F.L.003- Producing/ፕሮዲውሲንግ#Topic 01*
((መጨረሺያ/End))
※የፊልም/ቴሌቪዥን ፕሮዲውሲንግ/ማምረት
መሰረታዊያን! /Basics of Film/Tv
Producing※
★
በፊልም/ቴሌቪዥን ፕሮዳክሽኖች የማምረት ስራ ሂደት ውስጥ አንድ ፕሮዲውሰር/ አምራች በእውነቱ ምን ምንድነው የሚሰራው? /What does a producer actually do?
አንድ አምራች/ፕሮዲውሰር የፊልም እና የቴሌቪዥን ፕሮዳክሽኖች የማምረት ስራ ላይ በቅድሚያ ስለስክሪፕት፣ ስለዳይሬክቲንግ፣ ስለ ቀረፃ እና ኤዲቲንግን ጨምሮ የሁሉንም የፊልም/ቴሌቪዥን ስራዎች የፈጠራ ሂደቶችን ሰፊ በሆነ የዕውቀት ደረጃ ማወቅ እና ታሪኮች እንዴት እንደሚተረኩ ማወቅ አለባቸው፣ ስለዚህ እነዚህን ወሳኝ የማምረት ሂደቶችን በደንብ ለማሳካት የሚረዱ የፈጠራና የአመራር ውሳኔዎችን የመወሰን እና የማፅደቅ ብቃቱም ሊኖራቸው ይገባል፡፡
★
አንድ ፕሮዲውሰር ስኬታማ ፊልም መስራት የሚችለው በትንሹ እነዚህ መሰረታዊ ብቃቶችን/Skills/ ሲያዳብር ነው:
✔ ስለፊልም እና ቴሌቪዥን ፕሮዳክሽኖች በቂ እውቀት ሲኖረው
✔ ስለበጀት አያያዝ አወጣጥ እና የፊልም ቢዝነስ እውቀቱ ሲኖረው
✔ ለአከፋፋዮች እና ለህዝብ ማሳያዎች እና ለገበያ ማቅረብ የመቻል ብቃቱ ሲኖረው
✔በፕሮጀክቱ ውስጥ ከሁሉም ሙያተኞች ጋር በደንብ የማነሳሳት እና የመግባባት ብቃቱ ኖሮት ሲሰራ
✔ውሳኔዎችን እና ሀላፊነቶችን በግንባር ቀደምትነት የመውሰድ ብቃት ሲኖረው፣
✔ጥሩ የስራ ሁኔታ የመፍጠር ብቃት ሲኖረው እና
✔ህጋዊ የስራ ደንቦችን የማክበር ተነሳሽነት እና እውቀቱ ሲኖረው ሲሆን ዘርዘር ባለ መልኩ ደግሞ ከስር ተመልከቱ;
>>Click here to continue<<