TG Telegram Group Link
Channel: የፊልም ቋንቋ አካዳሚ / Film Language Academy👌
Back to Bottom
የተዋናይ መረጣ/Casting/
በኛ ሀገር የፊልም ስራ እንኳን በአሁኑ ጊዜ አስከ 200 ሺ የኢትዮጵያ ብር የሚከፈላቸው ደረጃ ኤ ተዋናዬች ሲኖሩ በቢ ደረጃና በሲ ደረጃ የምናስቀምጣቸው ተዋናዬች ከ100 ሺ እና ከ70ሺ ብር በታች አይከፈላቸውም ስለዚህ የምንሰራው ፊልም በጀት እቅድ ልንቀጥራቸው ካሰብናቸው ተዋናዬች ጋር መመጣጠኑን ማወቅ አለብን ይህውም ምን ያህል ተዋናይ በኤ ደረጃ ያሉ ተዋናዬችን እቀጥራሉሁ በቢ ደረጃስ ያለትን? በሲ ደረጃስ? አዳዲስ ተዋንያንስ? ረዳት ተዋንያንስ ምን ያህል አሉኝ? አጃቢ ተዋንያንስ? ለእያንዳንዱ ምን ያህል እከፍላለሁ በሚል በዝርዝር ሂሳቡን መስራት ይኖርበታል።

የሙያተኛ መረጣ/Selecting Crew/
የሙያተኛ መረጣም ሌላው በጀቱን እና የፊልሙንም ደረጃ የሚመጥነው መስፈርት ነው ምክንያቱም ሙያተኞቸ ደረጃቸው ከፍ ባለ ቁጥር በጀቱም ከፍ ይላል የፊልሙ ደረጃም በዛው ልክ ከፍ እያለ ይሄዳል። ስለዚህ ዳይሬክተሩ የብቃት ደረጃው ከፍ ያለ አርጌ ስኒማቶግራፈሩን መለስተኛ አቅም ያለው ባደርግ ያዋጣኛል? ወይም በግልባጭ እና እያሰባጠሩ የበጀት ልኬታቸውን በቅድሚያ በሚገባ አመጣጥኖ መስራት አስፈላጊ ይሆናል ማለት ነው።

ፕሮሞሽን(የማርኬቲንግ እና የማስታወቂያ ስራ) /Marketing & Distribution/
ይህ እጅግ ወሳኙ የፊልሙን ስራ የሚወስን የበጀት ክፍል ሲሆን ብዙዎች ፊልሙን ሰርቶ መጨረስ ብቻውን በቂ አድርገው ሲመለከቱ እናያለን ያ እጅግ በጣም የተሳሳተ ሃሳብ ነው። ለማርኬቲንግ ወይም የፕሮሞሽን ስራ ከአጠቃላዩ በጀት ከ20–40 % የሚደርሰውን ያህል መሆን አለበት፤ አንዳንዶች እንደውም እስከ 60% ይወስዱታል ስለዚህ ይሀንን ክፍል በሚገባ አስቦ የበጀት ምጣኔውን መስራት አስፈላጊ ይሆናል።
ከነዚህ ውጪ የበጀትን መጠን የሚለኩ ሌሎች ምክንያቶች የሚኖሩ ሲሆን ፕሮዲውሰሩ/አምራቹ ወደ ፉይናስ ማሰባሰብ ከመግባቱ በፊት በጥልቀት ሊሰራባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ናቸው።

