TG Telegram Group Link
Channel: TIKVAH-ETHIOPIA
Back to Bottom
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ከአንድ ሳምንት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ሚሊኒያም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ ኃይል ጋር በነበረው የተኩስ ልውውጥ ወቅት ሁለት " የፋኖ አባላት (አንድ አመራር እና አንድ አባል) " ፦ - ናሁሰናይ አንዳርጌ - አቤነዘር ጋሻው መገደላቸው መነገሩ ይታወሳል። ከዛ በኃላ እናቶቻቸው በሀዘን ውስጥ ሆነው አስክሬን ለመውሰድ እንዳልቻሉና እላይ ታች እያሉ እንደሆነ ግን ምንም መፍትሄ እንዳላሀኙ…
ፎቶ ፦ በሚያዝያ ወር መጀመሪያ አዲስ አበባ ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ የተገደሉት ሁለት የፋኖ አባላት ቤተሰቦች አስከሬናቸውን ሳያገኙ ፍትሃትና ባህላዊ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ጎንደር ውስጥ ፈጽመዋል።

ሁለቱ ወጣቶች ማለትም ፦
- ናሁሰናይ አንዳርጌ
- አቤኔዘር ጋሻው በተኩስ ልውውጥ ከተገደሉ በኃላ ወላጆቻቸው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት አስከሬናቸውን አግኝተው ቀብር ለመፈጸም ፌደራል ፖሊስ ፣ አዲስ አበባ ፖሊስ ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ድረስ ጥያቄ ቢያቀርቡም ምላሽ ሳያገኙ 2 ወር ለሚጠጋ ጊዜ መጠበቃቸውን እና በመጨረሻም ተስፋ መቁረጣቸውን ተናግረዋል።

ዛሬ ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ጎንደር ውስጥ የናሁሰናይ አንዳርጌ አስከሬኑ በሌለበት በባህላዊ መንገድ በቤተሰብና በወዳጆች ፍትሃቱና የሽኝት ሥነ ሥርዓቱ በአባ ጃሌ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል።

አንድ የቤተሰብ አባል ፤ ለቀስተኛው ካለ አስከሬን በተካሄደው የስንብት ሥነ ሥርዓት ላይ ለመታደም ወደ ቤተ-ክርስቲያን እያመራ ሳለ የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች የናሁሰናይ ፎቶ እና ስም ያለበትን 2 ባነር በኃይል ተቀብለዋል። ከዚህ ውጭ ምንም የተፈጠረ ነገር የለም " ብለዋል።

የአቤኔዘር ጋሻው የሽኝት በተመሳሳይ ቤተሰቡ አስከሬኑ ባላገኘበት ሁኔታ ቀደም ብሎ መከናወኑን የቤተሰቡ አባላት ገልጸዋል።

#Credit - BBC AMHARIC

@tikvahethiopia
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹

➡️ " በሃገራዊ ምክክሩ #ሁሉም አካላት ካልተሳተፉ ምክክሩ ውጤት ላያመጣ ይችላል " - የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

➡️ " ያኮረፉ እና ጫካ የገቡ #ታጣቂዎች በምክከሩ እንዲሳተፉ ከሲቪል ማህበረስብ  እና ከተለያዩ ሀገራት #ኤምባሲዎች ጋር እየሰራን ነው " - ኮሚሽኑ

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት እየተደረጉ ያሉ ግጭቶች ቆመው ሁሉም አካላት ወደ ንግግር አንዲመጡ ጠይቋል

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጫካ የሚገኙት ታጠቂዎች በምክክሩ ላይ እንዲሳተፉ ከለላ እንዲደረግላቸው መንግስትን የመጠየቅ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ሰብሳቢ ደስታ ዲንቃ " በሃገራዊ ምክክሩ ሁሉም አካላት ካልተሳተፉ ምክክሩ ውጤት ላያመጣ ይችላል " ብለዋል፡፡

በጫካ ያሉ ታጣቂዎች በምክክሩ አንዲሳተፉ ለዚህ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ  ምክር ቤቱ የጠየቀ ሲሆን ፥ " ይህ ካልሆነ ግን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ስራ ውጤት ላያመጣ ይችላል " ሲል የጋራ ም/ቤቱ ስጋቱን ተናግሯል።

