TG Telegram Group Link
Channel: የያሲኔ ወዳጅ 🇪🇹PAGE🇪🇹
Back to Bottom
ዛሬ ዓለምን እያነጋገረ ከዋሉትው ዜናዎች መካከል አንዱ ትልቅ ዜና ስድስት የዕድሜ ልክ የተበየነባቸው ፍልስጤማዉያን የኢስላሚክ ጂሃድ ከፍተኛ አባላት በጉድጓድ ዉስጥ ለዉስጥ አልፈው ዛሬ ማለዳ በከፍተኛ ደረጃ ጥበቃ ከሚደረግለት የኢስራኢል እስር ቤት ማምለጥ ነው፡፡
ከእስር ቤት ዉስጥ ወደ ዉጭው አጥር የተቆፈረው ጉድጓድ አሥራ ምናምን ሜትር ርዝማኔ አለው፡፡ ከስድስቱ አራቱ ዕድሜልክ የተፈረደባቸው ነበሩ። ሰዎቹ በሄሌኮፍተር እገዛ ጭምር እየተፈለጉ ነው፡፡

“በርተህ ቆፍር የጉድጓዱ የመጨረሻው ጫፍ ላይ የምታገኘው ብርሃንን ነው” ይላሉ ፍልስጤማውያን በመፈክራቸው ስለ ነፃነት ዋጋ ሲናገሩ፡፡
'ሰው ነፃነቴን ካለ ድንጋይ ይሰረስራል።'
Muhammed Seid Abx
ታላቅ የሂፍዝ ተማሪዎች የምርቃት ፕሮግራም

እሁድ መስከረም 09 /2014 ከጠዋቱ 3: 00 ጀምሮ በቄራ ሰላም መስጂድ ውስጥ የሚገኘው አንደሉስ መድረሳ ማዕከል በመጀመሪያ ዙር የአዳር የቁርአን ሂፍዝ ትምህርት ለ2 ተከታታይ አመታት ሲያስተምራቸው የነበሩትን ተማሪዎች እንዲሁም በክረምት ኮርስ ለ1ወር የተማሩትን ተማሪዎች ታላላቅ አሊሞች፣ዳኢዎች፣ኡስታዞች እንዲሁም ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት በድምቀት ያስመርቃል።

በዚህ ታላቅ ፕሮግራም ላይ እንድትገኙ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል
አንደሉስ የቁርኣን ሂፍዝ ማዕከል ሲያስተምራቸው የነበሩ ተማሪዎችን በዛሬው እለት በድምቀት አስመረቀ።

በቄራ ሰላም መስጂድ ውስጥ የሚገኘው አንደሉስ መድረሳ ማዕከል በመጀመሪያ ዙር የአዳር የቁርአን ሂፍዝ ትምህርት ለ2 ተከታታይ አመታት ሲያስተምራቸው የነበሩትን ተማሪዎች እንዲሁም በክረምት ኮርስ ለ1ወር የተማሩትን ተማሪዎች ታላላቅ አሊሞች፣ዳኢዎች፣ኡስታዞች እንዲሁም ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት በድምቀት አስመርቋል።
#መሞትማ ሁሉም ነፍስ ይሞታል!

ይህ ሰው የሞተው ግን ለአራት ወር የአላህን ቃል ለማሰማት ከሞቀው ቤቱ በራቀበት አላህ ቀርቦት ነው!
'ኹሩጅ' ላይ እያለ ድካም በቃህ እረፍ ተብሎ ነው!
ኢላሂ! እንደዚህ ዓይነት ሞት!

