TG Telegram Group Link
Channel: የፊልም ቋንቋ አካዳሚ / Film Language Academy👌
Back to Bottom
F.L.003- Producing/ፕሮዲውሲንግ#Topic 01*
((መጨረሺያ/End))
※የፊልም/ቴሌቪዥን ፕሮዲውሲንግ/ማምረት
መሰረታዊያን! /Basics of Film/Tv
Producing※

በፊልም/ቴሌቪዥን ፕሮዳክሽኖች የማምረት ስራ ሂደት ውስጥ አንድ ፕሮዲውሰር/ አምራች በእውነቱ ምን ምንድነው የሚሰራው? /What does a producer actually do?

አንድ አምራች/ፕሮዲውሰር የፊልም እና የቴሌቪዥን ፕሮዳክሽኖች የማምረት ስራ ላይ በቅድሚያ ስለስክሪፕት፣ ስለዳይሬክቲንግ፣ ስለ ቀረፃ እና ኤዲቲንግን ጨምሮ የሁሉንም የፊልም/ቴሌቪዥን ስራዎች የፈጠራ ሂደቶችን ሰፊ በሆነ የዕውቀት ደረጃ ማወቅ እና ታሪኮች እንዴት እንደሚተረኩ ማወቅ አለባቸው፣ ስለዚህ እነዚህን ወሳኝ የማምረት ሂደቶችን በደንብ ለማሳካት የሚረዱ የፈጠራና የአመራር ውሳኔዎችን የመወሰን እና የማፅደቅ ብቃቱም ሊኖራቸው ይገባል፡፡


አንድ ፕሮዲውሰር ስኬታማ ፊልም መስራት የሚችለው በትንሹ እነዚህ መሰረታዊ ብቃቶችን/Skills/ ሲያዳብር ነው:

ስለፊልም እና ቴሌቪዥን ፕሮዳክሽኖች በቂ እውቀት ሲኖረው
ስለበጀት አያያዝ አወጣጥ እና የፊልም ቢዝነስ እውቀቱ ሲኖረው
ለአከፋፋዮች እና ለህዝብ ማሳያዎች እና ለገበያ ማቅረብ የመቻል ብቃቱ ሲኖረው
በፕሮጀክቱ ውስጥ ከሁሉም ሙያተኞች ጋር በደንብ የማነሳሳት እና የመግባባት ብቃቱ ኖሮት ሲሰራ
ውሳኔዎችን እና ሀላፊነቶችን በግንባር ቀደምትነት የመውሰድ ብቃት ሲኖረው፣
ጥሩ የስራ ሁኔታ የመፍጠር ብቃት ሲኖረው እና
ህጋዊ የስራ ደንቦችን የማክበር ተነሳሽነት እና እውቀቱ ሲኖረው ሲሆን ዘርዘር ባለ መልኩ ደግሞ ከስር ተመልከቱ;
★ፊልም እና የቴሌቪዥን ፕሮዳክሽኖች እውቀት/Film and TV production awareness:

የፊልም ወይም የቴሌቪዥን ፕሮዳክሽን ፕሮዲውሰር ጠለቅ ያለ የፊልም ስራ እና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች የፈጠራ ስራ ሂደት እና እንዴት እንደሚሰሩ ማወቅ አለበት በተለይም ስለስክሪፕት አፃፃፍ፣ ስለዳይሬክቲንግ እና ስለኤዲቲንግ ማወቅ ግድ ይላቸዋል። (የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው በሚለው የኛ ሀገር ፊልም ፕሮዲውሰሮች ጥግ ቁጭ ብሎ ፊልሙ አልቆ በማሳየት እና ሱፍ አሳምሮ ምርቃት ላይ በመንጎማለል ከዛ በፍፁም ፊልማችን ሊያድግ አይችልም ይልቁኑም ወረቀት ገልበጥ አርጎ፣ ኢንተርኔት ፈተሽ አርጎ ስለሙያዉ በሚገባ ማወቅ እና ሙያው በሚፈልገው ልክ መስራት ያስፈልጋል።)

★ታሪክ ነገራ/Storytelling

ይህ ችሎታ ለአንድ ፕሮዲውሰር የሚያስፈልገው የተለያዩ የፈጠራ ነክ ጉዳዬች ላይ ቶሎ ውሳኔ መስጠት እንዲችል ከዳይሬክተሩ ጋር እንዲግባባ እና እንዲያግዘው በስተመጨረሺያም ከፍ ያለ የፈጠራ ውጤት ተሰርቶ ለመያዝም ጭምር ነው።

★የንግድ እውቀት/Commercial awareness:

አንድ ፕሮዲውሰር የፊልም ተመልካቾች፣ የማሳያ ስፍራ ወኪሎች/ ሲኒማዎች፣ቲቪ ጣቢያዎች፣ ዌብሳይቶች ሊሆኑ ይችላሉ/ እና የፊልም አከፋፋዮች የሚፈልጉትን አይነት ስኬታማ ፊልም ማምረት እንደሚችል የሚያውቅ መሆን አለበት።
★አደረጃጀት/Organisation:

አንድ ፕሮዲውሰር ከላይ በተዘረዘሩት የስራ ሂደቶች መሰረት የጠቅላላው ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት እና የክፍያ ጉዳዬችን በመደራደር እንዲሁም የፋይናንስ ክህሎቶችን በመጠቀም የፊልሙን የጊዜ ሰሌዳዎችን እና የፕሮዳክሽን/የምርት በጀትን ያዘጋጃሉ ፡፡

ፕሮዲሰሮች/አምራቾች ከጠቅላላው የፕሮዳክሽን/የምርት ቡድን እንዲሁም ከስርጭት እና ከግብይት ቡድኖች ጋር የመግባባት እና የመምራት ብቃት ሊኖራቸው ያስፈልጋል። በዚህም መሰረት ፕሮዲውሰሮች ለፊልም ስቱዲዮው የበላይ ተቆጣጣሪ ሥራ አስፈፃሚ አምራቾች/ለኤክስኪውቲቭ ፕሮዲውሰሮች ወይም ለኢንቨስተሮቹ/ ለገንዘብ ድጋፍ ሰጪዎች ወይም ደግሞ ለተከታታይ ፕሮዳክሽን አጠቃላይ መሪዎች (በቴሌቪዥን ድራማ) የስራውን ሂደት አስመልክቶ በየጊዜው በቂ መልስ ይሰጣሉ ወይም ሪፓርት ያደርጋሉ፡፡
የፕሮዲውሰሩ/አምራቹ ዋና ዋና ተግባራት ምን
ይመስላሉ?

የሚዳብር ፕሮጀክት/ስክሪፕት፣ ሃሳብ መፈለግ
/Finding & Developing Material/

አንድ ፕሮዲውሰር/አምራች ሁልጊዜ አዲስ ስክሪፕት ለማግኘት ፍለጋ ላይ ነው። እንዳንዴ ደግሞ/ይህ በውጪ ሀገር ፊልሞች እጅግ የተለመደ አሰራር ነው/ ራሳቸው የመጽሐፍ መብቶችን ይገዙና ፣ እና ለመፃፍ ደራሲ ይቅጠራሉ ወይም ደግሞ አንድ ጸሐፊ ቀደም ሲል ኦርጅናሉን ስክሪፕት ጨርሶ አናግሯቸው ወይ አይዲያውን ፒች አድርጎ/የስክሪፕት ፈጠራ ሃሳቡን በአጭሩ አቅርቦላቸው የፕሮዲውሰሩን/አምራቹን ትኩረት ወስዶ ይሆናልና ያንን ስክሪፕት ወደሚፈልጉት አይነት ፕሮጀክት ይለውጣሉ።

በጀት ማውጣት/Budgeting

አንድ ፕሮዲውሰር/አምራች ገንዘብ ፍለጋ/እደና ከመጀመሩ በፊት የፕሮዲውሲንግ አባላት ተሰባሰብው የበጀት እቅድ ያወጣሉ፡፡ ይህ ባለሀብቶች ጊዜያቸውን እና ገንዘባቸውን ለእነሱ ማድረግ ይችሉ እንደሆነ እንዲወስኑ ይረዳቸዋል ፡፡ የሚታይ አይነት እና በስርዓት የተሰራ የስራ ሂደት ካርታ/የስራ እቅድ በፕሮዲውሰሩ እና አቅሙ ባላቸው ባለሀብቶች መካከል መተማመንን ይፈጥራል ፡፡ እንዲሁም የትኛዎቹን የስራ ክፍሎች መቆረጥ እና የትኛው ጊዜ ላይ መስራት እንደማይችሉ ቀድሞ አውቆ በመግለጽ ተዋንያንን እና ሙያተኞችን በመቅጠር በኩል በትክክለኛው መንገድ ለመጓዝ በእጅጉ ይጠቅማል፡፡
ገንዘብ ማሰባሰብ/Fundraising

ፕሮዲውሰሩ/አምራቹ በእውነቱ ፊልሙን ለመስራት ገንዘብ የማግኘት ሃላፊነት አለበት ወይም ቢያንስ ቢያንስ ገንዘብ ለማግኘት የሚረዱ ሰዎችን ማግኘት ይኖርበታል! ይህ ታዲያ ብዙውን ጊዜ በፊልሙ ስራ ውስጥ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ አስፈፃሚ አምራቾች/ኤክስኪዊቲቭ ፕሮዲውሰሮች/ ሀሳቡን ለመሸጥ የፔክ ዴኮች/የፈጠራ ሀሳብ ማስረጂያ መድረክ/ የሚፈጥሩበት ቦታ ነው ፡፡