#ሌላው_ስጋት ብሎ ያነሳው ደግሞ የምክክር ኮሚሽኑ የተቋቋመበት አዋጅ  ግጭቶችን የማስቆም ሃላፊነት አልተሰጠውም ግጭት ሳይቆም በግጭት ውስጥ የሚደረግ ምክክር ደግሞ ውጤት ላያመጣ ይችላል ብሏል፡፡

የጋራ ም/ቤቱ ከጅምሩ ጀምሮ " በምክክሩ አንሳተፍም " ያሉ ፓርቲዎችን፣ በተለያየ ክልሎች ያሉ ታጣቂዎች በምክክሩ እንዲሳተፉ እንዲደርግ ኮሚሽኑን ጠይቋል፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ዶክተር ዮናስ አዳዬ ምክክሩ አሳታፊ እንዲሆን፣ ያኮረፉ እና ጫካ የገቡ ታጣቂዎች በምክከሩ እንዲሳተፉ ከሲቪል ማህበረስብ  እና ከተለያዩ አለም ሀገራት ኤምባሲዎች ጋር እየሰራን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

" ጫካ የገቡ አካላት በምክክሩ እንዲሳተፉ በመገናኛ ብዙሃን ተደጋጋሚ ጥሪዎችን እያደረግን ነው " ያሉት ዶ/ር ዮናስ " ሕጋዊ የሆነ መስሪያ ቤት ስለሌላቸው ጥሪ ለማድረግ ተቸግረናል፣ እዚህ ነን  አለን የሚሉ ከሆነ የተመካከሩ ጥሪ ወረቀት ይዘን ለመሄድ ዝግጁ ነን " ብለዋል፡፡

Credit - Sheger FM 102.1

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት #AddisAbaba በመንገድ ኮሪደር ልማትና በአስፓልት የማንጠፍ ስራ ምክንያት ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ የሚወስደው ዋናው መንገድ በከፊል ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ መዚህ መሰረት ፡- - ከለገሐር በመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ - ከእስጢፋኖስ በቀጥታ ወደ ቦሌ አየር መንገድ - ከኡራኤል በመስቀል አደባባይ ወደ…
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለበረራ ኤርፖርት የሚመጡ ሁሉ የመንገድ መዘጋቱን ታሳቢ እንዲያደርጉ አሳሰበ።

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ በመንገድ ኮሪደር ልማትና የአስፓልት ንጣፍ ስራ ምክንያት ወደ ቦሌ ዓለም-አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሚወስዱ አንዳንድ መንገዶች በከፊል ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድም መንገደኞች ለበረራ ወደ ኤርፖርት በሚሄዱበት ወቅት ይህን ታሳቢ በማድረግ ሊከሰት ከሚችል መዘግየት ራሳቸው እንዲጠብቁ አሳስቧል።

የሚዘጉት መንገዶች #የትኞቹ_ናቸው ? በዚህ ሊንክ ይመልከቱ ፦ https://hottg.com/tikvahethiopia/88048

#EthiopianAirlines

@tikvahethiopia
#OROMIA #PEACE

" የመንግሥት ወታደሮች ፣ ሌላም ፣ ንጹሃንም ዋጋ መክፈል የለባቸውም፤ ... ለሰላም ክፍት ነን ድርድሮችም እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን " - የኦሮሚያ ክልል መንግሥት

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አሁንም ቢሆን ያሉ ችግሮች #በሰላም እንዲፈቱ መንግሥት #ለድርድር ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል።

የክልሉ መንግሥት አመራሮች ከኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጋር በአዲስ አበባ እንደመከሩ ተነግሯል።

በምክክሩ ላይ የተገኙት የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ፕሬዜዳንት እና የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ታፈሰ ውይይቱ ልማትና ጸጥታ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ሲሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

