TG Telegram Group Link
Channel: TIKVAH-ETHIOPIA
Back to Bottom
#ግላመር

ግላመር የስነ-ውበት አካዳሚ አዳዲስ የከፈታቸውን ቅርንጫፎች እና ተማሪዎቹን አስመረቀ።

ግላመር የስነውበት አካዳሚ የቁጥር 5 ፣ 6 እና 7ተኛ ቅርንጫፎቹን መከፈት እንዲሁም በጥፍር እና አይላሽ ስራ ያስተማራቸውን ተማሪዎች መመረቅ ምክንያት በማድረግ ግንቦት 28/2016 ዓ.ም ምሽት በሸራተን አዲስ ሆቴል ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች እና ታዋቂ አርቲስቶች እንዲሁም የግላመር ቤተሰቦች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተመረቀ።

የግላመር ድርጅት መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ወ/ሮ ህይወት ታደሰ በመድረኩም የመጡትን እንግዶች አመስግነው ለተመራቂ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላቹ መልእክት ያስተላለፋ ሲሆን ግላመር ከዚህ በሗላም በመላው ኢትዮጵያ ቅርንጫፎቹን በጥራት እንደሚያሰፋ ገልፀዋል።

የድርጅቱ ም/ት ስራ አስኪያጅ የዚህዓለም ታምራት ይህንን ፕሮግራም በማስመልከት ለወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን ለ10 ተማሪዎች የነፃ የትምህርት እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ በስጦታነት አበርክቷል።

ግላመር የከተማችን ምርጥ እና ግዙፍ የስነ-ውበት ተቋም ነው።

https://www.instagram.com/glamournail_addis1?igsh=bnUyYnV5OWdjN3d1
#glamournail
#glamoureylash
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች  ወ.ዘ.ተ

አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ የሚያገኙበትን ሱቃችንን ይጎብኙ።

የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ ባሉበት ሆነው ይዘዙን እናደርሳለን።

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።

@sww2844 0928442662 / 0940141114

https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ፤ የመኖሪያ ቤት የአከራይ ተከራይ የውል ስምምነት ምዝገባ ዛሬ በሁሉም ክ/ ከተማ በሚገኙ ወረዳዎች ተጀመረ።

ማንኛውም የመኖሪያ ቤት አከራይና ተከራይ በምዝገባ ወቅት ማሟላት ያለባቸው ምንድነው ?

➡️ በህግ አግባብ የተዘጋጀ የመኖሪያ ቤት ውል ሰነድ

➡️ #የአከራይ እና #የተከራይ የነዋሪነት መታወቂያ ፣ የመስሪያ ቤት መታወቂያ ፣ መንጃ ፍቃድ ፣ ፓስፖርት ፣ የጠበቃ ፍቃድ ፣ የሰራተኞች ጡረታ መታወቂያ ፣ የዩኒቨርሲቲ / ኮሌጅ ተማሪ የሙያ ስራ ፍቃድ ኦርጅናል ኮፒ ፤

➡️ የመኖሪያ ቤት ውሉ የሚመዘገበው በወኪል ከሆነ ህጋዊ ውክልና የሁለት ምስክሮች የታደሰ መታወቂያ ኦርጅናል ኮፒ፤

➡️ አከራይ የመኖሪያ ቤቱን ለማከራየት የሚያስችል መብት እንዳለው የሚያሳይ ህጋዊ ሰነድ :-
- የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ
- ሰነድ አልባ ይዞታዎች መሆኑን ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ወይም
- በፍርድ አፈፃፀም የተሸጠ ንብረት ሰነድ ወይም
- የተከራየው ቤት በውርስ የተገኘ ሆኖ ስም ዝውውር ካልተፈፀመ የወራሽነት ማረጋገጫ

#ኦርጅናል እና #ኮፒ ይዘው  መገኘት አለባቸው።

መረጃው የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ነው።

" የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 " ምን ይዟል ? በዚህ ያንብቡ👇
https://hottg.com/tikvahethiopia/88081