በሌላ አነጋገር አንድ ፕሮዲውሰር ጥሩ ታሪክ ስክሪፕት ፈልጎ ያገኝና አቅሙ ያላቸውን ለፊልሙ ፋይናስ ማድረግ የሚችሉ ኢንቨስተሮችን ወይም በፊልም ሙያ ንግድ ውስጥ ያሉ ኤክስኪዊቲ ቭ ፕሮዲሰሮችን የሚያገናኝበት እና ለፊልሙ ስራ በቂ ገንዘብ የሚያስብበት መድረክ ነው። ( ይህ አሰራር በኛ ሀገር ፊልም ስራ ውስጥ የተለመደ ብቻ ሳይሆን በአጭሩ የለም ማለት ይቻላል - ነገር ግን ቀደም ሲል ደጋግመን እንዳልነው ለሀገራችን የፊልም እድገት እጅግ ጠቃሚው እና አስፈላጊው የስራ ሂደት ነው።)

መርሐግብር ማስያዝ/Scheduling

ፕሮዲውሰሩ/አምራቹ በተለምዶ የፊልም ስራውን አጠቃላይ የጊዜ ሰሌዳውን ያወጣል/ያቅዳል ፡፡ እና ባላቸው በጀት ወሰን ላይ በመመርኮዝ  የቀረፃ ቀናት ይመድባሉ ፡፡ አንደኛው ነገር ለዚህ ነው በጀት ማውጣት በጣም አስፈላጊ የሚሆነው ፡፡ ያገኙትን በጀት በቅድሚያ አውቀው ካወጡ ፣ ከወዲሁ በግምት ፣ በስንት ቀናት ፊልሙን ቀርፀው መጨረስ እንደሚችሉ ያውቃሉ።

ፕሮዲውሰሩ/አምራቹ እንዲሁ በልዩና አስፈላጊ ችሎታዎችና ፍላጎቶች ላይ በመመርኮዝ የጊዜ ሰሌዳ ያወጣል እናም የቀረፃ ቦታዎችን ቀድሞ ይመለከታል። በአንድ የቀረፃ ቦታ ላይ በዛ ያሉ ትዕይንቶች ካሉ ፕሮዲውሰሩ/አምራቹ በተመሳሳይ ቀን እዛ ቦታ ላይ ያሉ ትዕይንቶችን አሰባስቦ ፕሮግራሞችን ያዘጋጃል ፡፡
በእርግጥ ሁሌ እንደዚህ አርጎ ላያወጣ ይችላል እንደ ትዕይንቶቹ፣ እንደ ሚያስፈልጋቸው ነገሮች አይነት የቀረፃ እቅዶችን ሊያወጣ ይችላል።

ታዲያ በአሁኑ ጊዜ ነገሮች ቀለል እያሉ በመሄዳቸው የቀረፃ ፕሮግራምን ለማውጣት የሚያግዙ የፕሮዳክሽን/የምርት አስተዳደር ሶፍትዌር አሉ። በእነዚህ ሶፍትዌሮች አማካኝነት ከስክሪፕት መፃፍ ጀምሮ እስከ የቀረፃ መርሐግብር ማውጣት መላውን የፕሮዳክሽን/ምርት ሂደት አመቻችተው ለማቀድ ይረዳሉ።

ተዋንያንን እና ሙያተኞችን መቅጠር/ Cast & Crew

ፕሮዲውሰሩ/አምራቹ ሁሉንም ሰው የመቅጠር ሃላፊነት አለበት ፡፡ አዎ ዳይሬክተሩ ጨምሮ ፡፡ ነገር ግን ፕሮዲውሰሩ/አምራቹ የዳይሬክተሩን አለቃ ነው ለማለት ይከብዳል ፡፡ ፕሮዲውሰሩ/አምራቹ ለፊልሙ ታሪክ ተስማሚ የሆነውን ያንን ዳይሬክተር አፈላልጎ የሚቀጥርበት ምክንያት ለራዕያቸው/ዕይታቸው ሲል ነው ምክንያቱም ያ ስክሪፕት ያለ ዳይሬክተር እይታ፣ ትርጎማ ፊልም መሆን ስለማይችል ነው እና ዳይሬክተሩ ከተቀጠረ በኋላ አምራቹ የዳይሬክተሩን ራዕይ ለመደገፍ የቻለውን ሁሉ ያደርጋል ማለት ነው፡፡
ስለዚህ ታዲያ ማን ነው የፊልሙን ስራ በኃላፊነት የሚመራው?

ደህና ፣ በእውነቱ አቻ ለአቻ አብረው ይሰራሉ ​​ማለቱ ይቀላል፡፡ (ነገር ግን በኢንዱስትሪው የውስጥ ለውስጥ ፓለቲክስ ግን በፊልም ስራ ላይ ዳይሬክተሩ እንደቦስ ሲታይ በቴሌቪዥን ፕሮዳክሽን ደግሞ በአንፃሩ ፈላጭ ቆራጩ ፕሮዲውሰሩ ይሆናል) ብዙውን ጊዜ ዳይሬክተሩ ረዳት ዳይሬክተሩን የመቅጠር ኃላፊነት አለበት ፡፡ ፕሮዲውሰሩና እና ዳይሬክተሩ ሲሰሩም አብረው ይሰራሉ ​​፡፡ በነገራችን ላይ የዳይሬክቲንግ ሙያን ቀጣይ ርዕሰጉዳይ አድርገነው በሰፊው እንመለሰበታለን፣ የፕሮዲውሰር እና የዳይሬክተሩን የስራ አንድነት እና ልዩነቶችንም ከዛ በኃላ እንመለስበታለን!