በውይይቱ ፦

- የልማት ስራ ያለ ሰላም ውጤት አልባ እንደሆነ / ሰላም ለሁሉም ነገር መሰረት እንደሆነ ፤

- ሰው ሰርቶ የሚበላው ፣ ወልዶ የሚስመው ሰላም ሲኖር እንደሆነ አጽንኦተ ተሰጥቶበታል ብለዋል።

" ሰላም ለመንግሥት ብቻ የተተወ ስላልሆነ እንዴት ነው አብሮ መስራት የሚቻለው ? " የሚለውም መነሳቱን አስረድተዋል።

" መንግሥት እና ሸኔ የጀመሩት ድርድር ፤ በተለያየ ምክንያት አኩርፈው ጫካ የገቡ ነፍጥ ያነገቡ ጓዶች አሉ ፤ መንግሥት በሆደ ሰፊነት ዛሬ ነገ ሳይል እነዚህን አካላት ጠርቶ በጠረጴዛ ዙሪያ መነጋገር አለበት ይህ ሲደረግ ደግሞ ለሰዎቹ እውቅና ተሰጥቶ የህግ ከለላ ተሰጥቶ ነው ውይይት መደረግ ያለበት " የሚለውም መነሳቱን ገልጸዋል።

" በመንግሥት በኩል ' ዛሬም ቢሆን ክፍት ነው እንነጋገራለን ፣ ችግሮችን በጋራ ተነጋግረን እንፈታለን ' የሚል ምላሽ ነው የተሰጠን " ሲሉ ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ አሁንም ቢሆን የክልሉ መንግሥት በውይይት ያምናል ብለዋል።

" የመንግሥት ወታደሮች ፣ ሌላም ፣ ንጹሃንም ዋጋ መክፈል የለባቸውም፤ ሙሉ ትኩረታችን ወደ ሰላም ማምጣት ነው ያለብን። የፈለግነውን ነገር በአዳራሽ መወያይት ይቻላል። ጥረቶች ብዙ ነው ያደረግነው አሁንም ለሰላም ክፍት ነን እኛ 3ኛ ዙር ይሁን፣ 5ኛ ዙር ይሁን ፣ 10ኛ ዙር ድርድሮች እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን " ብለዋል።

#Ethiopia
#Oromia #VOA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#OROMIA #PEACE " የመንግሥት ወታደሮች ፣ ሌላም ፣ ንጹሃንም ዋጋ መክፈል የለባቸውም፤ ... ለሰላም ክፍት ነን ድርድሮችም እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን " - የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አሁንም ቢሆን ያሉ ችግሮች #በሰላም እንዲፈቱ መንግሥት #ለድርድር ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል። የክልሉ መንግሥት አመራሮች ከኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጋር በአዲስ አበባ…
ኦነግ እና ኦፌኮ በውይይቱ ተገኝተው ነበር ?

#አልተገኙም

" ውይይት መደረጉን የሰማነው እራሱ በሚዲያ ነው " - ኦፌኮ

በኦሮሚያ ክልል ይንቀሳቀሳሉ ከተባሉ ፓርቲዎች ጋር የክልሉ መንግሥት አድርጎታል በተባለው ውይይት ላይ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) #አልተሳተፉም

የኦፌኮ ዋና ፀሀፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ ለቪኦኤ ሬድዮ ፥ " ውይይቱ መደረጉን የሰማነው ከብዙሃን መገናኛ ነው። እንደ ግለሰብ ይሁን እንደ ተቋም የደረሰን ጥሪ የለም የኮሚኒኬሽን ክፍተቱ ከማን በኩል እንደሆነ አላውቅም " ብለዋል።

ኦፌኮ የክልሉ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል ቢሆንም ባለው ቅሬታ ሙሉ ተሳትፎ እያደረገ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

አቶ ጥሩነህ ፤ ለውይይት በም/ቤት ይሁን በመንግስት ጥሪ አልደረሰንም ብለዋል።

የኦነግ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለሚ ገመቹ በበኩላቸው ፤ ፓርቲያቸው በውይይቱ #እንዳልተሳተፈ ገልጸዋል።

" ለውይይቱ ጥሪ ሊደረግ ይችላል እኛ ግን የምንፈልገው በአንድ አካል አቅራቢነት የሚደረገውን ውይይት ሳይሆን ሁሉም በእኩልነት የሚሳተፍበትን ውይይት ነው። " ብለዋል።

" የምንፈልገው አንድ ሀገርን የሚያስተዳደር መንግሥት በሚሰጥህ ቦታ ተወስኖ መወያየት ሳይሆን እራሳችንን የመፍትሄ አካል ነን ብለን የምናይ አካላት በአንድ ላይ ሆነን በተመሳሳይ ድምጽ ተወያይተን ዘላቂ መፍትሄ የምናስቀምጥበት ካልሆነ ኦነግ በአንድ አካል ጥሪ የሚሳተፍበት መድረክ አይኖርም " ሲሉ ተናግረዋል።