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SouthEthiopiaRegion ➡️ " ... በረሀብ ከምንሞት መብታችን እየጠየቅን አደባባይ ላይ መሞት መርጠን ነው ወደ ርእሰ መስተዳድሩ ቢሮ የሄድነው " - የሶዶ ዙሪያ የመንግስት ሰራተኞች ➡️" ማንም መብቱን በነጻነት የመጠየቅ መብት አለው " - የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃፊዉ አቶ ወገኔ ብዙነህ የ2 ወራት ደሞዛችን ይከፈለን ያሉ የወላይታ ዞን የመንግስት ሰራተኞች አደባባይ መውጣታቸዉን…
#ደመወዝ #ደቡብኢትዮጵያ

° " ...ድርጊቱ የደመወዝ ቅሸባ ነው ሊባል የሚችለው ፤ እንዲህ አይነት የደመወዝ አከፋፈል ሰምተንም አናውቅ " - ሰራተኞች

° " ከእኛ #የሚወርደው የበጀት ሀብት እኮ የመንግስት ሰራተኛ ደመወዝ ለመክፈል የሚያስችል ነው " - የክልል ፋይናንስ ቢሮ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የመንግስት ሰራተኞች " የደመወዝ ይከፈለን " ጥያቄ በብርቱ ከተነሳባቸው አካባቢዎች አንዱና ዋነኛው የ #ወላይታ_ዞን እንደሆነ ይታወቃል።

ሰራተኞቹ ችግር ሲብስባቸው እና ታግሰው ሲመራቸው ሰልፍ  ጭምር በመውጣት ጥያቄ አቅርበዋል።

ለ3 ወራት ያለ ደመወዝ የቆዩት የመንግስት ሰራተኞች አሁን ላይ #የ40_በመቶ እና #የ50_በመቶ ክፍያ ብቻ እየተፈጸመላቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል #የፋይናንስ_ቢሮ ፤ " ደመወዝ ባለመክፈል የመንግሥት ሰራተኛውን እያስራቡ ይገኛሉ " ባላቸው የዞንና የወረዳ የስራ ሃላፊዎች ላይ ፖለቲካዊ እና አስተዳደራዊ #እርምጃ እንደሚወስድ አሳውቋል።

ቢሮው ለወረዳዎቹ በቂ በጀት ማስተላለፉን ገልጿል።

" ለሰራተኛው #ግማሽ_ደመወዝ በመክፍል ቀሪውን ለሌላ የወጭ ርዕስ ይጠቀሙበታል " ሲል ወቅሷል።

አሁን በተለያዩ ወረዳዎች እየተከፈለ ይገኛል የተባለው ደመወዝ በዞኑ መንግሥት ሰራተኞች ዘንድ አጥጋቢ ምላሽ ተደርጎ አልተወሰደም።

ሰራተኞቹ ለ ' ዶቼ ቨለ ሬድዮ ' በሰጡት ቃል ፤ " ምላሹ አጥጋቢ ያልሆነ ፣ የሰራተኛውን ስነ ልቦናም የጎዳ ነው " ብለውታል።

የመንግስት ሰራተኞቹ ፥ ደመወዛቸው ባልተለመደ ሁኔታ ተቆራርጦ እየተከፈላቸው እንደሚገኝ ተናግረው ፤ " የሰራተኞች ጥያቄው ተመልሷል ለማለት እንቸገራለን " ብለዋል።

በአብዛኞቹ ወረዳዎች ላይ አሁን እየተከፈለ የሚገኘው የደመወዛቸውን ከ40 እስከ 50 ፐርሰት ያህል መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሰራተኞቹ ፦

ደሞዛችን እንደተፈለገ ተቆረጦ እየቀረ ነው፤

አከፋፈሉ የፋይናንስንም ሆኖ የመንግሥት ሰራተኛ አስተዳደር መመሪያን የሚጻረር ነው፤

ድርጊቱ #የደመወዝ_ቅሸባ እንጂ ሌላ ምንም ሊባል አይችልም ምክንያቱም እንዲህ አይነት የደመወዝ አከፋፈል በትኛውም ዓለም ሰምተን አናውቅም ብለዋል።

ሰሞኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ዎላይታ ሶዶ ላይ የፋይናንስ ባለሙያዎች ሥልጠናዊ ውይይት አካሄዶ ነበር።

