TG Telegram Group & Channel
FŰŇ_ŽØÑĘ 😂😱 | United States America (US)
Create: Update:

⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷

˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ●•٠·˙
.
ደራሲ ሲራክ
.
⚀ ክፍል አስራ አንድ ⚀ 1⃣1⃣

ከድር ሰተቴን የመሳሰሉ እልፍ ሀቀኛ ዶሰኞች ለእውነት ሟች የሆኑ ጀግኖች የበቀሉባት በዘመናችንም እነ አህመዲን ጀበልን እነ ዶ.ር ኤልያስ ገብሩ አእምሮን እና ሌሎች እልፍ ጀግኖችን ያበቀለች ከተማ ነች ጅማ ወይም ገሙ።....
ፍሌም ክንዴን እየጎተተች፤
"ግሩሜ ፍቅር ማለት ለአንተ ምን ማለት ነው?" አለችኝ
"እኔ እንጃ! ሲወራ እራሱ ይከብደኛል የሆነ ቀፋፊ ነገር ነው።" አልኳት ፊቴን ጨምደድ አድርጌ እንግሽግሽ እያደረግኩ።
"አትቀልድ ግሩሜ!"አለች ቆም ብላ ጎንተል እያደረገችኝ።
የሆነ ጊዜ ክፍል ውስጥ ቤዛዬ የምላት ቅመም የሆነች ልጅ ነበረች እና ስትነግረኝ 'ፍቅር ማለት አንድ ሴት እና ወንድ የሚሰክሱት ሳክስ ነው' ብላኝ ነበር።እሷንም ከፌስ ቡክ ላይ መንትፋት ነው!" አልኳት እና ፈገግ አልኩ።
"ደረቅ ነህ ግሩሜ ሙት። ምን አለበት ብትነግረኝ ለምሳሌ ፊልሙ ላይ እየወደደችው እና እያፈቀረችው ጨክና መለየቷ ጨካኝ እንጂ አፍቃሪ ያሰኛታል? ፍቅር የልባችንን ሀገር መፈለጊያ ነው ትካዜያችንን መሸሸጊያ?
የልባችን መሻት እንዲሳካ እና ከተፈጥሮ ጋር እንድንታረቅ እኛ ነን ወደ ፍቅር የምምቀርበው ወይስ እሱ ነው ያለንበት ድረስ የሚመጣው?" አለች።ፍሌም ስታመር እፈራታለሁ አነጋገሯ ይከብደኛል።ለህይወት ያላት ግንዛቤ እና ትርጉም ይደንቀኛል።
አሁን እየተናገረች ያለው ነገር ልቤን ወጋኝ።
"የኔ ቆንጆ ፍቅር እኮ በአፋችን እንደቀለለ የአፍ እዳ አይደለም። ይልቅ ይልቅ የልብ እውነት ነው። ፍቅር እኮ ጥበብ ነው በግርድፍ አማን እና አርነት ያልታበየ ህቡዕ አማን!
ፍሌሜ ስለፍቅር ተዘፍኗል ፣ ተገጥሟል ፣ በመፅሀፍ ተፅፏል ግን ከንቱ ነው። ልብን አሙቆ ከማቀዝቀዝ ባለፈ ምንም ፋይዳ የለውም።
በእብሪት ከአጠላን መንፈስ ጋር ተፋተን በሰከነ እኛነታችን እኛነታችንን አጭተን እና ድረን ካልሆነ ፍቅር በልባችን አይገባም። እኛም ከወደቅንበት አንነሳም።
ስለክርስቶስ በመስቀል ላይ ለፍቅር ስለመሰቀል በአንደበታችን ያወራነውን ያህል በልባችን መች ኖረነው እናውቃለን?
ሰው ስለፍቅር ይህን አደረገ ያን አደረገ እያሉ ፊልም ይሰራሉ መፅሀፍ ይፅፋሉ ሙዚቃ ይዘፍናሉ። ታዲያ ሰው ለፍቅር መሰዋዕት ካልሆነ ለምን መሰዋዕት ሊሆን ነው?
ፍቅር እኮ የእያንዳንዳችን የምሉዕነት መለኪያ ነው። በፍቅር ቤት የጎደለ በምንም ቤት ምሉዕ ሊሆን አይችልም።
እነዚያ እገሌ ለፍቅር እንዲህ ሆነ እንዲያ ሆነ እያሉ የሚሰብኩት ከንቱ ውዳሴ የትም አያደርሰንም።ፍቅር ኑረት ነው ሊያውም እንደ አለት በጠነከረ ቃፊር የታጠረ ኑረት።
አንዳንዴ ሰው መሆናችን በራሱ እያወቅን እየመሰለን የሚያደድበን አባዜ አለው።.....

ክፍል አስራ ሁለት ይቀጥላል........

ደራሲ C-ራክ
comment ፦ @ABDSEWANTED

"SHARE" @ONLYZEGET

>>Click here to continue<<

FŰŇ_ŽØÑĘ 😂😱

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)