TG Telegram Group Link
Channel: ከራድዮን
Back to Bottom
💠 እንኳን ለፍልሰታ ጾም በሰላም አደረሳችሁ !!!
❤️❤️❤️
ጾሙን የሰላም ፣የፍቅር ፣የምህረት ያድርግልን::

#አሜን

https://hottg.com/+AAAAAFSJ49GBC3YRZoSNHQ
.
እንኳን #ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ትንሣኤና ዕርገት አደረሳችሁ !

"ሞት ሆይ! መውጊያህ የት አለ?"
(1ኛ ቆሮ.15:55)

#ሼር
__

#share #share ⤵️

https://hottg.com/+AAAAAFSJ49GBC3YRZoSNHQ
✣ ቅዱስ ሚካኤል ✣
.
እንኳን ቅዱስ ሚካኤል ወርሀዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ::
.
@gitim_menfesawi
@gitim_menfesawi
.
" ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት"

(የያዕቆብ መልእክት 1:2-3)

@gitim_menfesawi
@gitim_menfesawi
ታስበላብሃለች

አንድ እምነት የነበረው እረኛ ነበረ ይባላል፡፡ ምሳ ለመብላት ሲፈልግ ያሰማራቸውን በጎች ለቅዱሳን፣ ለመላእክት አደራ ሰጥቶ ይሔዳል፡፡

"ቅዱስ ገብርኤል ሆይ! እነዚህን በጎቼ ከተኩላ ጠብቅልኝ" ብሎት ይሔዳል፡፡ እንደ እምነቱም በጎቹ ተጠብቀዉለት ያገኛቸዋል፡፡ ሌላ ቀን ደግሞ "ቅዱስ ሚካኤል ሆይ! አንተ ጠብቅልኝ" ይሏል፡፡ እንዲህ በቅዱሳን እያስጠበቀ ምሳውን በልቶ ይመጣል፡፡

አንድ ቀን፦ "እመበቴ ሆይ! ዛሬ አንቺ ጠብቂልኝ" ብሎ ወደ ቤቱ ይሔዳል፡፡ አባቱ አገኙትና፦ "ዛሬ ለማን አስጠብቀህ መጣህ?" አሉት፡፡ "ለእመቤታችን አስጠብቄ መጣሁ" አላቸው፡፡ እርሳቸውም፦ "አዬ ልጄ! እርሷ'ማ ታስበላብሃለች" አሉት፡፡ "ለምን? ቅዱሳን፣ ጻድቃን፣ መላእክት የጠበቁትን እርሷ አትጠብቅምን?" ይላቸዋል፡፡ "አይ ልጄ! የተጠማን ውሻ በወርቅ ጫማዋ ያጠጣች፡ የተራበ አውሬ መጥቶ ቢበላ ትከለክለዋለችን? ታስበላብሃለች" ሲሉት "እውነትም" ብሎ ወደ መንጎቹ ሮጠ ይባላል፡፡

ርህርህተ ሕሊና ሆይ! ዘወትር በምልጃሽ በቃል ኪዳንሽ ጠብቂን፡፡ አሜን!!!

(በመምህር Samuel Ayalneh)
_____________

@gitim_menfesawi
…የእግዚአብሔር ሐገር(ከተማ) ሆይ ነብያት ድንቅ ድንቅ ነገርን ተናገሩልሽ ፣ ደስ የተሰኙ የጻድቃን ማደሪያ ሆነሻልና የምድር ነገሥታት ሁሉ በብርሃንሽ ይሄዳሉ ። ሕዝቡም ሠራዊቶቻቸውም በብርሃንሽ ይሄዳሉ ማርያም ሆይ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑሻል። ካንቺ ለተወለደውም ይሰግዱለታል ያገኑታልም።

ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም

________

@gitim_menfesawi
+ አባቶቻችን እንዲህ አሉ +

"እሳትና ውኃን ማዋሐድ እንደ ማይቻል በሰው ኃጥያት መፍረድም በራስ ኃጥያት ከመፀፀት ጋር አብሮ አይሄድም"ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው

"የማያማትብ እጅ ቀኙም ግራውም አንድ ነው"አባ ፓስዮስ ዘደብረ አቶስ

"እግዚአብሔር ለኃጥያተኛ ሰው ያለው ፍቅር ፃድቅ ሰው ለእግዚአብሔር ካለው ፍቅር ይበልጣል"አባ አርሳኒ

"ዕለትን የሰጠህ እርሱ ለዕለት የሚበቃህንም ይሰጥሀል"ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

