TG Telegram Group Link
Channel: P H O E N I X B A T C H 2 k 1 2
Back to Bottom
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
💥የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ቅሬታ

፨የተምሪዎችን ድምፅ በሚገባ ለዘገበው የሚድያ ጣቢያ በተማሪዎች ስም ምስጋናችንን እያቀረብን መንግስትም የተማሪዎችን ቅሬታ አስፈላጊውን ምላሽ እንዲሰጥ እንጠይቃለን።

ምንጭ፡ Nahoo TV 👇👇
@entranceexampreparetion
#Kesatyan_ASTU_AASTU

ለ አዳማ ና አዲስአበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለመወዳደር የተመዘገባችሁ በሙሉ

👉 ሚያዚያ 8 አርብ ከጧቱ 2:00 ፈተናው መሰጠት ይጀምራል።

👉 ለ መወዳደር የተመዘገቡ ሁሉም ተማሪዎች ስለ ፈተናው አሰጣጥ ገለፃ ወይም orientation ለማግኘት ነገ ሐሙስ 07/08/13 ከ ሰአት በሗላ በየራሳቸው የምዝገባ ማዕከል መገኘት አለባቸው።

👉 ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ጣቢያዎቻቸው ሲሔዱ Admission card እና የ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤታቸውን (Entrance result ) ይዘው መሔድ ይጠበቅባቸዋል።

👉 የ Entrance ውጤታችሁን copy አድርጋችሁ መያዝ ትችላላችሁ።

@kesatyan
@kesatyan
#Ethiopia : በ12 ኛ ክፍል ፍተና ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች ለቅሬታችን መልስ ይሰጠን በማለት በአሁን ሰአት ትምህርት ሚኒስትር በር ላይ ሰላማዊ ሰልፍ በማደግ ላይ ናቸው:: የተማሪዎቹ ሰልፍ ከዛሬው ጋር ለሁለተኛ ግዜ መሆኑ ነው::

Share

@gradee12
@gradee12
Have you checked out Ask Anything Ethiopia yet? It's Ethiopia's first question and answer platform, where you can get answers to your biggest questions from thousands of people! You can join using the link below:

https://hottg.com/ask_anything_ethiopia_bot?start=i394921036
🛑ማነው ሀገሩን ሚወድ

እኔ ሀገሬን እወዳለው ሚል ሰው በሙሉ ከኛ ከ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ጎን መቆሞ አለበት❗️


⚠️ ሀገርን ከዝርክረክ አመራሮች የማዳን ዘመቻ




✳️ ውድ ቅሬታችን ይሰማ ግሩፕ አባላቶች በሙሉ እና ሌሎችም ጉዳዩ እኔንም ይመለከተኛል ምትሉ ተማሪዎች
እንደምታውቁት ሀሙስ ለት ሰልፍ በመውጣት ቅሬታችንን ለሚመለከተው አካል ለትምህርት ሚኒስቴር አሰምተን ነበር በተጨማራም ተወካዮቻችን ገብተው በደንብ ቅሬታችንን ገልፀውላቸው ነበር በመቀጠል የነሱን ቅሬታ ሰምቶ ትምህርት ሚኒስቴር ሰልፍ የወጣውን ተማሪ ለማነጋገር ወደ ግቢ አስገብተው አነጋግረውን ጥያቄ ጠይቀናቸው እንደነበር ይታወቃል ከጥያቄዎቹ ውስጥም ፈተናው ተሰርቋል የሚል ነበር እነሱም ፈተናው ተሰርቋል ያላቹበትን data analaysis ሰርታቹ አምጡ እስከ ቅዳሜ አልያም ሰኞ በተወካዮቻቹ አማካኝነት መልስ እንሰጣለን ብለው እዛ የነበረውን ተማሪ ወደ ቤቱ እንዲሄድ ማድረጋቸው ይታወቃል። ከዛ ድረስ ያለው ቀን ሰኞ ደረሰ ለሰኞ የተቀጠሩት ተወካዮቻችንም መልሱን ለመስማት ትምህርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ደረሱ ውስጥም በመግባት ሲያነጋግሩ በስረሀት አላስተናገዷቸውም በል እንደውም መረጃቹ እየተጣራ ነው ፈተና እና ምዘና ኤጀንሲ ሂዱ በማለት ለማንገላታት ሞከሩ ተወካዮቻችንም ወደ ፈተና ምዘና ኤጀንሲ ሄዱ እዛ ሲሄዱ ግን የገጠማቸው አሳፋሪ እና አፀያፊ ነገር ነበር። ከአንድ የተማረ ትውልድ እፈጥራለው ከሚል ግለሰብ ማዮጣ ማይጠበቅ ነገር ነው የተመለከቱት

