TG Telegram Group & Channel
FŰŇ_ŽØÑĘ 😂😱 | United States America (US)
Create: Update:

⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷

˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ●•٠·˙
.
ደራሲ ሲራክ
.
⚀ ክፍል አንድ ⚀ 1⃣

➲ .... የሀምሌን ሰማይ እንደ እኔ ከፍቶታል።ቀኑ ገና በንጋቱ ድብስብስ እያለ ነው የነጋው። ሀምሌ 1 ቀን 2010 ዓ.ም እለተ እሮብ ጅማ መድሃኒያለም ሰፈር!
የሰኔ ሰላሳውን ግፊያ ፣ ትዝታ እና ናፍቆቱን አፈር ምሼ የቀበርኩበት እለት ከአስራ አንደኛ ክፍል ወደ አስራ ሁለተኛ ክፍል የመግባቴን ብስራት የሰማውበት ማግስት።
በእለቱ የእለቷ ፀሀይ ገና በሰበካው የተራሮችን ግርዶሽ ቀዳ ብቅ አላለችም።
እኔ አልጋዬ ላይ እንዳለሁ ድብርት ተጫጫነኝ። ከክፍል ጓደኞቼ በመለየቴ ክፍት ፣ ጥብብ ፣ ጭንቅ አለኝ።
ገና በጅማሬው ጠቁሮ እንደ አባቴ ቁጣ የሚያጉረመርመው ሰማይ በላዬ ላይ የወደቀ እስኪመስለኝ ድረስ ድብርት ተጫጫነኝ።
በአስቀያሚ ድብርት ውስጥ እንዳለሁ የክፍሌ በር ሲደበደብ ሰማው፤ እናቴ ናት።
መልሴን ሳትጠብቅ "ግሩም አባትህ ከሰል አምጥቷል ተነስና ከዘበኛው ጋር አስገባልኝ ዛሬ ውሎህን ተጋድመህ መዋልህ እኮ ነው! ግሩም!" አለች
ዝም አልኩኝ
" አንተ ግሩም " አለች ድምጿን ከፍ አድርጋ የበሩን ኳኳታ መጠን እየጨመረች " አቤት " አልኩኝ ድምፄን ከፍቶታል። "ግሩም! ምነው ልጄ አመመህ እንዴ? ድምፅህም ልክ አይደለም " አለች በሩ ላይ ጆሮዋን ልጥፍ አድርጋ።
"ደህና ነኝ" አልኳት በአጭር ቃል።
"ተነስ ቁርስህንም ብላ አባትህም መንገድ ላይ ከሰል አውርዷል እሱንም አስገባልኝ ጎሽ" አለች
"እሺ መጣሁ" አልኩኝ
ከእናቴ አጉል ውትወታ ለመትረፍ ብቻ! እናቴ ብዙም ሳትቆይ እንደሄደች የተረዳውት የኮቴዋ ዳና ከክፍሌ እየራቀ መሆኑን ስረዳ ነው።
አባቴ ልምድ ያለው የNGO ሹፌር ነው። የበርካታ አመታት የአሽከርካሪነት ልምድ አለው። በብዛት የመስክ ስራዎች ላይ ይሳተፋል።
ለመስክ ስራ ወደሌላ አከባቢ ሲሄድ ሲሄድ በርከት ያሉ ከሰሎችን ይዞ ይመጣል።
ዛሬም ለሰባት ቀናት ከቆየበት የመስክ ስራ መመለሱ ነበር። መምጣቱን ሳውቅ እና ወደ አስራ ሁለተኛ ክፍል መግባቴ ትዝ ሲለኝ በዚህ የድብርት ስሜት አባቴን መቀበል አልፈለግኩም።
የታዘዝኩትን ከሰል አስገብቼ ከቤት ወጥቼ ልውል ወስኜ ከአልጋዬ ወረድኩና እንደነገሩ ለባብሼ ከክፍሌ ወጣሁ።......

ክፍል ሁለት ምሽት 2:00 ይቀጥላል........

Any comment @abdsewanted

መልካም አዳር!!

"SHARE" @onlyzeget

>>Click here to continue<<

FŰŇ_ŽØÑĘ 😂😱

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)