TG Telegram Group Link
Channel: TIKVAH-ETHIOPIA
Back to Bottom
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ በኢትዮጵያ ታላቁ የጎዳና ላይ #ኢፍጧር ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለት ተከናውኗል።

Photo Credit : Abel Gashaw

#ኢፍጧር #ረመዷን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ራይ " ግጭቱ ከ20 ደቂቃ በላይ አልፈጀም፤ በግጭቱ የሞተ ሰውም የለም  " - በትግራይ ደቡባዊ ዞን የራያ ጨርጨር አስተዳዳሪ አቶ ግደይ ካልኣዩ " የአማራ ታጣቂዎች በትግራይ ግዛት ውስጥ የፈፀሙት ትንኮሳ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት  እንዲያስቆመው ተደርጓል " - የትግራይ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም የትግራይ እና አማራ ክልሎች የይገባናል ጥያቄ በሚያነሱበት…
#Update #ራያ

° “ ከያዙት ቦታ የሚገኘውን ኮስም 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ንብረቱ ዘርፈው ጭነውታል። አፍሪካ ህብረት ሁሉንም ታዝቧል ” - የአላማጣና አካባቢው አመራር

° “ ጉዳቱ በጣም ከፍ ያለ ነው። አጥንቱ ደቋል ” - የተጎጂ ቤተሰብ

በአማራ እና ትግራይ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ተቀሰቀሰ የተባለውን ተኩስ በተመለከተ በአማራ ክልል በኩል ሆነው ቃላቸውን የሰጡ አንድ የአካባቢ ከፍተኛ አመራር ከትላንት ወዲህ ያለውን ሁኔታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አብራርተዋል።

እኚሁ አመራር ፤ “ ዛሬ አፍሪካ ህብረት መጥተው ማን ስምምነቱ እንደጣሰ ተመልክተዋል። አፍሪካ ህብረት እያንዳንዱን ችግር አይተውታል ” ብለዋል።

“ ዛሬ ተኩስ የለም። የያዙት ቦታ አሁንም አለቀቁም። ከያዙት ቦታ የሚገኘውን ኮስም 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ንብረቱ ዘርፈው ጭነውታል። አፍሪካ ህብረት ሁሉንም ታዝቧል። መከላከያ ያለውን እውነታ አስረድቷቸዋል ” ሲሉ አክለዋል።

“ የሞተውን ዛሬ በክብር ቀብረነዋል። ማቹ ተፈራ ፍቃዱ ይባላል። የሁልግዜ ለምለም ቀበሌ ነዋሪ ነው። ቀብሩም ከቀኑ 7፡00 በጎልአጆ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል። ሪፈር የተላኩ አልተመለሱም ” ሲሉ ተናግረዋል።

በተኩሱ ጉዳት ደርሶባቸው ሪፈር ተጽፎላቸዋል ከተባሉት ሁለት ቁስለኞች መካከል የአንዱ ቤተሰብ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ ጉዳቱ በጣም ከፍ ያለ ነው። አጥንቱ ደቋል። በአላማጣ አዋሳኝ በኩል ድንበር ላይ ቆሞ እያለ ነው በእነርሱ (በህወሓት) በኩል ጥቃት የደሰበት” ብለዋል።

“ በጣም ከፍተኛ ጉዳት አለው ሁለቱም እጆቹ ከኋላውም ቀላል ጉዳት ደርሷል። ግን ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ሁለቱ እጆቹ ላይ ነው። ወደ ደሴ ሆስፒታል ሪፈር ተጽፎለት እንደገና ደሙ አልቆም ሲል ወልዲያ ሆስፒታል ከትላንት ማታ ጀምሮ እስከ ዛሬ (መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ/ም) 7፡00 ገብቶ ነበር። ከዚያ በኋላም ወደ ግል ክሊኒክ ገብቷል። ሁለቱም እጆቹ ላይ ስለሆነ በጣም ስቃይ አለው ” ሲሉ አክለዋል።

" በድንበራችን ላይ መጥተው ነው ጥቃህት ያደረሱት" ብለው፣ መንግሥት ለጉዳዩ ትከረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

የትግራይ እና የአማራ ክልል አዋሣኝ ቦታ የሚገኙ የስራ ኃላፊዎች በራያ በተፈጠረው ጉዳይ እርስ በእርስ እየተወነጃጀሉ ይገኛሉ።

በትግራይ ክልል በኩል ያሉ አመራሮች ሰሞነኛውን ተኩስ የከፈቱት የአማራ ክልል ታጣቂዎች እንደሆኑ ዛሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

" ግጭቱም ሆን ተብሎ  ፦
- የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ለማደናቀፍ
- የትግራይ ማህበረሰብ ተወካዮች ከጠቅላይ ሚንስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ያደረጉት ውይይትና የአማራ እና የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንቶች በፕሪቶሪያ ውል አተገባበር ዙሪያ የፈጠሩት መድረክን ተከትሎ 'ውሉ ተግባራዊ ይሆናል' የሚል ስጋት ስለፈጠረባቸው ነው " ብለዋል።