★ ዋና ዋና በጀት የሚሰራባቸው የስራ ምድቦች/ክፍሎች/

የፊልም ፅሁፍ እና የማደበር ስራ(Script & Development work)
የቅድመ-ምርት ስራዎች(Pre-production costs)
ተዋንያን(Cast)
የቀረፃ ስፍራ(Location)
የፊልም ስራው ሙያተኞች(Film Crew)
አማካሪዎችና ልዩ ሙያተኞች(Advisor& spatial crew)
የቢሮና ስራ ማስኬጂያ(Office costs)
የምግብ እና መጠጥ ወጪዎች(Catering)
የጉዞ እና ማደሪያ ወጪዎች (Transportation & living)
የስቱድዬ እና የግንባታ ስራ(Studio & Building works)
የቀረፃ መሳሪያዎች(Shooting Matterials)
ቁሳቁሶች እና አልባሳት(Props & Custium)
የገፅቅብ፣የፀጉር ስራ(Make up & Hair stile)
ቪዥዋል እና ስፔሻል ስራዎች(Visual& Spatial Effect)
የድህረ ምርት ስራዎች(Post production works)
የገበያና ማስታወቂያ ስራ(Markating & Promotion)
ስርጭት ና እይታ (Distribution& screening)
ግብር፣ታክስና ሌሎች ህጋዊ ክፍያዎች(Tax and other legal payments)
ሌሎች ወጪዎች(other costs)
መጠባበቂያ(Contengency) ናቸው።

የበጀት ስራ አሰራር የራሱ የሆነ የወረቀት አሰራር ያለው ሲሆን ዋናው በጀት በሚገባ በተደራጃ መልኩ መሰራት እና የትርፍ ክፍፍል፣ ወጪቀሪ መሰል ዝርዝሮችን በመስራት ኢንቨስተሩ ሊያገኝ የሚችለውን የተጣራ ትርፍ ሊያሳይ በሚችል መልኩ ተሰርቶ መቅረብ ይኖርበታል።
3. ቅድመ-ምርት/Pre-Production/

አንዴ ስክሪፕቱ ተዘጋጅቶ በጀቱ በገንዘብ ከተደገፈ በኃላ ፣ ለቀረፃ/ለተኩስ ቀናት ለመጀመር የምንዘጋጅበት ይህ የቅድመ ምርት ክፍለ ጊዜ ይሆናል ማለት ነው ፡፡ በቅድመ-ምርት ደረጃ ፊልሙ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው በግልፅ የሚታይ መሆን አለበት፡፡ በፊልሙ ማምረቻ ውስጥ ዋና ሚናዎች ይገለፃሉ ፣ ተዋናይ ተዋናይ ገጸ-ባህሪያትን ይፈልጋል እና ቦታዎቹን ለማግኘት አሰሳ አለ ፡፡ የቅድመ-ምርት ስራ ደረጃ ቀላል የሚባል አይደለም እንደውም ለቀረፃው እና ፊልሙ ተጠናቆ እንዲወጣ መደላደሉ የሚሰራበት ዋነኛው የስራው መሰረት የሚጣልበት ጊዜ ነው መቼም በማንኛውም ስራ ላይ መሰረቱ ምን ያህል ከባድ እና አስፈላጊ እንደሆነ እንረዳለን።

በዚህም ምክንያት ይህንን ሥራ ለማከናወን ሙሉ ትኩረትን መስጠት ይፈልጋል ፡፡ ግልጽ ያልሆነ ማንኛውም ዝርዝር ጉዳይ በጠቅላላው ፊልም ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል ስለዚህ ነገሮች ዘርዘር ብለው መቅረብ እና መሰራት ይኖርባቸዋል። በዚህ የስራ ደረጃ ዳይሬክተሩ የፊልሙን ዘይቤ ለመግለጽ ከዋና ዋና የስራ ክፍሎች/ሚናዎች ጋር አብሮ ይሠራል ፡፡ ይህ ማለት ከሲኒማቶግራፊ ፣ ከፕሮዳክሽን ዲዛይን/አርት ዲዛይን፣ ከአልባሳት እና ከቀረፃ ስፍራዎች ማናጀሮች እና ወዘተ ጋር ማለት ነው ፡፡
ይህ የሚሆነው ታዲያ ፕሮዲውሰሩ/አምራቹ እና ረዳት ዳይሬክተሩ ሁሉንም የእቅድ እና የቀረፃ መርሃ ግብሮችን የሚፈጽሙበት ጊዜ ነው ማለት ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ የቅድመ-ምርት ጊዜዎች በቀረፃ መርሃግብር ላይ በመመስረት ይወሰናሉ። ለምሳሌ ፣ ፊልሙን ለመቅረፅ አንድ ወር የሚወስድ ከሆነ የቅድመ-ምርት/ፕሪ–ፕሮዳክሽን ጊዜ ተመሳሳይ የጊዜ ቆይታ ሊኖረው ይገባል - ያ ማለት ደግሞ አንድ ወር ቅድመ-ምርት ጊዜ ካለ የአንድ ወር የቀረፃ/የምርት ጊዜ ይኖራል ቢኖር ይመከራል ነገርግን ይህ ግድ አይደለም እንደ አምራቹ የአሰራር ሁኔታ አንዳንዴ የቅድመ ምርቱ ጊዜ የሚኖርበት ሁኔታ ይኖራል ፡፡