🚫ከተባሉት አሳፋሪ ነገር በጥቂቱ

1⃣ ተማሪዎቹ ለኤንጀንሲውን ዋና ዳይርክተር ከማስረጃ ጋር የመጡበትን አላማ ለማስረዳት ቢሞክሩም ውጡልጥ ከቢሮዬ በማለት ተማሪዎቹን አሶጥተዋቸዋል።

2⃣ ተማሪዎቹ ተገቢውን ምላሽ ባለማግኘታቸው እሳቸውን እስከ ምሽቱ 11 ሰዓት በመጠበቅ ለማነጋገር ድጋሚ ቢጥሩም ከአንድ ሚኒስቴር በማይጠበቅ መልኩ ተማሪዎችን የመስደብ እና አልፎም የማንቋሸሽ ስራ ሰርተዋል።

3⃣ ተማሪዎቹ ፈተናው እንደተሰረቀ ሚያሳይ መረጃ ቢያመጡም ዳርይክተሩ ግን አልተሰረቀም የያዛቹት መረጃ የውሸት ነው። በማለት የውሸት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

4⃣ ተማሪዎቹ የተማሪ ሞራል እየተጎዳ ነው ተማሪ እራሱን እያጠፋ ነው ተማሪዎች ስነ ልቦናዊ ጉዳት እየደረሰባቸው ነው ብለው ለማስረዳት ሲሞክሩ ሚኒስተሩ እንዲህ ብለው ለተማሪው ምላሽ ተሰጥቷል

"ያላቹት አፍራካ ወስጥ ነው ከዛ ሲቀጥል ደሞ ethiopia ውስጥ"
በማለት ለተማሪዎቹ መልስ ሰጥተዋል።

⚠️ይህ ማለት ምን አይነት መልስ እንደሆነ ይብራራልን

5⃣ ዳይርክተሩ ካወሩት በጣም ሚገርመው part

" apptitude ፈተና እንደወጣ አውቂያለው እዚ ቁጭ ብዬ ደረሰኝ መልስ አሉ ከዛ ወዲያውኑ ፕሮፈሰር ጠራውና የapptitude መልስ የሰሩትን ፕሮፌሰር ጠርቼ ይህን ነገር እስኪ እዩት ብዬ አሳየዋቸው ይላሉ በtelegram የተላከውን መልስ እና መልሱ ሲሰራ 56 መጣ እና 56 የመጣውን ውጤት የተማሪውን ውጤት affect ስለ ማያረግ ተማሪዎቹ እንዲሰሩት ግሩፑን ተውኩት "በማለት ፈተናውን መሰረቁን እራሳቸው ተናግረዋል።

ሌሎችም የተባሉ ነገሮች አሉ


እኔ ይህን አሳፋሪ እና ቆሻሻ መልስ ስሰማ በጣም ነው ያፈርኩት በጣም ግን አሁን እኛ ማድረግ ያለብን ቀጣዩ ትውልድ የኛው ወንድም እና እህቶች ናቸው እና እነዚ አመራር ላይ ያሉት ደሞ ተማሪውን መግደል ነው የያዙት ስለዚ ይሄ ነገር በኛ ሊበቃ ይገባል የኛ ውጤት ባይስተካከልም ይህን ነገር ግን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እኛ ማስቆም አለብን ሀገራችንን ምኖዳት ከሆነ በነዚ ዝርክርክ አመራሮች ምክንያት የነገው ትውልድ መጥፋት ስለሌለበት ሁላችንም ተባብረን የሚከፈለውን መስዋትነት ከፍለን እስከ በላይ አካል ሄደን ይህን የነዚን ትውልድ አጥፊ አመራራሮችን ቆሻሻ ስራ ገሀድ በመውጣት አይደለም ትምህርት ሚኒስቴር ቀበሌ እንኳ እንዳይደርሱ ማረግ አለብን

