TG Telegram Group & Channel
FŰŇ_ŽØÑĘ 😂😱 | United States America (US)
Create: Update:

⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷

˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ●•٠·˙

ደራሲ ሲራክ
.
⚀ ክፍል ስድስት ⚀ 6⃣

"ግሩሜ እንዴት ነህ?" አለችኝ ፈገግታዋ ከፊቷ ሳይረጋ ከለበሰችው ኮት ጋር ትልቅ ሰው መስላለች።
"ደህና ነኝ ከየት ነው በዚህ ሰዓት?"አልኳት
"ባሌ ሰለቸሽኝ ሲለኝ ለአንዷ ሰጥቼው መመለሴ ነው አልገርምም?" አለችኝ ይበልጥ ፈገግ እያለች፤ ፈገግታዋ ልብ ያሞቃል በዚህ ብርዳም ምሽት እሷን በማግኘቴ ተደሰትኩ።
"ይገርምሻል እኔም ሚስቴ የሆነ ሰውዬ ጋ አየናት ያውም የሆነች ቆንጅዬ ሴት ናት አሉ 'ባሌን ውሰጂው ብላ የሰጠችው' ብለውኝ እኮ ጉድ ብዬ ስልኬን ስዘጋ ተገናኘን ወይ መገጣጠም!" አልኳት።
ከት ብላ ስቃ ስታበቃ "አቦ በአላህ ደስ ትላለህ አሳከኝ!" አለች በልስልስ ጥዑም አንደበቷ።
"ይልቅ ከየት ነሽ?" አልኳት ውብ አይኗ ላይ አይኔን ተክዬ
"አጎቴ ከጉዋደኞቹ ጋር አስተዋውቆኝ እቆያለሁ አንቺ ብሎኝ መመለሴ ነው። አንተስ ግሩሜ?" አለች።
አይ እኔማ ወክ እያደረኩ ነበር ካልቸኮልሽ ለምን ተቀምጠን አናወራም ?" አልኳት የመናፈሻውን ግቢ በአይኔ እየጠቆምኳት።
ጭንቅላቷን በመነቅነቅ እሺታዋን ገለፀችልኝና ገብተን የመናፈሻው ወንበር ላይ ተቀምጠን ስለብዙ ነገር አወራን። ወሬያችን ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ፍሌም በሳቅ ትንከተከት እንደነበር አስታውሳለሁ!።
ጥቂት የማይባል ጊዜ እንዳወራን የሰዓቱን መንጎድ ተመልክታ እንድንሄድ ጠየቀችኝ። ተያይዘን ከመናፈሻው ቅፅር ግቢ ስንወጣ ሰዓቱ ሁለት ሰዓት ከሰላሳን አጋምሶ ለሶስት ሰዓት ግስገሳውን አፍጥኖታል።
ታክሲም ሆነ ባጃጅ ጥድፊያ ነው። በእግራችን አዘገምን በጉዞአችን በበረደኝ ሰበብ ከፍሌሜ ጋር እየተጠጋጋን እየተጠጋጋን በስተመጨረሻ ተቃቅፈን ጉዞአችንን ባጀነው።
የእሷ መታጠፊያ ጋ ስንደርስ ይበልጥ ተቃቅፈን ትንሽ ከቆየን በኃላ "ደህና እደር ግሩሜ " አለችኝ "ደህና እደሪልኝ" ብዬ አፀፋውን መልሼ ወደ ቤት አዘገምኩ።
አልጋዬ ላይ በጀርባዬ ተንጋልዬ ያፈራነውን እያመሰኳሁ እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ።

🔅🔅🔆🔆🔆🔅🔅🔅🔆🔆🔆🔆🔆

ከዛች ምሽት ወዲህ ከፍሌም ጋር በሰፊው መገናኘት መቀራረብ ቻልን። ፍሌም ከድሬ በበለጠ እዚህ ከመጣች ወዲህ ደስታዋ እንደጨመረ ዘውትር ታወሳኛለች። አጎቷ ለፊልድ ወጣ ካለ መናፈሻው አይቀረን ሲኒማው አይቀረን የወንዝ ዳር ደፎች አይቀሩን ፣ በየመንገዱ ላይ ስንፈስ ነው የምንውል የምናመሸው!?።
እንዲህ እንዲህ እያልን ክረምቱን ለመባጀት ተቃረብን ሀምሌን ሸኝተን ነሀሴን አጋምሰነዋል። ይሄኔ እኔ ክፉኛ ጨነቀኝ ፍሌሜን ማጣት አልፈለኩም እሷን ማጣት ሞትን የመቀበል ያህል ከበደኝ። ስቀርባት እንደምትርቀኝ አልታወቀኝም ነበር መሰል።
ያን ሰሞን ቁዘማ ስራዬ ሆነ። ቤት ውስጥ ንጭንጭ አበዛለው ብቻዬን መዋል ማደርን አዘወትራለው። ፍሌም ስታስጠራኝም የለም አስብል ጀምሬያለሁ።

​​

ክፍል ሰባት ነገ ምሽት ይቀጥላል........

ደራሲ Cራክ
comment ፦ @ABDSEWANTED

"SHARE" @ONLYZEGET

>>Click here to continue<<

FŰŇ_ŽØÑĘ 😂😱

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)