ቅድመ-ምርት/Pre-Production/ ፣ እንደ የፊልም ሥራው የተለያየ ባህሪ ሊኖረው ይችላል፤ በአጠቃላይ ግን እንደ አንድ የስራ ሂደት ፣ የተወሳሰበ እና በተለይ ከስቱድዬ ውጪ ለሚሰሩ ፕሮዲውሰሮች ወይም ዳይሬክተሮች በሌላው አለም ነፃ ፊልም ሰሪዎች ለሚባሉት ከባድ ሊሆን ይችላል። ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ የተረጋጋ ፣ ፍሬያማ የፊልም ቀረፃን ለማረጋገጥ ከተፈለገ በቅድመ-ምርት ሂደት ውስጥ መካተት ያለባቸውን ከዚህ በታች ያሉ ወደዘጠኝ የሚደርሱ የስራ ሂደቶችን ተከትሎ መስራት ይመከራል፤ እያንዳንዳቸው ሂደቶች የራሳቸውን የሥራ ምድቦች እና የአሰራር ክፍሎች አሏቸው።
የመጨረሺያውን የቀረፃ ስክሪፕት በእጆዎ ያድርጉ!
/Lock the Shooting Script/

ፊልሞች ከተሰሩ በኃላ አስማታዊ ሆነው የሚታዩ ቢሆኑም፣ ድንገት ከአየር ላይ ግን ተፈጥረው አይመጡም። የቅድመ -ምርት/Pre-Production/ ሂደቱ ከመጀመሩ በፊት እንኳን ፣ አንድ ጥሩ ፊልም መሆን የሚችል ሀሳብ ያስፈልግዎታል ፣ እና ያ ሃሳብ ብዙውን ጊዜ በትክክል እንዲሠራ ደግሞ የተስተካከለ ራዕይ/እይታም ያስፈልግዎታል ይህም ማለት ሃሳቡ በሚገባ ወደ ስክሪን ፕሌይ መለወጥ አለበት ። ከዛን በኃላ ደግሞ የመጨናነቅ ጊዜ ሲመጣ ያንን ጥሩ ተደርጎ የተፃፈ ስክሪፕት ማጠናቀቅ እና ወደ ቀረፃ ስክሪፕት መለወጥ ያስፈልጋል - ይህም ሙያተኞቹ ዳይሬክተሩ ፣ ሲኒማቶግራፈር እና ካሜራ ሠራተኞች እንዲሁም ለተዋናዮችና ሌሎች ሙያተኞች የሚያነቡት ተደርጎ ማለት ነው።