" አሁንም የአማራ ክልል ታጣቂዎች ለቀጣይ ትንኮሳ በመዘጋጀት ላይ መሆናቸው ደርሰንበታል " ብለዋል።

የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት ውል እንዲከበርና የአማራ ክልል ታጣቂዎች በኃይል ከያዟቸው የትግራይ አካባቢዎች እንዲወጡ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

እስካሁን ድረስ በሁለቱም በኩል በክልል ደረጃ ስለ ጉዳዩ ያወጡት መግለጫ የለም። የፌዴራል መንግሥትም ያለው ነገር የለም።

መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ልውውጦችን ሲያስተናግዱ በቆዩት በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ እና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች ውስጥ ካለፉት 3 ቀናት ወዲህ አንጻራዊ የሚባል #ሰላም መኖሩን የአካባቢውን ነዋሪዎች ዋቢ በማድረግ ቪኦኤ ዘግቧል።

በሰሜን ሸዋ ዞን ፤ የአጣዬ ከተማ አስተያየት ሰጭዎች ፣ በአካባቢው አንጻራዊ ሰላም መኖሩን አመልክተዋል። ለደኅንነታቸው ሲሉ ወደ አጎራባች ቀበሌዎች የተፈናቀሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ግን በአሳሳቢ ችግር ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡

በተመሳሳይ፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አንጻራዊ ሰላም መኖሩን ነዋሪዎች ጠቁመዋል።

አልፎ አልፎ ግን የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማ አመልክተዋል፡፡

አንድ የሰንበቴ ከተማ ነዋሪ ፥ " መንገድ ዝግ ነው መንቀሳቀስ አልቻልንም። የጅሌ ጥሙጋና የአርጡማ ፋርሲ ወረዳዎች ተቆራርጠናል። ተረጋግቷል የሚባለው በሁለቱም ወረዳዎች መንግሥት ሰላም አስፍኖ መንገዶች ሲከፈቱ ነው። አሁን መንገድ አልተከፈተም ሰውም ችግር ውስጥ ነው " ብለዋል።

ነዋሪዎች ዘላቂ የሆነ ሰላም እንዲመጣ የፌደራል መንግሥቱ መፍትሔ እንዲያፈላልግ ነዋሪዎቹ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ጥሪ አቅርበዋል።

ሰሞኑን በነበረው የተኩስ ልውውጥ የሰው ህይወት ጠፍቷል፣ የአካል ጉዳት ደርሷል፣ ንብረት ወድሟል።

@tikvahethiopia
" ቲክቶክ እንዲታገድ ለካቢኔው ጥያቄ አቅርቢያለሁ " - የኢራቅ ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር

የኢራቅ የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ሂያም አል-ያስሪ ' ቲክቶክ ' የተሰኘው የአጫጭር ቪድዮ ማጋሪያ መተግበሪያ እንዲታገድ ለሀገሪቱ ካቢኔ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተናገሩ።

" የኢራቅን የማህበራዊ ህይወት ትስስር እየሸረሸረው ነው " ያሉት ሚኒስትሯ የእግድ ጥያቄውን በቅርቡ ካቢኔው እንደሚያየውና እንደሚነጋገርበት ገልጸዋል።

" መተግበሪያው ማህበረሰቡን የሚጠቅም የረባ ትምህርታዊ ጠቀሜታ የለውም ሙሉ በሙሉ መዝናኛ ላይ ያተኮረ ከምንም በላይ የኢራቅን ህዝብ ባህል፣ እሴት አጠቃላይ ትስስርን የሚሸረሽሩ ይዘቶች የሚሰራጩበት ነው " ብለዋል።

የኢራቅ ፓርላማ እንዲህ ያለው መተግበሪያ እንዲታገድ ድጋፍና ትብብር ማድረግ እንዳለበት ጠቁመዋል።

@tikvahethiopia
" እየመጣችሁ ላላስፈላጊ እንግልት እንዳትዳረጉ " - የቤቶች ልማት እና አስተዳደር

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ለጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝግበው እየጠበቁ ያሉ ነዋሪዎች ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ በተለይ #በቲክቶክ እየተለቀቀ ባለ የተሳሳተ መረጃ ምክንያት ወደ ቢሮ መጥተው እንዳይንገላቱ ጥሪ አቀረበ።

ቢሮው ፥ " ' የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝግባችሁ እየተጠባበቃችሁ ያላችሁ ብቁ መሆን አለመሆናችሁን ባምቢስ በሚገኘው የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ 5ኛ ፎቅ መታችሁ እንድታዩ ' በሚል የተለቀቀው መረጃ የተሳሳተ ነው " ብሏል።

ተመዝግበው እየተጠባበቁ የምትገኙ ነዋሪዎችም ላተፈለገ እንግልት እንዳይዳረጉ ጥሪ አቅርቧል።

" ተመዝጋቢዎችም ሆነ ሌሎች ነዋሪዎች የተቋሙ ባልሆኑ ማህበራዊ ሚዲያዎችም ሆነ ግለሰቦች በሚያናፍሱት ወሬ እንዳትታለሉ " ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የአማራ ክልል ይፋዊ ምላሽ ሰጠ።