"ለኃጥያተኛ ክንፍህን ዘርጋለት።ኃጥያቱን ልትሸከምለት ባትችል እንኳን ሸፍንለት"ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ

"ይቅር ካላልክ ገነትም ይቅርብህ"አባ ኤፍሬም አረጋዊ

"እጅግ ምርጡ ፀሎት "ጌታ ሆይ አንተ ሁሉን ታውቃለህ የፈቀድከውን አድርግልኝ" ማለት ነው"ባህታዊ ቴዎፋን

"እንግዲህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳን ሆናችሁ የተወደዳችሁም ሆናችሁ÷ምሕረትን÷ርኅራሔን÷ቸርነትን
ትሕትናን÷የዋሕነትን÷ትዕግስትን ልበሱ" ቆላስይስ[፫÷፲፪]

___

@gitim_menfesawi
"ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደእብራውያን ሴቶች በዋዛ ፈዛዛ ያደግሽ አይደለሽም: በንፅህና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ::"
[አባ ሕርያቆስ ቅዳሴ ማርያም]

------
@gitim_menfesawi
+"እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ ትምህርት ነው ትሕትናም ክብረትን ትቀድማለች"ምሳ[፲፭÷፴፫]

ትሁት ስብእናን ገንዘብ ማድረግ እለት እለት መጋደል እና የእግዚአብሔርን ቸርነት መለመን ይፈልጋል።ከዛሬ ለነገ ለመሻል መጸጸት(ንስሀ) የቅዱሳንን የህይወት ታሪክ ማንበብ እና መጸለይ መልካም ነው።

"ከእኔ ተማሩ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና" ማቴ11፤ 29
ጌታ ሆይ ትህትናን አስተምረን::
____
@gitim_menfesawi
# ምክረ አበው#}}
አንድን በክፉ ምግባር የተያዘን ሰው ወደ መልካም ነገር
ልትመልሰው ብትወድድ መጀመርያ ሰላሙን እንዲያገኝ
አድርገው፡፡ በፍቅር ቃል ከፍ ከፍ አድርገው። እንዲህ ያለን
ሰው ከክፉ ስራው እንዲመለስ ለማድረግ ከዚህ የተሻለ ዘዴ
የለምና። ሰው በተግባር የሚያደርገው ፍቅር ሰዎችን
የመለወጥ ፍጹም ሀይል አለውና።
ቀጥለህ በፍቅር አንድ ሁለት ቃልን ንገረው፣ በቁጣ
አትንገረው። በእርሱ ላይ አንዳች የጠላትነት ስሜት አታሳይ።
ፍቅር ሰዎችን ለመለወጥ መንገዱን እርሱ ያውቅበታል። ብቻ
አንተ እድሉን ስጠው። የፍቅር ሰውም ሁን።
(መክስምያኖስ ባህታዊ ዘሶርያ )
----
@gitim_menfesawi
''እውነተኛ ጿሚ ራሱን ከክፉ ምግባራት የከለከለ፤ ከንቱ የሆኑ ንግግሮችን ከመናገር የተቆጠበ፣ ሐሰትን የማይናገር፣ ሐሜተኛ ያልሆነ፣ በማንም ላይ የማይፈርድ፣ሽንገላን የማይወድና እኒህንም ከመሰሉ ነገሮች ራሱን የጠበቀ ፣የማይቆጣ፣ የማይበሳጭ ፣ተንኮለኛ ያልሆነ ፣ ቂመኛ ያልሆነና፣ እነዚህን ከመሳሰሉ ክፋቶች ሁሉ የራቀ ሰው ነው፡፡

ሕሊናህ ኃጢአትን ከማሰብ ይጡም፡ አእምሮህም ኃጢአትን ከማስታወስ ይከልከል፡፡ ክፉን ከመመኘት ሁሉ ጡም፡፡ ዐይኖችህ ከንቱ የሆኑ ነገሮችን ከመመልከት፣ ጆሮህም ከንቱ ከሆኑ ዘፈኖችና ከሐሜተኞች ሹክሹክታዎች ጠብቅ፡፡ አንደበትህ ከሐሜት፣ በሌላው ላይ ከመፍረድ ፣ ከስድብ፣ ከውሸት ፣ከማታለል፣ከሽንገላ ንግግሮች እንዲሁም ከማይጠቅሙና አጸያፊ ከሆኑ ቃላት ይጡሙ፡፡ እጆችህም ሰውን ከመግደልና የሌላውን ንብረት ከመዝረፍ ይጡሙ፡፡ እግሮችህም ኃጢአትን ለመፈጸም ከመሄድ ይጡሙ፡፡ ከክፉ ተመለስ መልካምንም ፈጽም፡፡''
#ቅዱስ_ኤፍሬም