በርግጥ እዚህ ጋር መታወቅ ያለበት ስክሪፕቶች ሁልጊዜ እየተስተካከሉ የሚሄዱ ሲሆን የተወሰኑ ነገሮች ሌላውቀርቶ አንዳንዴ ሙሉ ትዕይንቶች በማንኛውም ጊዜ አርትዕዖት ሊደረጉ ፣ ሊታከሉ ወይም ሊሰረዙ ይችላሉ (አንዳንድ ጊዜ በድህረ-ምርት ውስጥ እንኳን ማለት ነው!) ነገር ግን በአብዛኛው የፊልሙ የቀረፃ ስክሪፕት ዳይሬክተሩ የመጀመሪያ የቀረፃ እርምጃውን በሚጠራበት ጊዜ ለቀረፃ ዝግጁ ሆኖ የተዘጋጀ መሆን አለበት።
የታሪክ ሰሌዳዎች እና የቀረፃ ዝርዝር እቅድ ሰነዶች!
/Redy your Storybored & Shooting plan list/

የታሪክ ሰሌዳዎች/ስቶሪቦርድ/ እና የቀረፃ ዝርዝሮች ከቀረፃ ስክሪፕቶች ጋር ጎን ለጎን ተያይዘው የሚዘጋጁ አስፈላጊ ተግባራቶች ናቸው። ይህ የሚጠቅመው ለዳይሬክተሩ እና ለሲኒማቶግራፊው የማጣቀሻ እና የፈጠራ እይታውን ሞዴል እና የቅድመተከተል አቅጣጫ ለመፍጠር እና ለማመላከት የሚዘጋጁ ናቸው። አንዳንድ ዳይሬክተሮች ቀድመው ምን ምን በእጃቸው መገኘት እንዳለበት የሚያውቁ እና የሚፈልጉትን በትክክል የሚያውቁ ናቸው ስቶሪቦርዱንም እራሳቸውን መሳል ቢችሉም ፣ አብዛኛውን ጊዜ ግን የታሪክ ሰሌዳ አርቲስቶች/ሰአሊያንን ታሪኩን ይበልጥ ወደ ሕይወት ለማምጣት ይቀጥራሉ። አንዴ ፊልሙ በስዕል መልክ በስቶሪቦርዱ ላየረ ከታየ-በጥቁር እና ነጭ ንድፎች ውስጥ እንኳን- ቢሆን ሁሉም የፊልሙ ሙያተኞች ሊያዩት በሚችሉት መንገድ ሕያው ሆኖ መታየት ይችላል፤ ይህም ለዳይሬክተሩ ራዕዩን በማሳየተረ ከዚህ በኃላ ያለውን የራሱን የፈጠራና የትርጎማ ትግሉ እንዲገባ ያስችለዋል ማለት ነው።
ትክክለኛዎቹን ሙያተኞች ይቅጠሩ /Find the right crew/

አንዳንዶቹ የፊልም ሙያተኞች ቀድሞውኑ ለፕሮጀክት አስባችሁ፣ አናግራችሁ አዘጋጅታችሁዋቸው ሊሆን ይችላል፤ ወይ ቀድማችሁ አብራችሁ ሰርታችሁ በሚገባ ሙያዉን የምታውቁት ሊሆን ይችላል፤ ሌሎቹ እንደ ስክሪፕትጸሐፊው እና የታሪክ ሰሌዳ አርቲስት ያሉ የሥራ መደቦች በስራው ሂደቱ መጀመሪያ ላይ ሊቀጠሩ ይችላሉ - በአጠቃላይ ግን መላውን የፊልሙን ስራ ቡድን ከቅድመ ዝግጅት በፊት ለማወቅ እና ለመቅጠር መሥራት አለብዎት። ከሁሉም በላይ እነዚህ ብዙ ተግባራትን የሚያከናውኑ ሴቶች እና ወንዶች ሙያተኞች ብቃት ያላቸው፣ ታዛዥ ፣ በቡድን መንፈስ የሚሰሩ ሙያተኞች መሆን አለባቸው ምክንያቱም የፊልም ስራ የቀረፃ ስራ ብቻ ሳይሆን እልም ያለ የትብብር እና የቡድን መንፈስ የሚፈልግ ስራ ስለሆነ ማለት ነው።
የመቼት አሰሳና ማረጋገጥ/Location Scouting& Lock/