👉ሁላቹም ከጎናችን ልትቆሙ ይገባል❗️

ነገ እኛ ላይ የተፈፀመው እናንተም ላይ ሆነ ሌሎች ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ላይ ይህ ነገር ከመፈፀሙ በፊት "ሳይቃጠል በቅጠል ነውና "ነገሩ ሀገር ሚወድ ሰው በሙሉ ከኛ ጎን ለቆም ይገባል።


🛑ይህ ነገር በኛ ይብቃ🚫

ይብቃ❗️
ይብቃ ❗️❗️
ይብቃ ❗️❗️❗️
ይብቃ❗️❗️❗️❗️


ፍትህ ለ 12 ክፍል ተማራዎች

justice for grade 12 students




@keratachn12
#Kesatyan_update

ለ ASTU & AASTU መግቢያ ፈተና የወሰዳቹ በዚ link በመጠቀም ውጤታቹን ማየት ትችላላቹ::
http://cba4.astu.edu.et

@kesatyan
@kesatyan
2013 ወደ ዩንቨርሲቲ አዲስ የሚገቡ ተማሪዎች የዩንቨርሲቲ ምርጫ እጅግ ቢዘገይ እስከ ሚያዚያ 20 ድረስ ብቻ ሊሆን እንደሚችልና ዩንቨርሲቲዎችም በቀሪዎቹ የሚያዚያ ቀናት ማለትም ከሚያዚያ 20 በኋላ ባሉት ቀናት ተማሪዎቻቸውን እንዲቀበሉ አቅጣጫ ተቀምጧል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://hottg.com/temhert_bebete
https://hottg.com/temhert_bebete
''የ12ኛ ክፍል ምደባ ውጤት ይፋ ሆነ!


የሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስትር ለAhadu FM በላከው መረጃ መሰረት የዘንድሮው ምደባ ካለፉት አመታት ሁሉ በፋትሃዊነቱ እና በደረጃ ልኬት ቀመር ልዩ ያደርገዋል!

🔰በዚህም መሰረት ከ 500 በላይ ያመጡ ተማሪዎች ወደ 1ኛ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበዋል!!

🔰ከ 450 -500 ያመጡ ተማሪዎች ወደ 2ኛ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበዋል!!|

🔰ከ 400-450 ያመጡ ተማሪዎች ወደ 3ኛ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበዋል!!

🔰ከ ከመለፊያ ነጥብ -400 ያመጡ ተማሪዎች ወደ 4ኛ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበዋል!!''

የሚል መልዕክት ጓደኛዬ SHARE አርጎልኝ እኔ ግን አላመንኩትም!እናንቸም እንዲህ አይነት መረጃ ቢደርሳችሁ እንዳታምኑ እስካሁን ምደባ አልተለቀቀም!

እስከዛው ይቺን ለጓደኞቻችሁ ሼር እያረጋችሁ ጀለሶችን አስበርግጉ😂

🔗SHARE 🔗SHARE

📚 JOIN : @Exo_Ethiopia
📚 JOIN : @Exo_Ethiopia
* ዛሬ ይፋ በተደረገው የተማሪዎች ምደባ ላይ ቅሬታ አለን ያሉ ወላጆች እና ተማሪዎች መልዕክታቸውን እያደረሱ ይገኛሉ !