© tofiq bahru
የሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ሚኒስትሯ በገዛ ፍቃዳቸው ሥራቸውን መልቀቃቸውን አሳወቁ

የሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር ፊልሳን ዐብዱላሂ መሐመድ በገዛ ፍቃዳቸው ኃላፊነታቸውን መልቀቃቸውን አሳውቀዋል።

ወይዘሮ ፊልሳን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጻፉት የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ፣ ሥራውን ከተቀበሉበት ወቅት ጀምሮ የነበረውን ሁኔታ አንስተዋል።

ሆኖም ሚኒስትሯ ሥነ ምግባርን የሚጥሱ ሁኔታዎች መተማመንን እንደሚጥሱ ከመጥቀስ ውጭ ሥራቸውን ለምን እንደለቀቁ በይፋ አልገለጹም።

ወይዘሮ ፊልሳን ዐብዱላሂ መሐመድ የሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት ከመጋቢት 3፣ 2012 ጀምሮ ነው። 🔴


መረጃው ያደረሰን Amba Digital - አምባ Amba Digital - አምባ ዲጂታል
ዶ/ር ዐቢይ ጠ/ሚ ሆነው ተሾሙ።

ዶክተር ዐቢይ አህመድ አሊ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።
የአፋር ክልል የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃለፊ የነበሩት ወ/ሮ ዛራ ሁመድ የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባዔ ሆነው ተመርጠዋል።
ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ፣ ኢንስታግራም እና ሜሴንጀር መተግበሪያዎች መስራት አቁመዋል።

በፌስቡክ ስር የሚገኙት መተግበሪያዎቹ በተለያዩ የዓለም ሀገራት መስራት አቁመዋል። ኢትዮጵያ ውስጥም አገልግሎቶቹ ተቋርጠዋል።

መተግበሪያዎቹ በበርካታ አገራት መቋረጣቸውን ዓለም ዐቀፉ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቆጣጣሪ ተቋም ኔትብሎክስ አሳውቋል።

ችግሩ በምን ምክንያት እንደተፈጠረ ፌስቡክ እስካሁን ያለው ነገር የለም።
ከ6 ሰዓታት በላይ ተቋርጠው የቆየቱ ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ፣ ኢንስታግራም እና ሜሴንጀር አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።

ፌስቡክ ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ ከመጠየቅ ውጭ እስካሁን ችግሩ በምን ምክንያት እንደተፈጠረ ማብራሪያ አልሰጠም።

በፌስቡክ መቋረጥ በ5 ሰዓታት ውስጥ ብቻ የማርክ ዙከርበርግ የግል ሃብት በ7 ቢሊዮን ዶላር ዝቅ ማለቱን ብሉምበርግ ዘግቧል።

የፌስቡክ መተግበሪያዎች መቋረጥን ተከትሎ በትዊተር ፕላትፎርሙ ላይ ከፍተኛ የሆነ የተጠቃሚዎች ቁጥር ተመዝግቧል።
የውድ ነብያችን(ሰዓወ) ጠላት በሞት ተወገደ

ከሞት ለማምለጥ በፖሊስ ሲጠበቅ የቆየው ከነጠባቂ ፖሊሶቹ ሞተ

የውዱን ነብይ ክብር ለማጉደፍ በማሰብ በ2007 በውሻ ምስል ላይ የሳቸው ምስል ነው በሚል የካርቶን ምስል ሰርቶ የአለምን ሙስሊም አስቆጥቶ የነበረው ስዊዲናዊው ግለሰብ በመኪና አደጋ ህይወቱ አልፏል::

ላርስ ቪልክስ የተባለው ይህ ግለሰብ ይህን የካርቶን ምስል ሰርቶ ካሰራጨ ቡኃላ በደረሰበት ውግዘት ለደህንነቱ ሲባል በፖሊስ ጥበቃ ስር ህይወቱን ሲመራ የቆየ ሲሆን በሲቭል ፖሊሶች መኪና በሁለት ሲቭል ፖሊሶች ታጅቦ በመኪና እየየጓዘ በነበረበት ወቅት ከትልቅ መኪና ጋር ተጋጭቶ በ 75አመቱ ህይወቱ አልፏል::

በሰራው ወንጀል ስጋት ከሞት ለማምለጥ በፖሊስ ሲጠበቅ ቢቆይም ከነጠባቂ ፖሊሶቹ ሞት በመኪና አደጋ ጠልፎ ወስዶታል::

ይህን ሙጅሪም ግለሰብ የእጁን አላህ ይሰጠው ዘንድ ዱዓችን ነው! Abu Dawd Osman
HTML Embed Code:
2024/05/01 04:39:30
Back to Top