TG Telegram Group & Channel
FŰŇ_ŽØÑĘ 😂😱 | United States America (US)
Create: Update:

⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷

˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ●•٠·˙
.
ደራሲ ሲራክ
.
⚀ ክፍል ሰባት ⚀ 7⃣

ያን ሰሞን ቁዘማ ስራዬ ሆነ። ቤት ውስጥ ንጭንጭ አበዛለው ብቻዬን መዋል ማደርን አዘወትራለው። ፍሌም ስታስጠራኝም የለም አስብል ጀምሬያለሁ።
ስትሄድ ደግሞ ይከፋኛል። ውስጤ ፍሌሜን ይራባል።ትኩስ እምባዬ እንደሳማ ጉንጬን እየለበለበኝ ይወርዳል። ምን መወሰን እንዳለብኝ ግራ ገባኝ የማዋየው ጓደኛም ሆነ ወዳጅ የለኝም። የነበሩትንም ክረምቱ ወስዷቸዋል።
ከፍሌም አንደበት 'እዬዳለሁ አልሄድም 'የሚሉትን አቁሳይ ፈዋሽ ቃላቶችን ከአንደበቷ ሳልሰማ ልቤ፤ ልቤ ከራሱ ጋር ግብግብ ገጥሞ ሰርክ ያስጨንቀኝ ጀምሯል።
ማንን የውስጤን አዋይቼው ከልቤ ሀገር ዘልቆ ባማለደኝ እላለሁ። ግን ማለት ብቻ ነው። ወኔ እንደ ኳስ ተጫዋች ቁምጣ ካጠረኝ ሰነባብቷል።
ቤት ውስጥ ጠዋቱን ቁርስ ሳልበላ ስቆዝም እውላለሁ። በእናቴ ልመና እና ግዝት ትንሽ ነገር ቀማምሼ ፍሌሜን ብዙ ነገር ወዳዋየሁባት የጋራ ቦታችን እሄዳለሁ።
ጅማ ፉርስታሌ ሰፈር አዌቱ ወንዝ ዳር ዋርካው ስር ተቀምጬ በመሬቱ ላይ እየተጥመለመለ ሲሄድ በልዩ ፍቅር የማየውን የአዌቱን ወንዝ እየተመለከትኩ ፍሌሜን በጥልቅ ተመስጦ እና ጥልቀት የሀሳብ ባህር ውስጥ ሆኜ አሰላስላታለሁ።
በማሰላሰሌ ውስጥ አንድ ሃሳብ ከተፍ አለልኝና የቁዘማዬን ልጓም ከአዌቱ ዳር ካለው ዋርካ ሸብ አድርጌ በትዝታ ሰረገላ ተሳፍሬ አድማሱን እየቀደድኩ ነጎድኩኝ።

ቀኑ አንድ እሁድ ከሰዓት ነው።
የአዌቱ ወንዝ ዳር እና ከባቢው ጭር ብሏል። ውሃው እና ድንጋዮቹ ተጋጭተው ከሚፈጥሩት ድምፅ በቀር ምንም የሚሰማ ነገር የለም።
እኔ ግዙፉን የአዌቱን ዳር ዋርካ ተደግፌ የሆነ ወቅት ከፍሌም ጋር ሲኒማ አይተን ስላየነው ሲኒማ የተጠያየቅነው ነገር ትዝ አለኝ።
........ ቀኑ ደመናማ ነበር። ማንም በቤት ውስጥ የለም አልነበረም። እናቴ ሰርግ ብላ ጠዋት እንደወጣች አልተመለሰችም። ቅዱስ መንደር ሊጫወት ሄዷል። ትርሃስ ክፍሏ ተኝታለች። ፍሌም ቤቷ ደብሯት እኛ ጋ ልትጫወት መጣች። እኔ ትርሃስ የተከለቻቸውን አበባዎች እየነቀልኩላት ነበር። የቤታችን ድባብ ጭር እንዳለ ነው። ፍሌሜ ሰላም ብላኝ ደረጃዎቹ ላይ ተቀመጠች። ከቧንቧው ላይ በቱቦ ውሃው ቀድቼ እያጠጣሁኝ ተንኮል አስቤ ፍሌሜን ጠራዋት መጣች። በቱቦ ውስጥ እየተንፎለፎለ የሚመጣውን ውሃ ወደ እሷ መልሼ ዝም አልኩ። ውሃው ሲነካት ፍሌም ጮኸች።
ልታስቆመኝ ታገለች። ውሃው ሁለታችንም ላይ ወረደ ተረጫጨን ሁለታችንም በሰበስን ኃላ ላይ ፍሌሜን ሳያት ደስ ብሏታል። ጥቁሩ ዞማ ፀጉሯ በፊቷ ላይ ተበታትኗል።
ፈገግ አለች። ጎትቼ እቅፌ ውስጥ ወሸቅኳት። እንደተራራ የተገተሩ አጎጠጎጤ ጡቶችዋ ደረቴን እንደ አድዋ ጦር ወግተው በሰራ አካላቴ ላይ ሙቀት ለቀቁብኝ።........

ክፍል ስምንት ነገ ምሽት ይቀጥላል........

ደራሲ C-ራክ
comment ፦ @ABDSEWANTED

"SHARE" @ONLYZEGET

አንብባችሁ ለወዳጆ ሼር ያድርጉት!

>>Click here to continue<<

FŰŇ_ŽØÑĘ 😂😱

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)