁለት እጇ ይዛ አንዳች ነገር በኦሮምኛ ቋንቋ በተማረረ አኳኃን በፍጥነት ታወራለች።
ደንግጬ ከተቀመጥኩበት ተነሳው ፍሌሜም ቆሌዋ ተገፎ አብራኝ ተነሳች።
ሀደኮ አይኗን የአዌቱ ወንዝ ላይ ተክላለች የሆነ ነገር ገባኝ። በውሃ መቅጃዋ ስትጫወት የአዌቱ ወንዝ መቅጃዋን ይዞባት ሄዶ ነው። አሳዘነችኝ እንድትረጋጋ በሰውነት ቋንቋ አስተዛዘንኳት ግን ቃል ማውጣት አልሆነልኝም።
ፍሌሜ ግን ነገሩ እረብሿት "አይዞሽ እሺ አዝናለሁ።" አለቻት የውሃው ሿሿታ ያሰማት አልመሰለኝም።
ሀደኮ እየተረጋጋች መሆኑን ከሁኔታዋ ተረዳው።እኔና ፍሌም ላይ አፍጥጣለች።
ሁኔታዋን ፍሌም እየተከታተለች ነበርና ነገሩ ስለገባት ወደ እኔ ተጠግታ ጉንጬን ሳመችኝ በምላሹ እኔ ደህና አድርጌ ከንፈሯን ሳምኳት ሀደኮ የግርምት ሳቅ እና ደስታ እየሸመቀቃት ውሃዋን ይዛ እየሳቀች ሄደች።
ሀደኮ እንደሄደች ፍሌሜ ተደግፋኝ ፀጉሬን እየፈተለች።
"ግሩሜ ምን ሆነህብኝ ነው?" አለችኝ በለሰለሰ ድምፀት። ድምጿ መከፋቷን ያሳብቃል። በትንሹ ሳግ እያደናቀፋት እንደምታወራኝ ተሰማኝ።
"ፍሌሜ ምንም አልሆንኩም ዝም ብዬ ነው እንዲሁ!"አልኳት የሆዴን ዘክዝኬ ብነግራት ደስ ይለኛል።ከእሷ በቀር በወጉ የሚረዳኝ ሰው እንደሌለ ውስጤ ያውቃል።
"ግሩሜ ፍሌም እኮ ነኝ ለምን የሆንከውን አትነግረኝም"አለችኝ ወደ አንገቷ ስር ጎትታ እያቀፈችኝ።...


ክፍል አስራ አራት ነገ ምሽት ይቀጥላል........

ደራሲ C-ራክ
comment ፦ @abdsewanted

አንብባችሁ ለወዳጆቻችሁ ሼር በቅንነት!!

"SHARE" @onlyzeget
HTML Embed Code:
2024/04/27 08:03:36
Back to Top