MoSHE ዛሬ የአዲስ ተማሪዎችን ምደባ ይፋ ያደረገ ሲሆን ምደባቸውን የተመለከቱ አንዳንድ ተማሪዎች እና የተማሪዎቹ ወላጆች ቅሬታ እንዳለባቸው ገልፀዋል።

MoSHE ባስቀመጠው የቅሬታ መቀበያ አድራሻ (ድህረገፅ) ቅሬታቸውን እንደሚያሳውቁ ገልፀው ተገቢው ምላሻ እንዲሰጣቸውም አሳስበዋል።

ከውጤታ ጋር የፈለጉት ምርጫ አልተሰጠኝም ያለ አንድ የቲክቫህ አባል ፥ በሀገር አቀፉ ፈተና ከ630 በላይ ቢያመጣም የሚፈልገው የዩኒቨርሲቲ ምርጫ እንዳተጠበቀለት ገልጿል። ይህንንም የሚገልፅ ማስረጃውን ከላይ አያይዟል።

በተጨማሪ አንዲ ከ620 በላይ ያመጣች ተማሪም በ400 ቤት ውስጥ ውጤታ ያላቸው ምርጫቸው ሲጠበቅ የእሷ ግን እንዳልተጠበቀ ገልፃ የምደባው ሂደት እንዳሳዘናት ገልፃለች።

ይህን መሰል ሌሎች ቅሬታዎች ወደቲክቫህ እየተላኩ ሲሆን በምደባ ላይ ያሉ ችግሮች ጊዜው ሳይሄድ ማስተካከያ እንዲደረግ በወላጆች እና ተማሪዎች ተጠይቋል።

MoSHE ዛሬ የተማሪዎችን ምደባ ይፋ ሲያደርግ በምደባው ላይ ቅሬታ የሚኖራቸው ተማሪዎች ካሉ በአካል መምጣት ሳያስፈልጋቸው https://forms.gle/Jt9L7F2EDDC62YLQ7 በዚህ ሊንክ በመግባት ቅሬታቸውን እንዲያቀርቡ ብሏል።

ተማሪዎች ከላይ በተቀመጠው ቅሬታ መቀበያ ላይ ቅሬታችሁን ማሳወቅ ትችላለችሁ።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
በምደባ ዙሪያ ለቅሬታ አቅራቢዎች በሙሉ :

የ2013 ዓ.ም የተማሪዎች ምደባ ቅሬታ ማቅረቢያ ቀናት ከሚያዚያ 25 እስከ ሚያዚያ 28/2013 ዓ.ም ነው።

ቅሬታ ያላችሁ ቅሬታችሁን በአካል መምጣት ሳያስፈልግ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው ከታች ባለው ድረገፅ ላይ ወይም የኢሜል እና በስልክ አድርሻዎች ማቅረብ ትችላላችሁ።

ማሳሰቢያ: MoSHE በአካል የሚመጣ ቅሬታን የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

ዌብ ሳይት፡ https://forms.gle/Jt9L7F2EDDC62YLQ7
ስልክ ቁጥር ፦
• +251911763794
• +251943543805
ኢሜል፡ [email protected]

የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
ሚያዚያ 22 ቀን 2013 ዓ/ም

@tikvahethiopia @MinistryoSHE
'ከፍተኛ ውስጤት ያላቸው ተማሪዎች ቅሬታ'

የ2012 ብሄራዊ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ የቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የመጀመሪያው የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እንዳልተጠበቀላቸው ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ከፍተኛውን ውጤት ያስመዘገበው ተማሪ ብሩክ ባልካቸውን ጨምሮ ቢያንስ 10 ተማሪዎች በመጀመሪያው የዩኒቨርሲቲ ምርጫ እንዳልተመደቡ ተማሪዎች ለቲክቫህ አሳውቀዋል።

ከመስቀል አደባባይ ጀርባ የሚገኘው ቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት በ2012 ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበት ት/ቤት ሲሆን ከ600 በላይ ካመጡት 26 ተማሪዎች ጥቂቶቹ ብቻ በመጀመሪያ የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸው እንደተመደቡ ተማሪዎቹ ገልፀዋል።