* " የዛቻና የጠብ አጫሪነት የሆነውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መግለጫ ተመልክተነዋል " - የአማራ ክልል

የአማራ ክልል መንግሥት ዛሬ ሀሙስ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ፤ " የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም የአማራ ክልል ተማሪዎች መማሪያ መጻህፍትን እንደሰበብ ተመርኩዞ ያወጣውን የዛቻ እና የጠብ አጫሪነት መግለጫ ተመልክተናል " ብሏል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ የአማራ ክልል የትምህርት ስርዓትን በማጣቀስ " የተሳሳተ ካርታ ተሰርቷል " ሲል ያወጣው መግለጫ በተሳሳተ ካርታ ወደ አማራ ክልል ተካተዋል ያላቸውን አካባቢ ሕዝቦች ታሪካዊ እውነታን፣ ተጨባጭ ማስረጃዎችን እና ነባራዊ ሐቅን የካደ፣ አሳሳችና  የጠብ አጫሪነት ፍላጎትን የተሸከመ መግለጫ ነው ሲል ገልጿል።

#በትናንትናው እለት ደግሞ ከነበረበት አካባቢ በመንቀሳቀስ የራያ አላማጣ ወረዳ ቀበሌዎችን በመያዝ ነዋሪዎችን በመግደልና በማሰቃየት ላይ ይገኛል ሲል የአማራ ክልል ከሷል።

(ሙሉው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአማራ ክልል ይፋዊ ምላሽ ሰጠ። * " የዛቻና የጠብ አጫሪነት የሆነውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መግለጫ ተመልክተነዋል " - የአማራ ክልል የአማራ ክልል መንግሥት ዛሬ ሀሙስ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ፤ " የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም የአማራ ክልል ተማሪዎች መማሪያ መጻህፍትን እንደሰበብ ተመርኩዞ ያወጣውን የዛቻ እና የጠብ አጫሪነት…
" ... ከለመደው አጓጉል የካርታ ፖለቲካ ጨዋታ እንዲወጣ እንመክራለን " - የአማራ ክልላዊ መንግሥት

የአማራ ክልል መንግሥት ባወጣው መግለጫ ፤ " የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር ለሀገሪቱ ቋሚ ቀውስ ምንጭ ከሚያደርጉት ተግባራት እንዲታቀብ " ሲል #አስጠነቀቀ

የክልሉ መንግሥት ፥ በአሁን ሰዓት የወልቃይት  ጠገዴ ፣ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች ህዝብ ለረጅም ዓመታት በ " ህወሓት " በኃይል ተገፍፎባቸው የነበረው የማንነትና ጥያቄና ራስን በራስ የማስተዳደር ነጻነት የተመለሰበት እንደሆነ ጠቁሟል።

ህዝቡም እንደማንኛውም የሀገሪቱ ሕዝብ ሁሉ የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚነት መብቱ ሊቀለበስ የማይችል ነው ብሏል።

" የፕሪቶሪያው የሠላም #ስምምነት ከመፈረሙ በፊት ጀምሮ የአማራ ክልል እንደሌሎቹ ዞኖችና የልማት ትሩፋቶች ሁሉ የአካባቢው ሕዝብም #በትምህርቱም_መስክ ተጠቃሚ እንዲሆን አድርጓል " ሲል ገልጿል።

ክልሉ ፤ እንደሌሎቹ አካባቢዎች የነዚህ አካባቢ ህፃናትም የመማር መብታቸው እንዲከበር ግዴታውን መወጣቱን ገልጿል።

የትምህርት ስርዓቱን ሰበብ በማድረግ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በአማራ ክልል ላይ ጥቃት ከመፈጸም የማይመለስ መሆኑን የሚገልጽ የጠብ አጫሪ መግለጫ እንዳወጣ ጠቁሟል።

ይህም " ካለፉት ድርብርብ ውድቀቶች ትምህርት አለመውሰድን ከማሳየት የዘለለ ፋይዳ አይኖረውም " ሲል ተችቷል።

የአማራ ክልል መንግሥት ፥ " ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሀገራችንን እና ሁለቱን ክልሎች ወደ #ቀውስ ከሚያስገቡ ተግባራት በመቆጠብ ከለመደው አጓጉል የካርታ ፖለቲካ ጨዋታ እንዲወጣና የህዝብን ፍላጎት ማዕከል ባደረጉ ውይይቶች ላይ እንዲያተኩር  እንዲሁም አንድ ሀገር ለመገንባት ለሚፈለገው ዘላቂ ሠላምና ለሕዝቦች አንድነት መጽናት በሚበጅ ሐሳብና ተግባር ላይ እንዲያተኩር እንመክራለን " ብሏል።

ሙሉ መግለጫ ፦ https://hottg.com/tikvahethiopia/86444

@tikvahethiopia
HTML Embed Code:
2024/04/29 14:27:31
Back to Top