በመድረኩ የደሞዝ ጉዳይ በሰራተኞች ተነስቷል፡፡

የቢሮው ሃላፊ የሆኑት አቶ ተፈሪ አባተ ፥ ፋይናንስ ቢሮ ለወረዳዎች በቂ የበጀት ሀብት እያስተላለፈ እንደሚገኝ አሳውቀዋል።

ወላይታን ጨምሮ በክልሉ አንዳንድ ወረዳዎች ውቅጥ የፋይናንስ ቁጥጥር / ኦዲት / መደረጉን ጠቅሰዋል።

" ወደ ወረዳዎች ሚወርደው የበጀት ሀብት የመንግስት ሰራተኛ ደመወዝ ለመክፈል የሚያስችል ነው፡፡ ይሁን አንጂ አንዳንድ ወረዳዎች ከአሰራር ውጭ ደመወዝ #በፐርሰንት_እየከፈሉ ሰራተኛው እንዲራብ ፣ በክልሉ ላይም እንዲያማርር እያደረጉ ይገኛሉ " ብለዋል።

ክልሉ በቀጣይ በእነኝህ አካላት ላይ አስተዳደራዊ እና ፖለቲካዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ " #ለሽብረቃ የሚወጡ አላስፈላጊ ወጪዎችን ለመገደብ የሚያስችል የወጭ ቅነሳ መመሪያ ተግባራዊ ይደረጋል " ሲሉ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል።

Credit - #ዶቼቨለሬድዮ
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሲጀመር ‘የኮቴ’ ክፍያ አገር ውስጥ መጠየቅ አግባብ አይደለም " - ጣና የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች ማኀበር የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች ፣ ሞጆ መግቢያ ‘ #የኮቴ ’ በሚል ታጣቂዎች አስቁመው 2,000 ብር እያስከፈሏቸው መሆኑን እየገለጹ ይገኛሉ። ካሁን ቀደም ገንዘቡን ሲጠየቋቸው የነበረው አንዳንድ ጊዜ በቀን እንደነበር ፣ ከሰሞኑን ግን ቀንም ሌሊትም እየጠየቋቸው ከመሆኑም ባሻገር ድብደባና…
#Ethiopia

“... የፌደራል ፓሊስ በፓትሮል መንገድ ላይ ወጥቶ እንዲሰራ ሁሉ ተደርጓል ” - ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር

የድንበር ተሻጋሪ የከባድ መኪና #አሽከርካሪዎች አገር ውስጥ ከገቡ በኋላ በታጠቁ ኃይሎች እስከ ግድያ የሚድረስ ጥቃት እንደሚፈጸምባቸው መግለጻቸውን በተደጋጋሚ መረጃ ተለዋውጠን ነበር።

አሽከርካሪዎቹ፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ እየሰጠ እንዳልሆነ በመውቀስ የጥቃት መጠኑ ይለያይ እንጂ እስከ ቅርብ ጊዜ እንደቀጠለ ገልጸዋል።

ከዚህ ባለፈ ሀገር ውስጥ ገብተው የ " ኮቴ " እየተባለ የሚከፍሉት ክፍያ እጅግ ለስራቸው ፈተና እንደሆነ አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች እየደረሰብን ነው ያሉትን ችግር ለመቅረፍ በተጨባጭ ምን እየተሰራ ነው ? ሲል የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴርን ጠይቋል።

የተቋሙ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ ዶ/ር ቶለሳ በሰጡት ምላሽ ፣ “ ኢትዮጵያ ውስጥ ከገቡ በኋላ ሞጆ ወይንም ደግሞ ማራገፊያ ቦታ እስከሚደርሱ ነበር አሁን በጣም ቁጥጥር እየተደረገ ነው ” ብለዋል።

“ ከሚኒስቴር መ/ቤታችንም ሌላም አካል Direction ተሰጥቶ፣ እንዲያውም #የፌደራል_ፓሊስ በፓትሮል መንገድ ላይ ወጥቶ እንዲሰራ ሁሉ ተደርጓል ” ነው ያሉት።