እንደማሳያነት ፦
• በመፈተኛ ቁጥር 361757 - 669 ያስመዘገበው
• በመፈተኛ ቁጥር 361749 - 645 የተመዘገበው ውጤት
• በመፈተኛ ቁጥር 361725 - 640 የተመዘገበው ውጤት
• በመፈተኛ ቁጥር 361745 - 632 የተመዘገበው ውጤት የመጀመሪያው ምርጫቸው ያልተጠበቀላቸው የከፍተኛ ውጤት ባለቤት ተማሪዎች መካከል ናቸው።

በተመሳሳይ ፣ ልደታ ካቶሊክ ካቴድራል ፣ Kotebe Metropolitan University Menelik I Science Shared Campus ፣ ሀዋሳ ኮምቦኒ ከ600 በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች ምርጫቸው አለመጠበቁን አሳውቀዋል።

በምደባው ላይ ማረሚያና ማስተካከያ እንዲደረግ አሳስበዋል።

ከፍተኛ ውጤት አስመዝግበው በመጀመሪያ ምርጫቸው ያልተመደቡ ተማሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ ካሉ ትምህርት ቤቶች ብቻ ሳይሆን ከክልል ከተሞችም እንደሆነ ለቲክቫህ የተላኩት መልዕክቶች ያስረዳሉ።

@tikvahethiopia
Have you checked out Ask Anything Ethiopia yet? It's Ethiopia's first question and answer platform, where you can get answers to your biggest questions from thousands of people! You can join using the link below:

https://hottg.com/ask_anything_ethiopia_bot?start=i394921036
አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ !

የ2013 ዓ.ም የተማሪዎች ምደባ ቅሬታ ማቅረቢያ ቀናት ከዛሬ ሚያዚያ 25 እስከ ሚያዚያ 28/2013 ዓ.ም ነው።

ቅሬታ ያላቸው ቅሬታቸውን በአካል መምጣት ሳያስፈልግ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው ከታች ባለው ድረገፅ ላይ ወይም የኢሜል እና በስልክ አድርሻዎች ማቅረብ ይቻላል ነው የተባለው።

ማሳሰቢያ: MoSHE በአካል የሚመጣ ቅሬታን የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

ዌብ ሳይት፡ https://forms.gle/Jt9L7F2EDDC62YLQ7
ስልክ ቁጥር ፦
• +251911763794
• +251943543805
ኢሜል፡ [email protected]

[የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር]

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"...ተማሪዎች የእርስ በእርስ የዩኒቨርሲቲ ቅያሬ ሙከራ አይቻልም" - ወ/ሮ አመለወርቅ ሕዝቅኤል

[የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን]

አዲስ የተመደቡ ተማሪዎች በግል የሚያደርጉት የእርስ በእርስ የዩኒቨርሲቲ ቅያሬ ሙከራ ህገ-ወጥ እንደሆነ እና እንደማይቻል የኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከዩኒቨርሲቲ ዩኒቨርሲቲ በግል ለመቀያየር እየተቀመጡ ያሉ መልዕክቶች ተገቢ ያልሆኑ እና ህጋዊ አለመሆናቸውን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።

ዘንድሮ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ከ147 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ለመቀበል የተዘጋጁ ሲሆን የተማሪዎች ምደባም ይህን የመቀበል አቅም መሰረት በማድረግ እንደተካሄደ ወ/ሮ አመለወርቅ ሕዝቅኤል ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ወ/ሮ አመለወርቅ አክለው ፥ "ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ለመሄድ የማያስችል ምክንያት ያላቸው ተማሪዎች ማስረጃቸውን በማቅረብ ውሳኔ እያገኙ ነው ፤ ይህ አሰራር ከዚህ በፊትም እየተሰራበት ነበር" ብለዋል።

በተለይ ከህመም ጋር በተያያዘ ችግር ያለባቸው ተማሪዎች በሀኪሞች ቦርድ የተረጋገጠ ማስረጃ ካቀረቡ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል ሲሉ ገልፀዋል።

ከዚህ ውጭ ሚኒስቴሩ አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአመዳደብ ላይ ያላቸውን ቅሬታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ ይሰጣል ብለዋል።