እኛስ እውነተኛ ጿሚ ልንባል ይገባን ይሆን?
-----
@gitim_menfesawi
ወጣት መነኩሴ ወደ አባ እንጦንዮስ መጣ። እየተማረረ እንዲህ አለ "አባቴ ሆይ ከመነኮስሁ ዓሥር ዓመታት አለፉኝ። ነገር ግን የዲያቢሎስን ፈተናውን መታገስ አቃተኝ ፣ እጅግ እየታገለኝ ነው" አባ እንጦንስም ለዚህ መነኩሴ የሚገባውን ምክርና ተግሣፅ ሠጥቶ አሰናበተው። መነኩሴው ከወጣ በኋላ ዲያቢሎስ ወደ አባ እንጦንስ ቀርቦ እንዲህ አለ። "በሕያው እግዚአብሔር እምላለሁ ፣ ይኼ ሰው መመንኮሱንም አላውቅም"

እኛ በዲያቢሎስ ተፈተንሁ ለማለት ራሱ ገና ነን ፣ ምክንያቱም የራሳችንን ድካምና ምኞት ገና ድል አልነሣንም።

"ምንም እንደ መቅደሱ መንጻት ባይነጻ የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ልቡን የሚያቀናውን ሁሉ ቸሩ እግዚአብሔር ይቅር ይበለው" (2 ዜና 30: 19)
------
@gitim_menfesawi
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት †††

††† በቤተ ክርስቲያን ክቡር ከሆኑ ሊቃነ መላእክት አንዱ የሆነው ቅዱስ ገብርኤል ብዙ የክብር ስሞች አሉት:: በተለይ ግን:-
*ሊቀ አርባብ:
*መጋቤ ሐዲስ:
*መልአከ ሰላም:
*ብሥራታዊ:
*ዖፍ አርያማዊ:
*ፍሡሐ ገጽ:
*ቤዛዊ መልአክ:
*ዘአልቦ ሙስና . . . እየተባለ ይጠራል::

በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን ስሙ በብዛት ተጠቅሷል:: ስለ ረዳትነቱና አማላጅነቱም ቤተ ክርስቲያን በስሙ ታቦት ቀርጻ: መቅደስ አንጻ በሥርዓት ክብሩን ትገልጻለች::

ከእነዚህም አንዱ ሠለስቱ ደቂቅን እንዳዳነ የሚታሰብበት አንዱ በዓሉ ዛሬ ነው::
"ለዝንቱ ዜናዊ መልአከ ኃይል::
በዛቲ ዕለት ከመ ይትገበር በዓል::
መምሕራን አዘዙ ወሠርዑ በቃል::" እንዲል:: (አርኬ)

ንጉሡ ከምርኮ ወጣቶች ለቤተ መንግስት ሲመርጥ ሦስቱ ቅዱሳንና ዳንኤል ተመርጠው የምቾት ሕይወት ተዘጋጅቶላቸው ነበር:: ነገር ግን በምግብና በአምልኮ ከአሕዛብ ጋር መተባበርን አልፈለጉምና ምርጫቸው ጾምና ጸሎት ከቆሎ ጋር ሆነ::

ምንም እንኳ በቤተ መንግስት ውስጥ ቢኖሩ: ምንም የነገሥታት ልጆች ቢሆኑ ለእነርሱ ከእግዚአብሔር ፍቅር የተሻለ አልነበረምና በጥሬ ቆሎ ተወስነው ኖሩ::

አምላካቸው ከሃሊ ነውና በውበትም ሆነ በጥበብ በባቢሎን ምድር ከነርሱ የሚደርስ አልተገኘም:: ንጉሡም በባቢሎንና በአውራጃዋ ላይ ሾማቸው:: ስማቸውንም በአማልክቱ ስም ሲድራቅ: ሚሳቅና አብደናጐ አላቸው::