“ ስለዚህ እኛ እንደዚህ አይነት #እሮሮ ይደርስባቸዋል የሚል መረጃ የለንም ” ያሉት ዶክተር ቶተሳ፣ “ አዲስ የመጣ ነገር የለም። #እየተሻሻለ_መጣ_እንጂ ” ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፣ አሽከርካሪዎቹ አገር ውስጥ ከገቡ በኋላ “ በተለይ ኦሮሚያ ክልል” የ “ #ኮቴ ” እየተባሉ 2,000 እንደሚከፍሉና ከዚህም አለፍ ሲል ድብደባ ጭምር እየደረሰባቸው መሆኑን እየገለጹ ነው። እናንተ ደግሞ ‘ ችግሩ እየቀነሰ ነው ’ እያላችሁ ነው። ለዚህ ቅሬታ ምላሽዎ ምንድን ነው ? የሚል ጥያቄ አቅርቧል።

ዶ/ር ቶለሳ “ አዎ ይኼኛውን እኛም ከጭነት ተሽከርካሪ ተወካዮች ጋር ስብሰባ አካሂደን ነበር። በዚህም ወቅት ክፍያ እንደሚያስከፍሉ ሰምተናል ” ብለዋል።

ችግሩን ለመቅረፍ ከከተማው አስተዳደር ጋር ውይይት እንደሚደረግ ገልጸዋል። “ #ድብደባ ለሚባለውን ግን መረጃ የለንም። ካለ እንሄድበታለን ” ብለዋል።

“ ከኦሮሚያ ክልል መንግስትም ጋር አውርተን መፍትሄ የምንሰጥ ይሆናል ” ሲሉም አክለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#Amhara

በአማራ ክልል ዓመቱን ሙሉ ጭራሽ ምንም ያልተማሩ ተማሪዎች እንዳሉ ተሰምቷል።

በዚህም ምክንያት ምንም አይነት የ6ኛ፣ የ8ኛ እና የ12 ክፍል ፈተና የማያስትፈትኑ ዞኖች እንዳሉ ታውቋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ በሰጠው መግለጫ ፥ ከዓመቱ መጀመሪያ ጀምሮ ምንም መቆራረጥ ሳይኖር እየተማሩ አሁን ላይ ትምህርታቸውን እየጨረሱ ያሉ ተማሪዎች አሉ ብሏል።

መሃል ላይ እንዲጀምሩ የተደረጉና የይዘት ክለሳ ተደርጎ እክሰ ነሃሴ ወር ተምረው እንዲያጠናቅቁ የሚደረጉም አሉ ፤ እነሱ አሁን ትምህርት ላይ ናቸው ሲል ገልጿል።

ዓመቱን ሙሉ በሙሉ ደግሞ ጭራሽ ምንም ያልተማሩ ተማሪዎች እንዳሉ ቢሮው አሳውቋል።

ይህ በአብዛኛው በጎጃም ቀጠና እንደሆነ ተጠቁሟል።

ሰሜን ጎጃም እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ምንም አይነት ተማሪ / አንድም እንኳን ተማሪ የ6ኛ ፣ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ፈተና #እንደማያስፈትኑ ገልጿል።

ምስራቅ ጎጃም ግን ትንሽ ተማሪ አለው ተብሏል።

የትምህርት ቢሮው አሁን ላይ እየተማሩ ያሉ ግን ፈተና የማይፈተኑትን በቀጣይ በሁለተኛው ዙር እንዲፈተኑ ለማድረግ መታቀዱን አመልክቷል።

ምንም ያልተማሩ ተማሪዎችን በሚመለከት ያለ አንዳች ጥፋታቸው ከእድሜያቸው ላይ አንድ አመት መቀነሱ አገባብነት ስለሌለው የተጎዳ ስነልቦናቸውን ለመጠገን ሚያግዝ ስልጠና ይዘጋጃል ብሏል።

የይዘት ክለሳ ተደርጎም ቢሆን ሲማሩ ከነበሩ ተማሪዎች ወደኃላ እንዳይቀሩ ለማድረግ ጥረት ይደረጋል ሲል ገልጿል።

በአማራ ክልል የ8ኛና 6ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 4/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጥ ሲሆን ፦