ከዚህ በኃላ እንግዲህ ፕሮዲውሰሩ የቅድመ-ምርት እና የምርት ሙያተኞች ከተቀጠረ በኋላ በሚገባ ማስተዳደር ይጀምራል፤ በቅድመ-ምርት ወቅት የቀረፃ ቦታዎችን እና ፈቃዶችን ማረጋገጥ፣ የቀረፃ ፕሮግራሞችን ማደል በዛ መሰረት ማስተዳደር፣ እንደ ተቀጣሪዎቹ ተዋንያን እና ሙያተኞች እስፈላጊ የሆኑ ኮንትራቶችን ማስፈፀምን የመሳሰሉትን ያካትታል በሚገባ ይሰራሉ።

በፊልሙ መደበኛ የቀረፃ ወቅት ፕሮዲውሰሩ/አምራቹ በአምራቹ/ከፕሮዳክሽን ቡድን ላይ ዋናው ሰው እሱ ነው ፡፡ ሁሉም ሥራውን እየሠራ መሆኑን በማረጋገጥ ከሁሉም የዲፓርትመንት/መምሪያ ኃላፊዎች ጋር በመግባባት ይሰራል ፡፡ በእርግጥ የተለያዩ አምራቾች የተለያዩ ነገሮችን ሊሰሩ ይችላሉ፣ እንደ ላይን ፕሮዲውሰር፣ ኮ ፕሮዲውሰር የመሳሰሉት ማለታችን ነው ፡፡ በመሬት ላይ ግን ማለት በሚታይ መልኩ ግን ፕሮዲውሰሮች/አምራቾች በተለምዶ የመስመር አምራቾች/line producer እንደማለት ናቸው እንግዲህ ላይን ፕሮዲውሰሩ ደግሞ ከሱ ስር ሆኖ ይሰራል ማለት ነው
ይህ ማለት በኛ ሀገር ፊልም ስራ ሂደት ፕሮዲውሰሩ እና ፕሮዳክሽን ማኔጀሩ ተናበው እንደሚሰሩት ማለት ይሆናል፡፡

በድህረ-ምርት/Post-production/ ወቅት
የማስተዳደር ስራ

በቀረፃ ወቅት ፕሮዲውሰሮች/አምራቾች ቀድመው ከኤዲተሮች/አርታኢዎች ጋር መገናኘት ይኖርባቸዋል ፡፡ ፕሮዳክሽኑ/ምርቱ ተቀርፆ ከመዘጋቱ በፊት ብዙውን ጊዜ የተቀረፁ ፉቴጆችን ወደ ኤዲተሩ ይልካሉ ፡፡ አንዴ ፕሮዳክሽኑ/ምርቱ ከተዘጋ በኃላ ፕሮዲውሰሩ/አምራቹ እንደ ዳይሬክተሩ ሁሉ ኤዲተሮቹንም ሆነ ዳይሬክተሮቹን በሚፈልጉት ሁሉ ይረዷቸዋል ፡፡ በተጨማሪም በዚህን የስራ ወቅት ፕሮዲውሰሩ ዳይሬክተሩን የቪኤፍኤክስ/Vfx -ቪዥዋል ኢፌክት ሙያተኞች በመቅጠር ወይም እንደ ሙዚቃ አቀናባሪ ወይም እንደ ቀለም ባለሙያ ያለ ማንኛውንም የፖስት ፕሮዳክሽን ሙያተኞችን እንደአስፈላጊነቱ በመቅጠር ያግዟቸዋል፡፡

አንዳንድ ጊዜ;
በትላልቅ ፕሮደሰክሽኖች/ምርቶች ላይ ፕሮዲውሰሩ/አምራቹ እንዲሁ በዳይሬክተሩ እና በስቱዲዮው መካከል መካከለኛ ወይም እንደአገናኝ ሰው ሆኖ ይሠራል ፡፡
ግብይት / ስርጭት (Markating/
      Distribution)

ፊልሙን ለገበያ ማቅረብ ከፕሮዲውሰሩ/ከአምራቹ ዋነኛ ሚናዎች መካከል አንዱ ነው ፡፡ እናም ወደዚህ የሚሄድ በጣም ትንሽ ነው ፡፡ በሲኒማ ቤቶች ማስገባት፣ ለቴሌቪዥን ጣቢያዎች መላክ፣ ፊልም ፌስቲቫሎች ውስጥ ማስግባት ወይም የወረቀተ ወራቀቶች ስራዎች መሰራታቸው እና የእይታ ና ስርጭት ግብረ ሀይሎች ማዳረስ የመሳሰሉትን ስራ ሁሉ በሚገባ ይሰራል፣ ያስተዳድራል።

መቼም በዚህ ሂደት በእውነቱ የፕሮዲውሰሩ/የአምራቹ ሥራ በጭራሽ የማያልቅ ሊመስል ይችላል አይደል?፡ ግን ምን ማድረግ ይቻላል እውነታው እንግዲህ ይህው ነው!

