ታስበላብሃለች
አንድ እምነት የነበረው እረኛ ነበረ ይባላል፡፡ ምሳ ለመብላት ሲፈልግ ያሰማራቸውን በጎች ለቅዱሳን፣ ለመላእክት አደራ ሰጥቶ ይሔዳል፡፡
"ቅዱስ ገብርኤል ሆይ! እነዚህን በጎቼ ከተኩላ ጠብቅልኝ" ብሎት ይሔዳል፡፡ እንደ እምነቱም በጎቹ ተጠብቀዉለት ያገኛቸዋል፡፡ ሌላ ቀን ደግሞ "ቅዱስ ሚካኤል ሆይ! አንተ ጠብቅልኝ" ይሏል፡፡ እንዲህ በቅዱሳን እያስጠበቀ ምሳውን በልቶ ይመጣል፡፡
አንድ ቀን፦ "እመበቴ ሆይ! ዛሬ አንቺ ጠብቂልኝ" ብሎ ወደ ቤቱ ይሔዳል፡፡ አባቱ አገኙትና፦ "ዛሬ ለማን አስጠብቀህ መጣህ?" አሉት፡፡ "ለእመቤታችን አስጠብቄ መጣሁ" አላቸው፡፡ እርሳቸውም፦ "አዬ ልጄ! እርሷ'ማ ታስበላብሃለች" አሉት፡፡ "ለምን? ቅዱሳን፣ ጻድቃን፣ መላእክት የጠበቁትን እርሷ አትጠብቅምን?" ይላቸዋል፡፡ "አይ ልጄ! የተጠማን ውሻ በወርቅ ጫማዋ ያጠጣች፡ የተራበ አውሬ መጥቶ ቢበላ ትከለክለዋለችን? ታስበላብሃለች" ሲሉት "እውነትም" ብሎ ወደ መንጎቹ ሮጠ ይባላል፡፡
ርህርህተ ሕሊና ሆይ! ዘወትር በምልጃሽ በቃል ኪዳንሽ ጠብቂን፡፡ አሜን!!!
(በመምህር Samuel Ayalneh)
_____________
@gitim_menfesawi
>>Click here to continue<<