ከነገር ሁሉ በኋላ አሕዛብ ቀንተውባቸዋልና የክፋት አዋጅን አሳወጁ:: ናቡከደነጾር 60 ክንድ ቁመት ያለውን የወርቅ ምስል አቁሞ ስገዱ ቢላቸው አይሆንም በማለታቸው ተቃጥለው እንዲሞቱ እሳት ተፈረደባቸው:: ነበልባሉ ከጉድጓዱ ወደ ላይ 49 ክንድ ቢነድም ቅንጣት ያህል ፍርሃት አልጎበኛቸውም::

ወደ እሳቱም ሲጥሏቸው መልዐከ አድኅኖ ቅዱስ ገብርኤል ደርሶ አዳናቸው:: ከሆነው ነገር የተነሳ አሕዛብ አፈሩ:: ናቡከደነጾር ግን ከዙፋኑ ተነስቶ የቅዱሳኑን አምላክ እግዚአብሔርን ባረከ::

ቅዱሳኑን ያዳነ ቅዱስ መልአክ እኛንም ያድነን ዘንድ እንደ አባቶቻችን
"አድኅነኒ ዘአድኃንኮሙ በአክናፊከ ምንትው::
አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ሠለስቱ እደው::" እያልን እንለምነው:: (መልክዐ ገብርኤል)
------
@gitim_menfesawi
++የማያቋርጠው የእመቤታችን ትሕትና ++
እመቤታችን በቃናው ሰርግ ቤት የተገኘችበት ምክንያት የገሊላ አውራጃ ሰው በመሆንዋ ነው፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ወደ እርስዋ የተላከውም
‹ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ› መሆኑ ይታወሳል፡፡ (ሉቃ. ፩፥፳፮) እርስዋም
የሀገር ሰው በመሆንዋና በደግነትዋ በዚህ ሰርግ ቤት ተገኝታለች፡፡ ወደ ሰርግ ቤት በመምጣትዋ የምናስተውለው ትልቅ ቁምነገር የእመቤታችንን ትሕትና ነው። እመቤታችን ከፍጥረት ሁሉ ተለይታ ፈጣሪዋን ለመውለድ የተመረጠችበት አንደኛ ዋነኛው ምክንያት ትሕትናዋ ነው፡፡

‹‹ወደ ትሑትና መንፈሱም ወደተሰበረ ሰው እመለከታለሁ›› በማለት የተናገረው ልዑል እግዚአብሔር እመቤታችንን ከሌሎች በላይ ሆና ያገኘበት ዋነኛው ምክንያት ትሕትናዋ ነበር፡፡ እርስዋም ስትጸልይ ‹‹የባርያዪቱን መዋረድ አይቷልና›› ብላ ከእንስተ ዓለም ለይቶ የመረጣት አምላክ በእርስዋ ላይ ምን እንዳየ ነግራናለች፡፡ (ኢሳ. ፶፯፥፲፭ ፤ ሉቃ. ፩፥፵፰) ቅዱስ ያዕቆብ ስሩግም የእመቤታችንን ትሕትና ከሌሎች እንደ አብርሃም ፣ እንደ ሙሴ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ያለ ትሑታን አበው ጋር ካስተያየ በኋላ ‹‹ነገር ግን በምድር
ላይ እንደ ማርያም ራሱን ዝቅ ያደረገ ሰው የለም ፤ በዚህም ምክንያት እንደ እርስዋ የከበረ ማንም አለመኖሩ በግልጥ የሚታይ ነገር ነው›› ብሏል፡፡

(On The Mother of God ; Homily 1
St. Jacob of Serug)
እመቤታችን የአምላክ እናት ሆና ፈጽሞ ያልተለወጠና የማያቋርጥ ትሕትና ነበራት፡፡ ከሰው ልጆች ሁሉ እንደ እመቤታችን ያለ ትሕትና ያለውም የለም፡፡ ከፍጥረታት ሁሉ በላይ የሚያደርጋትን አምላክን የመውለድን ክብር መሸከም የቻለችበት ታላቅ ትሕትና ነበራት፡፡ ትዕቢት ብዙ ፍጹማንን ሳይቀር የጣለ እስከ ሕይወት ፍጻሜ ድረስ የማይለቅ ፈተና ነው፡፡
ወደ ሰማይ በቅድስና መሰላል የወጡ ብዙ ቅዱሳን ጥቂት ሲቀራቸው የወደቁት በትዕቢት ነው፡፡ ክብሩና ጸጋው ሲጨምር ጠባዩ የማይለወጥ ሰው
የለም፡፡ አንድ አባት እንዲያውም ‹ጸጋንና ክብርን አትሥጠኝ ፤ ጸጋና ክብርን ከሠጠኸኝ ደግሞ መሸከም የምችልበት ትሕትና ሥጠኝ› ብሎ እስከመለመን ደርሷል፡፡