ከፊልም ስርጭት እና አቅራቦት/እይታ እንዲሁም የፕሮሞሽን(ፕሮሞቲንግ) ስራዎች ጋር የፕሮዲውሰሩን ተግባራት አያይዘን በሌላ ርዕስ እንመለስበታለን ለአሁኑ ግን እዚህ ጋር አበቃን።

Extra Sources/ተጨማሪ ግብዓቶች; Film spot, Masterclass,filmconnection,Backstage,student blinder, and Film language acadamy library.

#በላይጌታነህ#የፊልምቋንቋቲቪናፊልምአካዳሚ
F.L.003- Producing/ፕሮዲውሲንግ#Topic 02*  
                        ክፍል 1/Part 1

የፊልም ፕሮዳክሽን 7 የስራ ሂደት ደረጃዎች/The 7
Stages Of Film Production/

የፊልም ፕሮዳክሽን ሥራ ማለትም ስክሪፕትን ወደ ፊልም የመለወጥ ስራ ረጅምና ውስብስብ የስራ ሂደት ነው ፡፡ የፊልም ማምረት ብዙ የስራ ሂደቶች እና ስራዎችን እንዲሁም በተለያዩ የሂደቱ ደረጃዎች ውስጥ የሚሳተፉ ሰዎችን/ሙያተኞችንም ይፈልጋል።

እንግዲህ በዚህ ጽሑፍ ውስጥ የምንመለከተውም ይሄንኑ ሂደት ነው! በዋነኛመት ብዙዎቻችን እንደምንስማመበት አንድ የፊልም ምርት ስራ ሂደት በሦስት ደረጃዎች የመክፍል አዝማሚያ በዚህ ፅሁፍም እናሳያለን ይህውም ቅድመ-ምርት/Pre-production/፣ ምርት/ Production/ እና ድህረ-ምርት/Post-Production/ በሚለው የተለመደ የፊልም ዋና የስራ ሂደቶች ማለት ነው። እንደእውነቱ ግን የፊልም ምርት ስራ ሂደት 7 ደረጃዎች አሉት፤ ይህ እንግዲህ እኛ በምንስማማበት በዚህ ፅሁፍ እሳቤ መሰረት ነው ምክንያቱም ሌሎች በ9 ክፍሎች አንዳንዶች ደግሞ በ12 ክፍሎች ከፋፍለው የሚሰሩ ስላሉ ነው በሌላ በኩል ደግሞ በ5 ክፍሎችም በመክፈል የሚሰሩ አይታጡም ነገር ግን አሁን እኛ ለኛ ሀገር ፊልም ስራ ሂደት ይጠቅማል ብለን በምናስብበት በ7 ዋና የስራ ሂደት ክፍሎች በመክፈል እናሳያችሀኋለን፡፡ ወደዛ ከማለፋችን በፊት እስቲ ለማሳያ ያህል ሌሎች አከፋፈሎቸ ለምሳሌ ያህል እናሳያችሁ በስተመጨረሺያ በማነፃፃር ክፍተቶቹን መሙላት ለእናንተ እንተወዋለን
ባለ 3 የፊልም ስራ ሂደት/The 3 stage of film production/

1. ቅድመ-ምርት/Pre-production
2. ምርት/Production
3. ድህረ-ምርት/Post-production
ባለ 5 የፊልም ስራ ሂደት/ The 5 stage of film production/

1. ማዳበር/ማልማት(Development)
2. ቅድመ-ምርት/Pre-production
3. ምርት/Production
4. ድህረ-ምርት/Post-production
5. ስርጭት/እይታ(Distribution)
ባለ9ኙ የፊልም ስራ ሂደት/The 9 stage of film production

1. ሃሳብ ማግኘት/The Idea
2. ማዳበር/ Development
3. ማደራጀት/Packaging
4. በጀት ማሰባሰብ/ማረጋገጥ(Financing)
5. ቅድመ-ምርት/Pre-production
6. ምርት/ቀረፃ(Production/ The shoot)
7. ድህረ-ምርት/Post-production
8.ስርጭት/Distribution
9. እይታ/Screening
ባለ12ቱ የፊልም ስራ ሂደት ደረጃዎች/The 12 Stage of Film Production/