የታሪክ ሰሌዳዎቹ ላይ የተሳሉትን አይነት የቀረፃ አከባቢዎች ማግኘት ቀጣዩ የስራ ሂደት ነው ወይም ደግሞ በተገላቢጦሽ የተገኘው የቀረፃ ስፍራ ላይ በመመርኮዝ ስቶሪቦርዱን መስራት ሊያስፈልግዎት ይችላል ፣ ስለሆነም የቀረፃ ስፍራዎቹን በጠቅላላ ቀደም ብሎ ማግኘት ቁልፍ ስራ ነው። ብዙ ፕሮዲውሰሮች/አምራቾች እና ዳይሬክተሮች ይህንን ስራ እየዞሩ እራሳቸው ማግኘት ይፈልጉ ይሆናል ፣ ነገርግን ብዙውን ጊዜ በጣም የተሻለው ነገር ለቀረፃ በታቀደው ስፍራ ዙርያ አእምሮ ውስጥ የተሳለውን ወይም ኦሪጅናልዎቹ ስፍራዎች ለስክሪፕትዎ ፍጹም ተስማሚ በሆነ ሁኔታ እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ የሚያውቅ ባለሙያ የመቼት አሳሽ/ሎኬሽን ስካውት መቅጠር ነው።

በስቱዲዮ ወይም በድምጽ መድረክ ውስጥ የሚቀረፅ ከሆነ ደግሞ ትክክለኛው ስቱድዬ ከመጀመርያ ማግኘት እና እርግጠኛ ሆኖ ከቀረፃ እቅድ ውስጥ ከማከተት በፊት በሚፈለገው ቀናት አለመያዙን ማረጋገጥ ያስፈልጋል- በቃ ልክ ለሠርግ አዳራሾችን እንደሚያሲዙት አድርገው ይያዙዋቸው! አንዳንድ ስፍራዎች አስፈላጊዎቹን ህጋዊ ፈቃዶች እና የወረቀት ሥራዎችን ለማካሄድ በቂ ጊዜ ስለሚፈልጉ በተለይ በቀላሉ የማይገኙ ቦታዎችን ቀደም ብሎ ማግኘትና ማረጋገጥ እንዲሁ በጣም አስፈላጊው ስራ ነው።
ትክክለኛውን በጀት ይፍጠሩ (እና በእቅዱ መሰረት ይጓዙ)
/Create a proper Budget( and stik to it)

የሚፈለጉትን የቀረፃ መሣሪያዎችን ማግኘት እና ለቀረፃው የሚፈለጉትን ሥፍራዎች በእጆ ማግኘትዎን ለማረጋገጥ አሁን በጀትዎን አጠናቆ መስራት ያስፈልጋል። አንዳንድ ጊዜ ይህ የባለሙያ ስራ ሊሆን ይችላል። በነገራችን ላይ ይህ የቅድመ-ምርት ስራጊዜ ብዙም አስደሳች የስራ ክፍል በጭራሽ አይደለም ፣ ግን ደግሞ ብዙውን ጊዜ እጅግ በጣም አስፈላጊው የስራ ጊዜ ነው። ስለዚህ እዚህ ጋር ሁሉንም የበጀት ጉዳዬች እቅድን አጠናቆ ማለፍ ያስፈልጋል።