184,393 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ሰኔ 4 እና 5 ቀን 2016 ዓ.ም

170,470 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ሰኔ 13 እና 14 ቀን 2016 ዓ.ም ፈተናቸውን ይወስዳሉ ተብሏል።

በአማራ ክልል በአጠቃላይ (በሁሉም የትምህርት ደረጃ) በዚህ ዓመት መመዝገብ የነበረባቸው 6.2 ሚሊዮን ተማሪዎች ውስጥ የተመዘገቡት 4 ሚሊዮን ናቸው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ፋብሪክ የፋሽን ዲዛይን ማሰልጠኛ ተቋም

ስልክ ፦ 0911375989 / 0924903999

👉 አድራሻ ፦  ሰሚት ፍየል ቤት አፍለንት ትሬዲግ  ውልና ማስረጃ ያለበት ህንፃ ላይ  4ኛ ፎቅ

👉 Telegram - https://hottg.com/FabricSchoolOfFashionDesign

ፋብሪክ የፋሽን ዲዛይን ማሰልጠኛ ተቋም
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች  ወ.ዘ.ተ

አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ የሚያገኙበትን ሱቃችንን ይጎብኙ።

የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ ባሉበት ሆነው ይዘዙን እናደርሳለን።

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።

@sww2844 0928442662 / 0940141114

https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #Axum የአክሱም ኤርፓርት ሰኔ 2/2016 ዓ/ም ዳግም የበረራ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል።  በትግራይ ጦርነት ከፍተኛ  የሆነ ጉዳት የደረሰበት የአክሱም አፄ ዮውሀንስ አራተኛ  ኤርፖርት ሰኔ 2 የመጀመሪያ ዳግም በረራውን ያደርጋል። እሁድ ሰኔ 2 በኤርፓርቱ ዳግም መደበኛ የበረራ  አገልግሎት ስነ-ሰርዓት ማስጀመሪያ ጥሪ የተደረገላቸው የክልልና የፌደራል ባለስልጣናት እንደሚገኙ ቲክቫህ…
#Axum #Update
 
የአክሱም ሃፀይ ዮሃንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፍያ ከሶስት ዓመት በኃላ ዛሬ እሁድ ሰኔ 2 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት የመጀመሪያውን ይፋዊ የአውሮፕላን  በረራ አስተናግዷል።

የዳግም በራራ አገልግሎት ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት የክልል እና የፌደራል ባለስልጣናት በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።

በቦታው የሚገኘው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በላከው መረጃ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን አዲስ አበባ ተነስቶ ከቀኑ 6:00 ላይ አክሱም የደረሰው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737-700 አውሮፕላን 140 ተጓዦች ይዟል።

ከተጓዦቹ ውስጥም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ፣ የፌደራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች ይገኙበታል።

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ  አስተዳደር ፕረዜዴንት አቶ ጌታቸው ረዳ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

#Axum #Ethiopia #Tigray

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#Axum #Update   የአክሱም ሃፀይ ዮሃንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፍያ ከሶስት ዓመት በኃላ ዛሬ እሁድ ሰኔ 2 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት የመጀመሪያውን ይፋዊ የአውሮፕላን  በረራ አስተናግዷል። የዳግም በራራ አገልግሎት ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት የክልል እና የፌደራል ባለስልጣናት በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል። በቦታው የሚገኘው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በላከው መረጃ ከቦሌ…
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ ፦ የአክሱም የሃፀይ ዮሐንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፊያ በትግራይ ጦርነት በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ከአገልግሎት ውጭ ሆኖ ቆይቷል።

ጦርነት መቆሙና ሰላም መፈጠሩን ተከትሎት ባለፉት ወራት ጥገና ተደርጎለታል።

ዛሬ ሰኔ 2/2016 የመጀመሪያውን ዳግም የአውሮፕላን በረራ አስተናግዷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑትን አቶ መስፍን ጣሰውን ፣ የፌደራል እና የክልል የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ 140 ተጓዦች የያዘው የመጀመሪያ አውሮፕላን አክሱም ሃፀይ ዮሐንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ አቀባበል ተደርጓል።

በአቀባበል ስነ ስርዓቱ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ባለስልጣናት ተገኝተዋል።

Video Credit - Tigrai TV

@tikvahethiopia
#DStvEthiopia

✈️ አውሮፓ እንሂድ

🏆የምትወዱዋቸውን የአውሮፓ ታላላቆችን የዋንጫ ፍልሚያ 5 ቀን ቀረው!