እመቤታችን ግን ማንም ያልደረሰበትና ሊደርስበትም የማይቻለውን የእናትነት ክብርን ይዛ ፣ በመላእክት አንደበት ተመስግና ለቅጽበት እንኳን
አልተመካችም፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ‹በትሕትና የተናገርሽ ተራራ ሆይ› ብሎ ያመሰገናት ይህች
ድንግል እንደ ተራራ ከፍ ያለች ስትሆን ራስዋን እንደ ሸለቆ ዝቅ አድርጋ‹‹እንዲህ ያለ የምስጋና እጅ መንሻ እንደምን ይደረግልኛል?›› ብላ በልብዋ አሰበች፡፡ በብዙህ የእናታችን ትሕትና እጅግ እንደነቃለን ፤ ‹ድንግል ሆይ እንዲህ ያለ የምስጋና እጅ
መንሻ እንደምን አይደረግልሽም? የተመረጥሽው የሰማይና ምድርን ፈጣሪ ልትወልጂ አይደለም ወይ? እሳተ መለኮትን ተሸክመሽ ፣ ሰማይና ምድር የማይችሉትን ችለሽ እንዲህ ያለ የምስጋና እጅ መንሻ እንደምን አይደረግልሽም?› እያልንም እናመሰግናታለን፡፡

አምላክን ከፀነሰችበት ሰዓት ጀምሮ እመቤታችን ከፍጥረት ሁሉ በላይ የሚያደርጋትን ክብር ተጎናጽፋ እያለ ለቅጽበት አልታበየችም፡፡ በሦስት መንገድ ማለትም በሃሳብዋም ፣ በንግግርዋም ፣ በሥራዋም ትሕትናን አሳይታናለች፡ ሰማያዊ መልዐክ አደግድጎ እያመሰገናት ‹እንዲህ ያለውን የምስጋና እጅ
መንሻ እንደምን ይደረግልኛል?› ብላ በልብዋ በማሰብ በሃሳብዋ ትሑት እንደሆነች አሳይታናለች፡፡ በንግግርዋ ደግሞ ከመጽነስዋ በፊትም ከጸነሰች
በኋላም ራስዋን ‹እነሆኝ የጌታ ባሪያ› ‹የባሪያዪቱን መዋረድ አይቶአልና› በማለት በትሕትና ጠርታለች፡፡ ቅዱስ ያሬድ ‹እንዖ አመቱ እሞ ረሰያ› እንዲል እግዚአብሔር ባሪያው ስትሆን እናቱ አደረጋት ፤ እርስዋ ደግሞ እናቱ ስትሆን ራስዋን
ባሪያ አደረገች፡፡

በተግባር ደግሞ ትሕትናዋን ያሳየችን ከመልዐኩ ብሥራት በኋላ ባደረገችው ጉዞ ነው፡፡ እንደጸነሰች በእመቤት ደንብ ልቀመጥ ሳትል ወደ ተራራማው ወደ ኤፍሬም ሀገር ኤልሳቤጥን ለመጠየቅ ተፋጥናለች፡፡ የአምላክ እናት ሆና እያለ የነቢዩን እናት ኤልሳቤጥን ተሳልማለች፡፡ በስተርጅና የጸነሰችውን ኤልሳቤጥን ስትንከባከብ ሦስት ወራት ቆይታለች፡፡ (ሉቃ.፩፥፶፮) አሁን ደግሞ በታላቅ ትሕትናዋ በሰርግ ቤት አስቀድማ ተገኘች፡፡መገኘትዋ ብቻ ሳይሆን ሰርግ እንደተጠራ እንግዳ በክብር ወንበር ተቀምጣ
መደሰትን አልመረጠችም፡፡ የሰርግ ቤቱ ወይን ጠጅ ማለቅ ከደጋሾቹ ቀድሞ ያስጨነቀው እርስዋን ነበር፡፡ በማያቆም ትሕትናዋ የምትደነቀው እመቤታችን በቃና ሰርግ ቤትም ውሎዋ ከክብር እንግዶች ጋር ሳይሆን ከአገልጋዮቹ ጋር ነበረ።

(ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)
/ከቃናዘገሊላ መጽሐፍላይ የተወሰደ/
------
@gitim_menfesawi
💛ጌታችን ስለተወለደባት ምሽት ቅዱስ ኤፍሬም አንዲህ አለ....

