TG Telegram Group & Channel
FŰŇ_ŽØÑĘ 😂😱 | United States America (US)
Create: Update:

⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷

˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ●•٠·˙
.
ደራሲ ሲራክ
.
⚀ ክፍል አስራ ሁለት ⚀ 1⃣2⃣

ፍቅር ኑረት ነው ሊያውም እንደ አለት በጠነከረ ቃፊር የታጠረ ኑረት።
አንዳንዴ ሰው መሆናችን በራሱ እያወቅን እየመሰለን የሚያደድበን አባዜ አለው።
ቆይ እኔ ያየሁትን ካላያችሁ እሞታለሁ ብሎ መደስኮር ምኑ ነው ጉብዝና???
ስለ ክርስቶስ መሰዋዕትነት ዘመንን ሙሉ መደስኮር ጀግንነት አይደለም። ይልቁንም ከክርስቶስ ባልተናነሰ መንገድ ስለፍቅር መሰዋዕት መሆኑ ነው ጀግንነት።
ክርስቶስማ የህይወት አሸናፊ ድርብርብ ጀግና ነው። ስለክርስቶስ አላወራሽም ማለት ፍቅርን አታውቂም ማለት አይደለም።ስለክርስቶስ ሁሌ አወራሽ ማለትም ፍቅርን ታውቂያለሽ ማለት አይደለም። አመንም አላመንም ከክርስቶስ መሰዋእትነት ባልተናነሰ መልኩ በሁላችንም ልብ ውስጥ ታላቅ ፍቅር አለ። አንደበታችን ሊገልፀው የማይችለው ትልቅ እውነት! ግድንግድ ሀቅ።
በእኛና በልባችን መካከል የወደቀው ዋርካ አላሻግር አለን እንጂ።
ፍሌሜ ይሄ በእኛና በልባችን መካከል የወደቀው ዋርካ መቆየቱ ሲበረታ አረም እያረባ አላስፈላጊ ፍሬ አፍርቶ የልባችንን ሀገር ጋርዶታል።
እኛም አረሙን ከመንቀል ይልቅ ተስማምቶን እየኖርን ነው።
የኔ ፍሌም ፍቅር እኮ የሞት መድሃኒት ናት። ሰው የሞት ሞቱን የሚሞተው ነብስ እና ስጋው ስትለያይ ሳይሆን ፍቅርን ሲያጣ ነው።"አልኳት አይኗን ቡዝዝ አድርጋ በፅሞና ስታዳምጠኝ ከቆየች በኃላ እምባ በአይኗ ሞልቶ የአይን ሽፋሏን አረጠበው።
"ግሩሜ እዚህ የሚደርስ ፍቅር አለኝ ብዬ አስቤ አላውቅም! እወድሃለሁ ግሩሜ"አለች።
ከትርሃስ ጋር ሁሌ የምንነታረካት ነገር ዛሬ ቦታዋን አገኘች አልኩኝ በልቤ። አባብያት መንገዳችንን ቀጠልን።
,,,,,,,,,,,,,, ►►►►►►►►►►►►► ,,,,,,,,,,,,

የሰው ኮቴ ዳና እና ኮሽታ ሰምቼ ዘወር ስል ፍሌም ናት። በዚህ ሰዓት እዚህ ወንዝ ዳር ትመጣለች ብዬ አልገመትኩም።ተነስቼ ቆምኩ ሰላምም ሳትለኝ ዋርካው ስር አጠገቤ ቁጭ አለች።
ድብርብር ብሏታል። ሳቋ እንደ ጉም በኗል። ፍዝዝ ብላለች።ከፍሌም ጋር ሁሌም ዋርካው ስር ስንቀመጥ "ሀደኮ" የምንላት የልጅ እናት ሁሌም እኛ በተቀመጥንበት ቀጥታ መጥታ ውኃ ትቀዳለች።
ውኃ እየቀዳች አይኗን ሰበር አድርጋ ትመለከተናለች። ደስ እንዲላት ፍሌሜን እስማታላሁ። ደስ እያላት አይኗን ሰበር አድርጋ በሀፍረት እጇን በአፏ ጭና እየሳቀች ትሄዳለች።
ሁሌም መጥተን እንደተቀመጥን ትመጣለች። እድስማት እየደጋገመች ታየናለች እስማታለሁ።እጇን በአፏ ጭና እየሳቀች ትሄዳለች።
ዛሬም ልክ ፍሌም ተክዛ መጥታ አጠገቤ ቁጭ እንዳለች መጣች። ውሃውን እየቀዳች ተመለከተችን።....

ክፍል አስራ ሶስት ነገ ምሽት ይቀጥላል........

ደራሲ C-ራክ
comment ፦ @ABDSEWANTED

"SHARE" @ONLYZEGET

>>Click here to continue<<

FŰŇ_ŽØÑĘ 😂😱

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)