⚽️በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአውሮፓ ዋንጫ ሊጀመር ነው! በጀርመን የሚደረጉትን ደማቅ ጨዋታዎችን ሁሉንም በቀጥታ በዲኤስቲቪ በጎጆ ፓኬጅ በ350 ብር ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#Euro2024 #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
የሐሳብ መድረክ 💬

https://hottg.com/+01D5gVgONq8yMjE8

" መብቷ ነው / መብቱ ነው ? "

ምንድነው መብቱ ነው ? መብቷ ነው ?

የሌላ ሰዎች ልጆች ሲሆኑ እንደፈለጉ ይሁኑ እድሜዋ/ው ነው ፤ መብቷ ነው / መብቱ ነው ... የእኛ ልጆች ሲሆን የምን መብት ነው ? ስነ-ስርአት ትያዝ / ይያዝ የሚል አመለካከት በማህበረሰባችን ውስጥ ትልቅ ቀውስ ይፈጥራል።

የኛ ልጆች ሲሆኑ ወደ ቤተክርስቲያን / ወደ መስጂድ የሌሎች ሲሆኑ " እድሜያቸው ነው መብታቸው ነው የፈለጉበት ይሂዱ " ማለት ፤ አልፈ ሲልም ከነሱ ጋር ባልተገባ ቦታ ዝቅ ብሎ መለዋል ጉዳቱ የከፋ ነው።

ሁሉም ነገር ገደብ ሲኖረው ጥሩ ነው።

ዛሬ የፈለጉበት ይዋሉ የተባሉ ልጆች ነገ የኛንም ልጆች ይዘው እንደማይጠፉ ምን ያህል እርግጠኞች ነን ?

ሁሉም ታዳጊ ልጆች ልጆቻችን ናቸው ብለን ወደ ጥሩ ቦታ እንምራቸው። ከተሳሳተ መንገዳቸው እናርማቸው። ነግበኔ ነው እንበል !

በናውስ (Nous) የሐሳብ መድረክ...እርሶም በውስጦ የሚመላለሰውን የሚናገሩበት ቦታ ያጡትን ጠቃሚ #ሐሳብ_ያጋሩ👇
https://hottg.com/+01D5gVgONq8yMjE8

@NousEthiopia
#ደመወዝ

° " ደመወዝ በአግባቡ #እየተከፈለን_አይደለም ፤ የሚመለከተዉ አካል ካላናገረን ማስተማር አንችልም " - የከምባ ወረዳ መምህራን

° " በየሶሻል ሚዲያ ' ደመወዝ አልተከፈለንም ' እያሉ ገጽታችንን የሚያበላሹትን በህግ እንጠይቃለን " - የዞኑ ትምህርት መምሪያ ሀላፊ

° " ያልተከፈላቸው መምህራን
#ስራ_ስለማቆማቸው መረጃ አለኝ " - የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር

ከሰሞኑ በጋሞ ዞን ከምባ ወረዳ መምህራን " ደሞዝ በአግባቡ እየተከፈለን አይደለም " በማለት ቅሬታቸዉን አሰምተዋል።

" ዞኑ ውስጥ ካሉት ሀያ ክላስተሮች ተለይተን ደመወዝ አልተከፈለንም " ያሉ መምህራን ስራ ማቆማቸውንና የሚመለከተው አካል ካላናገራቸው ስራ እንደማይገቡ በመግለጽ ቅሬታቸዉን አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ይህንን የመምህራን ጉዳይ ሰምቶ ይመለከታቸው ያላቸውን አካላት ማለትም ፥ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበርና የዞኑን ትምህርት መምሪያ አነጋግሯል።

የክልሉ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አማኑኤል ጳዉሎስ ምን አሉ ?