@tikvhaethiopiaBOT @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች 👆

- የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የ2013 ዓ.ም አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ሴኔት የፀደቀዉን ትክክለኛ የመግቢያ ቀን በዚህ ሳምንት ጥቂት ቀናት ዉስጥ ይገለፃል። አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ጥቂት ቀናት የቀሯቸው ስለሆነ ከወዲሁ ሁለንተናዊ ዝግጅት እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፏል።

- በ2013 በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ግንቦት 5 እና 6 ቀን 2013 ዓ/ም መሆኑ በይፋ ተገልጿል። ምዝገባ ጠባሴ ቀበሌ 09 በሚገኘው ዋናው ግቢ ነው የሚካሄደው። ኦረንቴችን ግንቦት 7 ተካሂዶ ሰኞ ግንቦት 9 ትምህርት ይጀምራል።

አስፈላጊ : የ8ኛ ፣የ10ኛ ክፍል ፣ የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት እና የብሄራዊ ፈተና ውጤቶች ማስረጀ ዋናውም እና ከእያንዳዱ 2 ፎቶ ኮፒ ፤ አንሶላ ፣ ብርድልብስ ፣ የስፖርት ትጥቅ።

- በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በ2012 ዓ/ም በ2ኛ ሴሚስተር በተለያየ ምክንያት ትምህርት አቋርጠው ለቀሩ የ3ኛ፣ 4ኛ፣ እና 5ኛ ዓመት ተማሪዎች የነበሩ MoSHE ትምህርት እንዲቀጥሉ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲመለሱ እና ትምህርት እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀርቧል። ከላይ የተጠቀሱ ተማሪዎች ከ04-05/09/2013 ድረስ ሬጅስትራ እና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ እንዲመዘገቡ ተብሏል።

- የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንዳሳወቀው ትክክለኛው የህብረቱ መገኛ ይህ @AUSUE ብቻ በመሆኑ ተማሪዎች በተለያዩ ገፆች ሀሰተኛ መረጃዎች እንዳይደናገሩ አሳስቧል።

- ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ የ5ኛ አመት የኤሌክትሪካል እና ኮምፒዩተር ምህንድስና ተማሪዎች ኢንተርንሽፕ ወጥተው የቆዩ ሚያዚያ 30/2013 እንዲመለሱ ጥሪ አስተላልፏል።

- የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ ዓመት እና ከዛ በላይ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው በ26-27/08/2013 ዓ/ም መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ተማሪዎቹ ባሉበት ሆነው በኦንላይን እንዲመዘገቡ ተብሏል። ለ1ኛ እና 2ኛ ዓመት ተማሪዎች በቅርብ ይገለፃል። መመዝገቢያ : estudent.wsu.edu.et

📎የዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ የተማሪ ተወካዮች፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች የቲክቫህ መረጃ ማስቀመጫ /ማከማቻ አድረሻ @TikvahUniversityybot @tikvahethiopiaBOT
የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርስቲ ምዝገባ ለአጭር ጊዜ ተራዝሟል፡፡

የመጀመሪያዉ ቴክኒካል ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያዎቹ ምሩቃን ለመሆን የመቁረጫ ነጥቡን የምታሟሉ ተማሪዎች መመዝገብ ትችላላሁ ተብሏል።

MoSHE
@TIKAVAHUNIVERSITY
#DebreBirhan_Universitiy

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ግንቦት 5 እና ግንቦት 6 የነበረው ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የግቢው ተማሪዎች ህብረት ምክትል ፕሬዝዳንት አሳውቆናል ።

በነገው ዕለት የተራዘመው የመግቢያ ቀን እንደሚነገርም ጨምሮ ገልፆልናል።

መረጃው ላልደረሳቸው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ሼር አድርጉላቸው።

ኢትዮ ዩኒቨርስቲ መረጃ
Share
ተጨማሪና ወቅታዊ መረጃ ለማግኛት
👇👇👇👇
@ethio_university_info
@ethio_university_info
ለጥቆማ👇👇
@think_positiive
HTML Embed Code:
2024/04/30 02:53:15
Back to Top