1. ሃሳብ ማግኘት/The Idea
2. ፋይናስ ማፈላለግ/Development finance
3. የፊልም ድርሰት ማዳበር/Script Development
4. ማደራጀት/Packaging
5. በጀት ማሰባሰብ/ማረጋገጥ(Financing)
6. ቅድመ-ምርት/Pre-production
7. ምርት/ቀረፃ(Production/ The shoot)
8. ድህረ-ምርት/Post-production
9. ሽያጭ/Sales
10.ግብይት/የሽያጭ ስራ(Markating)
11. ስርጭት/እይታ(Exeibition)
12. ሌሎች ክንውኖች/Other works
ከላይ ያሉት የስራ ሂደት ክፍፍሎች ለንፅፅር እና ሃሳባችሁን ለማዳበር የሚረዳ ሲሆን እኛ የመረጥነውን በለ7 ክፍል የስራ ሂደትን ደግሞ በጥቂቱ ዘርዘር እንመልከተው

7ቱ የፊልም ስራ ሂደት ደረጃዎች/The 7 Stage of Film Production/

1. ማዳበር/ማልማት(Development)
2. በጀት ማሰባሰብ/ማረጋገጥ(Financing)
3. ቅድመ-ምርት/Pre-production
4. ምርት/Production
5. ድህረ-ምርት/Post-production
6. ግብይት/የሽያጭ ስራ(Markating)
7. ስርጭት/እይታ(Distribution)

እያንዳንዱን ደረጃ በትክክለኛው ቅደም ተከተል መስራት የቀረፃ ቀናትን ቀላል ያደርግልናል እና ሁሉም ነገር ያለችግር መከናወኑን ያረጋግጣልናል። በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ስለእነዚህ ደረጃዎች እና በፊልም ምርት ውስጥ ዋና ሚናዎችን በተመለከተ ሁሉንም ዝርዝሮች እንነጋገራለን ፡፡ ወደ ውስጥ እንግባ!

ለመሆኑ ፊልም ማምረት ምንድነው?

ፊልም ማምረት ፊልም የሚሰራበት የስራ ሂደት ነው ፡፡ ስለ ፊልም ዝግጅት ስናወራ ከጅማሬ ፊልምን ለመስራት ታሪክን ከመፈለግ እስከ ፍፃሜው ለተመልካች እይታ እስከሚቀርብበት ስለአጠቃላዩ የፊልም ስራ የማምረት አጠቃላይ ሂደት ማውራት አለብን ማለት ነው፡፡ ብዙ ሰዎች የፊልም ማምረት ስክሪፕቱን መፃፍ ፣ የተወሰነ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እና ፊልም መቅረፅን መጀመር ብቻ ነው ብለው ያስባሉ ፡፡ ነገር ግን ፣ የፊልም ምርት ስራ ከዚህ የበለጠ ነው ፡፡ የፊልም ማምረት የገንዘብ ድጋፍን ፣ የፊልም ሰራተኞችን መቅጠር ፣ ቦታዎችን መፈለግ ፣ ግብይት እና ስርጭትን/እይታን ያካትታል ፡፡ የተሻለ ግንዛቤ እንዲሰጣችሁ ለማገዝ እስቲ ስለ እያንዳንዱ የስራ ደረጃ በጥቂቱ ዘርዘር አርገን እንነጋገር።
የፊልም ፕሮዳክሽን 7 የስራ ሂደት ደረጃዎች/The 7 Stages Of Film Production/

1. ማዳበር/ማልማት(Development)

ወደ የፊልም ስራን ማዳበር ደረጃ የሚወስዱን ብዛ ያሉና የተለያዩ መንገዶች አሉ ፡፡ ብዙን ጊዜ ግን ይህ የስራ ሂደት የሚጀምረው ቀደም ሲል በተጻፈ ስክሪፕት ላይ በመነሳት ወይም ደግሞ አስፈፃሚ አምራች/Excutive Producer/ ይዞ በሚነሳው ወደ ስክሪፕትነት የሚለወጥ የፊልም ሃሳብ ላይ በመነሳሳት ነው፤ እንደዚሁም አንድ ፊልምን ለመስራት የተነሳሳ ወይ መደበኛ ስራው የሆነ ፕሮዲውሰር/አምራች በተለያየ መንገድ ያለቀለት የፊልም ድርሰት በማፃፍ ወይም ሃሳቦችን በማፈላለግ መርጦ በመግዛት የሚጀመር ሊሆን ይችላል፡፡ ሌላው መንገድ ደግሞ በአንድ አይነት አላማ ላይ በመመርኮዝ የተፃፈ ወይም የተዘጋጀ ፕሮጀክት - አንድ የፊልም ፕሮዳክሽን ኩባንያ ወደፊልምነት እንዲለውጠው/ እንዲሠራው በሚጠይቅበት ጊዜ ነው ፡፡ በዚያ ጊዜ ታዲያ ፕሮጀክቱን የሚያስጀምረው/የተቀበለው ፕሮዲውሰሩ/አምራቹ ለስራው ሀላፊነት በመውሰድ ስክሪን ጸሐፊውን በመቅጠር በሀሳቡ ላይ መሥራት ይጀምራል ፡፡