💛‹‹ይህች ምሽት ንጹሕ የሆነውና እኛን ሊያነጻን የመጣው (አምላክ) የተገለጠባት ንጽሕት ምሽት ናት፡፡

💛ጆሮአችን ንጹሕ ይሁን ፤ ዓይኖቻችንም ወደ ንጹሕ ነገር ይመልከቱ ፤ የልባችን ስሜት ቅዱስ ይሁን! ንግግራችንም አክብሮትን ይሞላ!

💛ይህች ምሽት የዕርቅ ምሽት ናት ፤ ስለዚህ ማንም ሰው ወንድሙን ተቆጥቶ እንዳያስቀይም!

💛ይህች ምሽት ለዓለም ሁሉ ሰላምን ያስገኘች ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው አይሸበርባት፡፡
ይህች ምሽት የደግነት ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው ክፉ አይሁን!

💛ይህች ምሽት የትሕትና ምሽት ናትና ማንም ሰው
እንዳይታበይባት!
ይህች ምሽት የደስታችን ቀን ስለሆነች የበደሉንን
አንበቀልባት!

💛የበጎ ፈቃድ ቀን ናትና የጭካኔ ቀን አናድርጋት!
የጸጥታ ቀን ናትና በቁጣ የምንነድባት ቀን አናድርጋት!

💛ዛሬ እግዚአብሔር ወደ ኃጢአተኞች የመጣበት ቀን ነው ፤ ስለዚህ ጻድቅ ሰው በኃጢአተኞች ላይ አይኩራባቸው!

💛ዛሬ እጅግ ባለጠጋ የሆነው አምላክ ስለ እኛ ደሃ የሆነበት ቀን ነው፤ ስለዚህ ሀብታም ሰው ድሆችን ወደ ገበታው ይጥራቸው፡፡

💛ዛሬ ያልጠየቅነውን ሥጦታ የተቀበልንበት ዕለት ነው፡፡ ስለዚህ እጆቻቸውን ዘርግተው እየጮኹ ለሚለምኑን ሰዎች የእርዳታ እጃችንን እንዘርጋ!

💛የዛሬዋ ዕለት ለጸሎቶቻችን የሰማያትን በር ከፍታልናለች ፤ እኛም ይቅርታን ለሚጠይቁን ሰዎች በራችንን እንክፈት!

💛ዛሬ አምላክ የሰውነትን ማኅተም በራሱ ላይ አተመ ፤ ሰውም አምላክነትን ማኅተም ተጎናጸፈ!››

#ትርጉም: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ💜

-------
@gitim_menfesawi
"ለዘተወልደ እምድንግል ምንተ ንብሎ ናስተማስሎ አርዌ ገዳምኑ አንበሳ ወሚመ ከራድዮን ዖፍ ጸዐዳ ንጉሠ ይሁዳ እምዘርዐ ዳዊት ዘመጽአ።"
ድጓ

ከራድዮን የሚባል ፀዐዳ ዖፍ አለ ይኸውም ከቤተ መንግስት ወስደው ያኖሩታል። ሰው ሲታመም ወስደው ያቀርቡታል። ያ ሰው የሚሞት የሆነ እንደሆነ አያየውም ፊቱን ይመልስበታል የሚድን የሆነ እንደሆነ ግን ያየዋል ቀርቦም አፉን ከፍ አድርጐ እስትንፋሱን ይቀበለዋል። በእስትንፋሱ ምክንያት ደዌ ከሰውየው ወደሱ ይመለሳል። ታማሚው ይድናል ወፉ ይታመማል፣ነጭ የነበረው ይጠቁራል፣ብርድ ብርድ ይለዋል፣ዋዕይ ሙቀት ሲሻ ወደ አየር ይወጣል። ዋዕይ ሙቀቱ ሲሰማው ሲያይልበት ከባሕር ይገባል። ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በባሕር ኑሮ የቀደመ ጠጉሩን መልጦ አድሶ ይወጣል።
______________________
ከራድዮን የጌታ ምሳሌ
የታመመው ሰው የአዳም ምሳሌ
______________________

