✔ገንዘብ ማሰባሰብ/Fundraising
ፕሮዲውሰሩ/አምራቹ በእውነቱ ፊልሙን ለመስራት ገንዘብ የማግኘት ሃላፊነት አለበት ወይም ቢያንስ ቢያንስ ገንዘብ ለማግኘት የሚረዱ ሰዎችን ማግኘት ይኖርበታል! ይህ ታዲያ ብዙውን ጊዜ በፊልሙ ስራ ውስጥ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ አስፈፃሚ አምራቾች/ኤክስኪዊቲቭ ፕሮዲውሰሮች/ ሀሳቡን ለመሸጥ የፔክ ዴኮች/የፈጠራ ሀሳብ ማስረጂያ መድረክ/ የሚፈጥሩበት ቦታ ነው ፡፡
በሌላ አነጋገር አንድ ፕሮዲውሰር ጥሩ ታሪክ ስክሪፕት ፈልጎ ያገኝና አቅሙ ያላቸውን ለፊልሙ ፋይናስ ማድረግ የሚችሉ ኢንቨስተሮችን ወይም በፊልም ሙያ ንግድ ውስጥ ያሉ ኤክስኪዊቲ ቭ ፕሮዲሰሮችን የሚያገናኝበት እና ለፊልሙ ስራ በቂ ገንዘብ የሚያስብበት መድረክ ነው። ( ይህ አሰራር በኛ ሀገር ፊልም ስራ ውስጥ የተለመደ ብቻ ሳይሆን በአጭሩ የለም ማለት ይቻላል - ነገር ግን ቀደም ሲል ደጋግመን እንዳልነው ለሀገራችን የፊልም እድገት እጅግ ጠቃሚው እና አስፈላጊው የስራ ሂደት ነው።)
✔መርሐግብር ማስያዝ/Scheduling
ፕሮዲውሰሩ/አምራቹ በተለምዶ የፊልም ስራውን አጠቃላይ የጊዜ ሰሌዳውን ያወጣል/ያቅዳል ፡፡ እና ባላቸው በጀት ወሰን ላይ በመመርኮዝ የቀረፃ ቀናት ይመድባሉ ፡፡ አንደኛው ነገር ለዚህ ነው በጀት ማውጣት በጣም አስፈላጊ የሚሆነው ፡፡ ያገኙትን በጀት በቅድሚያ አውቀው ካወጡ ፣ ከወዲሁ በግምት ፣ በስንት ቀናት ፊልሙን ቀርፀው መጨረስ እንደሚችሉ ያውቃሉ።
ፕሮዲውሰሩ/አምራቹ እንዲሁ በልዩና አስፈላጊ ችሎታዎችና ፍላጎቶች ላይ በመመርኮዝ የጊዜ ሰሌዳ ያወጣል እናም የቀረፃ ቦታዎችን ቀድሞ ይመለከታል። በአንድ የቀረፃ ቦታ ላይ በዛ ያሉ ትዕይንቶች ካሉ ፕሮዲውሰሩ/አምራቹ በተመሳሳይ ቀን እዛ ቦታ ላይ ያሉ ትዕይንቶችን አሰባስቦ ፕሮግራሞችን ያዘጋጃል ፡፡
>>Click here to continue<<