የኦሮሞን ችግር የሚፈተው በእውነታ ላይ የተሰመሰረተ አካታች ውይይት እንደሆነ የገለጹት አቶ ለሚ ፤ ውይይት ሂደቱን ጠብቆ አካታች በሆነ መልኩ መከናወን አለበት አሁን ያለው አካሄድ ሂደቱን ያልጠበቀ ቅንነት የሌለው በአንድ አካል ብቻ ተጎትቶ እየሄደ ያለ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ም/ቤት ሰብሳቢ እና የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ፕሬዜዳንት አቶ ሰለሞን ታፈሰ ኦነግ እና ኦፌኮ ከውይይት መቅረታቸውን አረጋግጠዋል።

" በድረገጻችን ላይ ለቀናል፣ በዋትስአፕ ላይ ተለቋል። እንደምንሄድ ኮሚቴው ሲወስን ተለቋል። በአካል አነጋሬያለሁ የሚመለከታቸውን ኦሮሚያ የኢትዮጵያ እምብርት ናት እናተ ስለሚመለከታችሁ ለምን አብረን አንሄድም? ብዬ ነግሬያቸዋለሁ። ተጋብዘዋልም " ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

#Ethiopia
#Oromia #VOA
#OFC #OLF

@tikvahethiopia
ወጣትነት በዘህራህ ልዩ ከወለድ ነጻ የሴቶች ቁጠባ ሒሳብ ሲታገዝ፣ የስኬት ጉዞ ከመቼውም ይልቅ ይፋጠናል!

አቢሲንያ አሚን ዕሴትዎን ያከበረ!

የተለያዪ ጠቃሚ ምክሮችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ።
https://hottg.com/BoAEth

#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #አቢሲኒያአሚን
#ዘህራ #የሴቶችቁጠባ #የሁሉም_ምርጫ
#AmazonFashion

አማዞን ፋሽን ለተማሪዎች እንኳን ለመመረቂያ ቀናቹ አደረሳቹ እያለ በዚህ አመትም ለተመራቂ ተማሪዎች ልዩ ቅናሽ አድርገናል።

ኮት ብቻ 3 ሺ ብር ሙሉ ልብስ በ5 ሺ ና በ8 ሺህ፣ ሸሚዝ በ1200 ፣ ጫማ በ2200 ብር ብቻ ።

አድራሻ ፦ ፒያሳ የገበያ ኣዳራሽ ወይም ፒያሳ የድሮው ዳውንታውን ህንፃ ምድር ላይ። 

ስልክ ፦ 0920880443/ 0919339250

Telegram👉https://hottg.com/+AAAAAEc8iQJX1Zjgepjq1w
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray #TPLF የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የዛሬውን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔን አወደሱ። አቶ ጌታቸው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ሰላምን ለማጠናከር በትክክለኛው አቅጣጫ አንድ እርምጃ የተራመደ ነው ብለውታል። ዛሬ የሚኒስትሮች ም/ቤት ያሳለፈው " የኢትዮጵያ የምርጫ ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ…
#Update

ፓርላማው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ( #ህወሓት ) ዳግም ህጋዊ እውቅና ሊያገኝ የሚችልበትን / በድጋሚ እንዲመዘገብ የሚፈቅድለትን የአዋጅ ማሻሻያ አጽድቋል።

" የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነምግባር አዋጅን " የሚያሻሽለው የህግ ረቂቅ የጸደቀው በ2 የፓርላማ አባላት ተቃውሞ፣ በአንድ ድምጸ ተዐቅቦ፣ በአብላጫ ድምጽ ነው።

" በአመጽ እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበሩ " የፖለቲካ ፓርቲዎችን " በልዩ ሁኔታ " እንዲመዘገቡ የሚያስችለው የህግ ማሻሻያ፤ የፖለቲካ ቡድኖቹ ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶችን እና የምርጫ ቦርድን ኃላፊነት የዘርዘረ ነው።

የጸደቀው የአዋጅ ማሻሻያ ፥ " ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመጻ ተግባር ላይ ተሰማርቷል " በሚል " ህጋዊ ሰውነቱ እንዲሰረዝ " የተደረገው ህወሓት #በድጋሚ እንዲመዘገብ የሚያስችሉ አንቀጾችን በውስጡ ይዟል።