እንግዲህ ምን እንላለን ሥላሴ አስቀድመው የአዳምን መበደል ሞትም እንዲመጣበት ያውቃሉና ገና ዓለም ሲፈጠር እግዚአብሔር አንድያ ልጁን አሳልፎ ለመስጠት ዝግጁ እንደ ነበር የ ከራዲዮን ወፍ አፈጣጠር ምስክር ሆነን ።

✞እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዐል በሰላም አደረሰን✞
________
@gitim_menfesawi
"ዮሴፍ እግዚአብሔር ወልድን እንደ ህፃንነቱ አቀፈው፣እንደ አምላክነቱም አገለገለው፣ በመሐሪነቱም እጅግ ደስ አለው በፈራጅነቱ ግን እጅግ ፈራው።"

ቅዱስ ኤፍሬም
------------
@gitim_menfesawi
​​#የፍቅር_ሐዋርያ

ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን "የፍቅር ሐዋርያ" ትለዋለች:: ለ70 ዘመናት በቆየ ስብከቱ ስለ ፍቅር ብዙ አስተምሯል:: ፍቅርንም በተግባር አስተምሯል:: በየደቂቃውም "ደቂቅየ ተፋቀሩ በበይናቲክሙ - ልጆቼ ሆይ! እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ" እያለ ይሰብክ ነበር::

+በተለይ ደግሞ ከፈጣሪው ክርስቶስ ጋር የነበረው ፍቅር ፍጹም የተለየ ነበር:: በዚህ ምክንያትም ጌታ ባረገ ጊዜ እንዲህ ብሎታል:- "ለፍጡር ከሚገለጥ ምሥጢር ከአንተ የምሠውረው የለኝም::"

+ቀጥሎም በንጹሕ አፉ ስሞታል::
ሊቁ:-
"ሰላም ለአፉከ ለዮሐንስ ዘሰዓሞ::
ንጽሐ ኅሊናሁ ወልቡ ለዐይነ ፍትወትከ ሶበ አደሞ::" እንዳለው:: (መልክዐ ኢየሱስ)

ቅዱስ ዮሐንስ ከእመቤታችንም ጋር ልዩ ፍቅር ነበረው:: እርሷ እንደ ልጇ ስትወደው: እርሱ ደግሞ እንደ እናቱ ልቡ እስኪነድ ድረስ ይወዳት ነበር:: እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ ተከትሎ ያገኛት እመቤቱ ናትና::

+ከዚያ ሁሉ ጸጋና ማዕረግ የመድረሱ ምሥጢርም ድንግል ናት:: ለ15 ዓመታት በጽላሎተ ረድኤቷ (በረዳትነቷ ጥላ) ተደግፎ አብሯት ሲኖር ብዙ ተምሯል:: ከመላእክትም በላይ ከብሯል:: ከንጽሕናዋ በረከትም ተካፍሏል::

+ስለ ድንግል ማርያምም "ነገረ ማርያም" የሚል ድርሰት ሲኖረው "የሰኔ ጐልጐታንም" የጻፈው እርሱ ነው::

+ድንግል ባረፈችበት ቀንም ልክ እንደ ልጇ ክርስቶስ እርሷም ስማው: ታቅፋው ዐርፋለች:: ሊቃውንቱ ለዚህ አይደል በንጹሕ ከንፈሮቿ መሳምን (መባረክን) ሲሹ:-
"በከመ ሰዓምኪ ርዕሰ ዮሐንስ ቀዳሚ::
ስዒሞትየ ማርያም ድግሚ::" ያሉት::

+ታላቁ ቅዱስ ሐዋርያ ዕድሜው 90 ዓመት በሆነው ጊዜ በዚህች ዕለት ተሰውሯል:: ከዚያ አስቀድሞም የዓለምን ፍጻሜ ተመልክቷል:: ዛሬ ያለበትን የሚያውቅ ቸር ፈጣሪው ነው::

እናት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን ስትጠራው እንዲሕ ነው:-
ወንጌላዊ
ሐዋርያ
ሰማዕት ዘእንበለ ደም
አቡቀለምሲስ (ምሥጢራትን ያየ)
ታኦሎጐስ (ነባቤ መለኮት)
ወልደ ነጐድጉዋድ
ደቀ መለኮት ወምሥጢር
ፍቁረ እግዚእ
ርዕሰ ደናግል (የደናግል አለቃ)
ቁጹረ ገጽ
ዘረፈቀ ውስተ ሕጽኑ ለኢየሱስ (ከጌታ ጎን የሚቀመጥ)
ንስር ሠራሪ
ልዑለ ስብከት
ምድራዊው መልዐክ
ዓምደ ብርሐን
ሐዋርያ ትንቢት
ቀርነ ቤተ ክርስቲያን
ኮከበ ከዋክብት . . .