አቶ አማኑኤል ፥ " በዞኑ በከምባ ወረዳ #ለመምህራን እየተከፈለ ያለው ደሞዝ የተቆራረጠና አግባብ ባልሆነ መልኩ እየተፈጸመ ነው " ብለዋል።

አክለውም ፤ " በክላስተር ተቆራርጦ ከመክፈሉ ባለፈ በአንድ ትምህርት ቤት እንኳን ለጥቂት መምህራን ተከፍሎ ለአብዛኛው ደግሞ አለመከፈሉ ያበሳጫቸው መምህራን ስራ አለመግባታቸውን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች ስለመዘጋታቸው መረጃ አለን " ብለዋል።

የጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊው አቶ አብርሀም አምሳሉ ምን አሉ ?

አቶ አብርሀም ፤ " ያለኝ መረጃ ለመምህራን ደመወዝ በአግባቡ እየተከፈላቸው መሆኑን እና ስራም እየተሰራ መሆኑን ነው " ብለዋል።

" ይሁንና በየሶሻል ሚዲያው ላይ የአካባቢውን ገጽታ ለማጠልሸት በማሰብ ' ደመወዝ አልተከፈለንም ' እያሉ የሚንቀሳቀሱ አካላት ወሬውን እያናፈሱት ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" እነዚህ አካላት በህግ እየተጠየቁ ሲሆን ወደፊትም ይጠየቃሉ " ብለዋል።

ምን አልባት ያልተከፈላቸዉ መምህራን ካሉ የዲስፕሊን እና መሰል ችግር ያለባቸው ሊሆኑ ይችላሉ ሲሉ አክለዋል።

በተጨማሪም በአካባቢው ላይ ትምህርት መቋረጡን የሚመለከት መረጃ እንደሌላቸዉ በመግለጽ ችግር ተከስቶ ከሆነ እንደሚስተካከል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray በትግራዩ ጦርነት ምክንያት በየቦታው የተቀበሩ እና የተጣሉ ተተኳሾች፣ ፈንጂዎች አሁንም በሰው ህይወት ላይ አደጋ ማድረሳቸው ቀጥሏል። ዛሬ ዓርብ ግንቦት 16 / 2016 በተጣለ ተተኳሽ ባል እና ሚስት ህይወታቸው አልፏል። አደጋው ያጋጠመው በትግራይ ክልል ፣ በማእከላዊ ዞን ቆላ ተምቤን ምረረ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ሲሆን በተተኳሹ ምክንያት የባል ህይወት ወድያው አልፏል። የሟች ሚስት ወደ…
#Tigray🚨

በሓውዜን ወረዳ በተጣለ ተተኳሽ #የ4_ሰዎች ህይወት ጠፋ።
 
በትግራዩ ጦርነት ምክንያት በየቦታው የተቀበሩ እና የተጣሉ ተተኳሾች ፣ ፈንጂዎች አሁንም በሰው ህይወት ላይ አደጋ ማድረሳቸው ቀጥሏል።

ሰኔ 1/2016 ዓ.ም በትግራይ ክልል በምሰራቃዊ ዞን ፤ ሓውዜን ወረዳ ማይጎቦ ቀበሌ ገበሬ ማህበር በፈነዳ ተተኳሽ የ4 ወገኖች ህይወት #ተቀጥፏል

ከአራቱ የአደጋው ሰለባዎች ሶስቱ የአንድ ቤተሰብ አባል ናቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሓውዜን ወረዳ ኮሙኒኬሽን ባገኘው መረጃ  ፥ ሟቾቹ ከ 9 እስከ 14 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ገና ትንንሽ ልጆች ናቸው።

ከሰላም ስምምነቱ በኋላ የሰኔ 1/2016 ዓ/ም አደጋን ጨምሮ በትግራይ የተለያዩ ወረዳዎች በተጣሉ እና በተቀበሩ  ተተኳሾችና ፈንጂዎች ከ107 ሰዎች ላይ የሞት ፣ የአካል መጉደል አደጋ ደርሷል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
HTML Embed Code:
2024/06/09 18:44:12
Back to Top