" አንድ የፖለቲካ ቡድን ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመጽ ተግባር ውስጥ የተሳተፈ እንደሆነ እና ይህንን ተግባር ማቆሙን እና ሕገ መንግስታዊ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን አክብሮ ለመንቀሳቀስ መስማማቱ በሚመለከተው የመንግስት አካል ከተረጋገጠ፣ የፖለቲካ ቡድኑ በልዩ ሁኔታ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ሊመዘገብ ይችላል " ሲል አዋጁ ደንግጓል።

#EthiopiaInsider
#TPLF

@tikvahethiopia
#USA

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሜክሲኮ በኩል ወደ አሜሪካ የሚገቡ ስደተኞችን ለመቆጣጠር ያለመ አዲስ እና መጠነ ሰፊ ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ዛሬ ይፋ እንደሚያደርጉ ተነግሯል።

ውሳኔው የአሜሪካ ኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት በየዕለቱ ከሚመለከቱት በሕገ ወጥ መንገድ የገቡ ተጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር በላይ አመልካቾች የሚቀርቡ ከሆነ ጥያቄያቸውን ሳይመለከቱ በቀጥታ ከአገር እንዲባረሩ ማድረግ የሚያስችል ሥልጣን ይሰጣል።

ይህም ድንበር ላይ ያሉ ባለሥልጣናት አሜሪካ የሚገቡ #ስደተኞች ቁጥርን እንዲገድቡ እንደሚያስችላቸው ተነግሯል።

ፕሬዝዳንት ባይደን ሥልጣን ላይ በቆዩባቸው ባለፉት 4 ዓመታት ውስጥ ከ6.4 ሚሊዮን በላይ ስደተኞች በሕገ ወጥ መንገድ ወደ አሜሪካ ለመግባት እንደሞከሩ ተነግሯል።

ይህም እስካሁን ከታየው ከፍተኛው ነው።

የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ፤ ባይደን አሁን ላይ በ1952 የወጣውን በአሜሪካ ጥገኝነት የማግኘት ሥርዓትን ለመገደብ የሚያስችለውን ሕግ ለመጠቀም እያሰቡ እንደሆነ ዘግበዋል።

212 (ኤፍ) በመባል የሚታወቀው ሕግ ወደ አሜሪካ የሚገቡ የውጭ ዜጎች " ለአገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም አስጊ የሚሆኑ ከሆነ " ፕሬዝዳንቱ " እንዳይገቡ ማገድ "  የሚያስችለው ነው።

#BBC
#USA #Immigration

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪው #ሰኔ_ወር 2016 ዓ/ም ወደ ሁለት የሀገር ውስጥ የበረራ መዳረሻዎች በረራ ይጀምራል። አየር መንገዱ #ከሰኔ_10_ጀምሮ ወደ ወለጋ ፣ ነቀምቴ በረራ እንደሚጀምር አሳውቋል። በረራው በሳምንት 4 ጊዜ እንደሚካሄድ ተገልጿል። ከዚህም ባለፈ ፥ በትግራይ ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየው ወደ አክሱም የሚደረገው በረራ ከሰኔ 1 ጀምሮ ዳግም እንደሚጀምር ታውቋል።…
ፎቶ ፦ የአክሱም አፄ  ዮውሀንስ አራተኛ  ኤርፖርት #በተያዘለት_የጊዜ_ሰሌዳ አገልግሎት መስጠት እንዲጀመር የሚያስችሉት የጥገና ስራዎች አሁን ላይ ወደመጠናቀቁ መሆናቸው ተነግሯል።

በትግራይ ጦርነት ከፍተኛ የሆነ ጉዳት የደረሰበት ኤርፖርቱ የጥገና ስራው ቀን እና ሌሊት እየተሰራ ነበር።

የጥገና ተቆጣጣሪ አካል የአውሮፕላን ማረፍያው የሚገባውን ጥራት በያዘ ደረጃ ስራው እየተሰራ መሆኑን ጠቁሟል።

በረራው እንዲጀመር በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ በረራው እንዲጀመር የማጠናቀቅ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ወደ አክሱም መደበኛ በረራ እንደሚጀመር ማሳወቁ ይታወሳል።

#Ethiopia #Tigray #Axum

Photo Credit - Tigray TV

@tikvahethiopia            
HTML Embed Code:
2024/06/04 11:39:24
Back to Top