በቅዱስ ዮሐንስ ላይ ያደረ የእመቤታችን ድንግል ማርያምና የአንድ ልጇ ፍቅር በእኛም ላይ ይደር::

ቅዱስ ዮሐንስን የወደደ ጌታ በፍቅሩ ይጠግነን:: ከእናቱ ፍቅር አድርሶ በሐዋርያው በረከት ያስጊጠን::

#ጥር 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ ሐዋርያ
(ፍቁረ እግዚእ)
2.አባ ናርዶስ ጻድቅ (ዘደብረ ቢዘን)
3.ቅዱስ ጊዮርጊስ
4.ቅዱስ ማርቴና

#ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ
2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት)

+"+ በጌታ ኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ : የእናቱም እህት : የቀለዮዻም ሚስት ማርያም : መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር:: ጌታ ኢየሱስም እናቱን : ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን 'አንቺ ሆይ! እነሆ ልጅሽ' አላት:: ከዚህ በሁዋላ ደቀ መዝሙሩን 'እናትህ እነሁዋት' አለው:: ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት:: +"+ (ዮሐ. 19:25)

------------
@gitim_menfesawi
ከአባቶች አንደበት 🙏🙏🙏

"ጸሎት የማያፈቅር ሰው ብታይ ምንም ዓይነት በጎ ነገር በውስጡ እንደሌለ ትረዳለኽ - ወደ እግዚአብሔር የማይጸልይ ከኾነ በመንፈሳዊነቱ ሞቷል ሕይወትም የለውም"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

"ጸሎት ችላ የሚል ሰው እንዲኹም ለንስሐ የሚያበቃ ሌላ በር አለ ብሎ የሚያስብ በዲያቢሎስ ተሸንግሏል"
ማር ይስሐቅ

"ጸሎት አእምሮን ወደ እግዚአብሔር ማቅረብ ነው"
ማር ይስሐቅ"

ሙሽራውን ሰውቶ ለሙሽራይይቱ የሚመግባት ይህ እንደምን ያለ ነገር ነው? መላዕክት ሊነኩት የማይቻላቸውን ምድራዊና አፈር ሲሆን በእጆቹ ዳሶ ፈትቶ ሙሽሪትን በስብከቱ ጠርቶ ሙሽራውን የሚመግባት ይህ እንደምን ያለ ነው? ለእዚህ መደነቅ ይገባል፡፡"
...#አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ                    
  -------------
@gitim_menfesawi
ገሃድ ምንድን ነው?

ገሃድ መገለጥ መታየት ነው፡፡ በጥምቀት መገለጥ መባሉ ሰው የሆነው አምላክ በዓለም ሲኖር እስከ 30 ዓመት እድሜው ድረስ ሰዎችን ለማዳን የመጣ መሲህ ሰው የሆነበት፣ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ እሱ መሆኑን ሳያውቁ ከኖሩ በኃላ በ 30 ዓመት እድሜው በባሕረ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ እጅ ሲጠመቅ አብ በደመና ሆኖ ‹‹የምወደው ልጄ ይህ ነው›› በማለቱ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል በራሱ ላይ ሲያርፍ በመታየቱ ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ይሰቀላል ይሞታል ይነሳል ብለው የተናገሩለት መሲሕ እርሱ መሆኑ ተገልጦአልና፡ አንድም ሦስቱ አካላት በአንድ ጊዜ ታይተዋልና ምስጢረ ሥላሴ የተገለጠለት በመሆኑ ገሃድ ይባላል፡፡ (ማቴ 3፡13-17)
ይህን በማሰብ የምንጾመው ጾም “የገሃድ ጾም” ይባላል፡፡ ቀኑም በዓለ ጥምቀት ከመዋሉ አንድ ቀን ቀድሞ ማለትም ጥር 10 ቀን ለ 11 አጥቢያ ነው፡፡ስለዚህ ጥር 10 ቀን ከ ሰባቱ አጽዋማት አንዱ የሆነው የገሃድ ጾም ነው ማለት ነው!
------------
@gitim_menfesawi
HTML Embed Code:
2024/05/01 01:55:50
Back to Top