የስራ ሂደቱ ከላይ ባነሳናቸው በየትኛውም መንገድ ይጀምር የእድገቱ ሂደት የፊልሙን አጠቃላይ እቅድ እና የስክሪፕት ሃሳብ ያካትታል ፡፡ ጸሐፊዎቹ ሥራቸውን በሚሠሩበት ጊዜ ፕሮዲውሰሩ/አምራቹ ደግሞ ከሽያጩ ሥራ ጀምሮ ገንዘብ የማሰባሰብ ወይም ሀሳቡን እንዲያወጣ የመጀመሪያ ጠቅለል ያለ ቅኝት ያደርጋል ፡፡ ስክሪፕቱ አንዴ ከፀደቀ በኋላ ዳይሬክተሩ ይቀጠርና ከፀሐፊው ጋር በመሆን የፊልም ስራውን ቅኝትን፣ ትረካውን፣ የፊልሙን ሃሳብ በመከለስ ለቀጣይ የስራ ሂደቶች ዝግጁ እንዲሆን ያደርገዋል ማለት ነው።
የማዳበር/Development የስራ ሂደት ደረጃ ፕሮጀክቱ የሚወለድበት ጊዜ ነው ማለት እንችላለን። በዚህ ክፍል እንግዲህ የፕሮጀክት ሀሳቡን መፍጠር ፣ መጻፍ ፣ ማደራጀት እና የእቅድ ማውጣት ደረጃ ነው። በዚህ የስራ ሂደት ውስጥ የሚከተሉት ተግባራቶች ይከናወናሉ;

የመጀመሪያ በጀት እቅድ ይሰራል
ዋና ተዋናይ ሊሆኑ የሚችሉ ተዋናዬች ይመረጣሉ/
ይታሰባሉ
ቁልፍ የፈጠራዎች ሙያተኞች ይመረጣሉ
ዋና የቀረፃ ሥፍራዎች በመዘዋወር ምልከታ
ይደረግባቸዋል
በርካታ የስክሪፕት ረቂቆች ሊጻፉ ይችላሉ
ፕሮጀክቱ ምን እንደሚሆን እና ምን ያህል ወጪ
እንደሚያስወጣ ለማሳየት ሁሉም መሠረት ነው።

አንድ ፕሮዲውሰር/አምራች ስለ አንድ ፕሮጀክት ካሰበ ወይም ጸሐፊው በአንድ ገጽ ላይ ቃላትን መጻፍ ከጀመረበት ቅጽበት ያ ፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ክፍል ይጀምራል። የማዳበር/Development ደረጃ ፕሮጀክቱን በይጀመር የአረንጓዴ ብርሃን ለማብራት ወይም ራሱን ችሎ በገንዘብ ተሟልቶ ወይንም ደግሞ ወደ ቅድመ-ምርት የስራ ደረጃ ለመግባት ወራት ወይም ዓመታትም ሊወስድበት ይችላል።

ለአንድ ፊልም አረንጓዴ ማብራት ማለት ስቱዲዮው ሀሳቡን አፅድቆ ለፕሮጀክቱ ፋይናንስ የሚያደርገው አካል ፋይናስ አድርጎ ወደ ምርት ይገባል ማለታችን ነው። በማዳበር እድገቱ ክፍል ላይ የተሰማሩት ሠራተኞች ታሪኩን እና ተጓዳኙን በጀት የሚሠሩ ጥቂት የፈጣሪዎች እና የሥራ አስፈፃሚዎች ቡድን በመሆኑ ከሌሎች ደረጃዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር በጣም አናሳ ናቸው። አንድ ፕሮጀክት ፋይናንስ ካገኘ በኋላ ፕሮጀክቱ እንዲጠናቀቅ በቀረፃ ቀናት እና የጊዜ ገደቦች ላይ ትኩረት በማድረግ ወደ ቅድመ-ምርት ደረጃው ይሄዳል ማለት ነው። (የፋይናስ እና የፕሪ ፕሮዳክሽን የስራ ሂደቶችን ዝርዝር ሂደቶች በሚቀጥሉት ክፍሎች ይመልከቱ)

ይቀጥላል …
F.L.003- Producing/ፕሮዲውሲንግ#Topic 02*  
                        ክፍል 2/Part 2
የፊልም ፕሮዳክሽን 7 የስራ ሂደት ደረጃዎች/The 7
Stages Of Film Production/

2. በጀትን ማሰባሰብ/ማጎልበት(Financing)

በጀትን የማጎልበት ስራ የፊልም ቅድመ-ዝግጅት ወሳኝ የስራ ደረጃ ነው ፡፡ ገንዘብ ማሰባሰብን ለመጀመር ፕሮዲውሰሩ/አምራቹ በበጀቱ ላይ መሥራት እና ለእያንዳንዱ የስራ ደረጃ ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያስፈልገው ቅድመ ትንበያ ማድረግ አለበት ፡፡ ምክንያቱም የእያንዳንዱ የሥራ ምድብ የበጀት ፍላጎት አጠቃላይ በጀቱ ላይ ለውጥ ያደርጋሉ ወይ የበጀቱን መጠን ይወሰናሉ ፡፡የፊልም ፕሮዲውሰሩ አንዴ የሚያስፈልገውን በጀት ካወቀ ከሙያተኞቹ ፣ ከበጀት አቅራቢዎቹ ፣ ከተዋንያን ፣ ከቀረፃ ስፍራ አመቻቺዎች እና ከድህረ-ምርት ሙያተኞች ጋር ወዘተ ተገቢውን ድርድር ማድረግ ይችላሉ ወይ ግምታዊ ዋጋዋችን ማስቀመጥ ይችላሉ፡፡

ፕሮዲውሰሮች/አምራቾች ከኢንቨስተሮች በመገናኘት፣ በተለያዩ ገንዘብ አገናኝ ኔትወርኮች እና በፋይናስ ማሰባሰቢያ ስብሰባዎች ላይ በመገኘት ፣ በክሬዲት ገንዘብ፣ ከአንዳንድ አትራፊ የፋይንስ ተቋማት እንዲሁም ከባንኮች በብድር ሊሆን ይችላል ፋይናንስን ለማግኘት ይሞክራሉ፡፡ (በኛ ሀገር ሲገለበጥ ደግሞ ፕሮዲውሰሮቹ ገንዘቡን የሚያገኙበትን አቅጣጫ ተከትለው ከዘመድ አዝማድ፣ ከጓደኛ ወይ ከቤተሰብ ወይንም የተለያየ ሽያጭ አርገውም ሊሆን ይችላል ገንዘቡን ወደአካውንታቸው በማስገባት ሴኪዊር ያረጋሉ – እንደእውነቱ ከሆነ ጥቂት ብር በመያዝ በጨበጣ የሚጀምሩ ስራዉን እያቆራረጡ የሚሰሩ እንዳሉ ሆነው ማለት ነው)
በዚህ መልኩ ፕሮዲውሰሩ ገንዘቡን ያሰባስባል፤ እንዲሁም በውጪው አለም ከተለመዱ የፋይናስ የመፈለግያ ዘዴዎች መካከል የሆነውን የፕሮጀክታቸውን ሀሳብ/የስክሪፕት እና አጠቃላይ የበጀት ፍላጎታቸውን አጠቃለው/ በተለያዩ የፊልም ነክ ፕሮግራሞች ላይ እንደ ፊልም ሽልማቶች፣ ፌስቲቫሎች፣ ምርቃቶች ላይ በመገኘት የፊልም ኢንቨስተሮችን፣ አስፈፃሚዎች/ኤክስኪዊቲቭ ፕሮዲውሰሮችና ስቱድዬችን በመገናኘት ለማማለል እና በጀታቸውን ሴኪዊር ለማረግ ይሞክራሉ። (መቼም ይህ አይነት አሰራር በሀገራችን የፊልም ስራ ውስጥም በአጭር ጊዜ እንደሚለመድ ተስፋ እናደርጋለን)

ምንም እንኳን የፊልም ስራ የበጀት አሰባሰብ እና የበጀት አሰራር ርዕሰጉዳይን በአንድ ወጥ ርዕሰ የምንመለስበት ቢሆንም ለጊዜው መታለፍ የሌለባቸውን ወሳኝ ነጥቦች እናንሳ

★የፊልምን በጀት መጠነ የሚወስኑ ነገሮች ምን ምንድናቸው?

የፊልሙ ዘውግ እና የታሪክ ሂደት/ስፋት(Gener & Story place & time)
የፊልሙ በጀት ከሚያንስባቸው እና ከሚበዛባቸው ምክንያቶች አንዱ ዘውጉ ወይ ስክሪፕቱ የሚዳስሰው የታሪክ ስፋት ነው። እንደ ጀብዳዊ/አድቬንቸር ወይም የጦርነት ፊልሞች ከፍተኛ በጀት እንደሚያወጡ በቀላሉ መገመት ይቻላል በሌላ በኩል ቀለል ያለ የኮሜዲ ወይንም የፍቅር ፊልም ሆኖም ታሪኩ የሚሄድበት ዘመን የታረክ ክዋኔ ስፋት ውስብስብነት በጀቱን በከፍተኛ ደረጃ ሊለጥጠው ይችላል፤ ስለዚህ ፕሮዲውሰሩ/አምራቹ ሀሳቡን/ስክሪፕቱን ከመምረጡ በፊት ይሄንን አይነት ፊልም ሊያሰራ የሚችል በጀት ማሰባሰብ ወይ ማግኘት እንደሚችል በቅድሚያ ማረጋገጥ አለበት።

የቀረፃ ስፍራ /Location/
የቀረፃ ስፍራ አንዱ የበጀትን መጠን የሚወስን ጉዳይ ሰሆን የቀረፃ ስፍራዎቹ አይገኜ መሆን፣ ብዛት፣ በድጋሜ የመገንባት ሁኔታ ወዘተ ሊሆን ይችላል።
HTML Embed Code:
2024/05/15 16:32:25
Back to Top