የቀረፃ መሣሪያዎችን ይምረጡ/Select your gear/

የቀረፃ መሳሪያዎችን በቅድሚያ መርጦ መወሰን ያስፈልጋል በሚሜ ፊልም ነው የሚቀርፁት ወይስ በዲጂታል ካሜራ? በዲጂታልስ ሆኖ በምን አይነት ዲጂታል? በ4ኬ፣ በ6ኬ ወይስ ከዛ በላይ ያንን የሚያስተናግድ የቁስቁስ፣ የሙያተኛ የኤዲቲንግ አቅምስ አልዎት? ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ካገኙ በኋላ መሣሪያዎቹን አብዛኛውን ጊዜ ከቀረላ መሳሪያ ኪራይ ቤቶች ሄደው ለሚፈልጉት ቀን ቀጠሮ በማስያዝ በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ።
አስፈላጊ የወረቀት ጉዳዬችን ያስተካክሉ /Fix all Legal peper works/

አሁን ደግሞ የወረቀት ስራ ይከተላል ፤ ይህም ማለት አንዴ ምን ዓይነት የቀረፃ መሳሪያዎች እና የቀረፃ ስፍራዎች እንደሚፈልጉ ከታወቀ በኃላ እነዚህ አገልግሎቶች እና ኪራዬችን ህጋዊ የሚያደርጉ ፈቃዶች እና ኢንሹራንስ መሰል ወረቀቶች ዝግጁ መደረግ አለባቸው። ምናልባት አንዳንድ ስፍራዎች በመንግስታት ፍቃድ የሚሰሩ እንዲሁም አንዳንዶቹ የሕዝብ ንብረቶች ላይ ቀረፃ ለማካሄድ ፈቃዶች የሚያስፈልጋቸው ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳብዶቹ ደግሞ በግል ስምምነቶች ወይም የአካባቢው ባለንብረት/ባለስልጣን ስምምነቶች ያስፈልጋሉ - ሌላው ደግሞ አንዳንዴ በተለይም የቤት እቃዎችን ወይም ለየት ያሉ መሣሪያዎችን ማዘዋወር ወይም ከቀረፃ በኋላ መመለስ፣ ማሳመር፣ ማስተካከል፣ ግድግዳዎቹን እንደገና መቀባት ብቻ ብዙ አይነት ስምምነቶች ሊኖሩ ይችላሉ ፤ እነዚህ ጉዳዬች በሚገባ ቀድሞ መጨረስ ያስፈልጋል። ሌላው እኛ ሀገር ብዙም የተለመደ ባይሆንም እርስዎ ወይም ከሠራተኛዎ አባላት አንዱ በቦታው ወይም በተከራዩት የፊልም መሣሪያዎችዎ ላይ በድንገት ጉዳት ካደረሱ እራስዎን ለመጠበቅ እና ከኪሳራ ለመዳን ኢንሹራንስ ቀድሚ መግባቱ ይመከራል።
ትክክለኛውን ተዋንያን ያግኙ /Find the Right Cast/

ከዚህ በኃላ የመጨረሺያዎቹን ተዋንያን ላይ መወሰን አስፈላጊ ይሆናል - ይህም ምንም ያህል ተዋናዮችን በኦዲሽን ቅድመ እይታ ቢመለከቱም መጨረሺያ ላይ አንዳቸውን መርጠው መወሰን አለቦት። አንዳንደ በጭንቅላትዎ ውስጥ ለገመቱት ወይም ለገፀባህሪው ሚና ይስማማል ብለው የሚያስቡት ሰው ፍጹም ሰው ማግኘት ባለመቻሉ ልትበሳጩ ትችላላችሁ ይህ የሚጠበቅ ነው ፣ ወይም ምናልባት ሁለት እኩል ምርጥ ተዋናዮችን አግኝተው በሁለቱ መካከል ለመወሰን እየሞከሩ ጸጉርዎን እየነጩም ይሆናል፤ ያም ሆነ ይህ ግን አሁን መወሰን ግድ ይላል፣ ቀደም ብሎ ደጋግሞ ማየት እና ወደውሳኔ መዳረስ ያስፈልጋል የሚፈለገው ሰው ካልተገኘ ደግሞ ከአካባቢያችሁ ውጭ ብዙ ተዋንያንን ለማግኘት እንድትችሉ የተለያዩ የተዋናይ ወኪሎችን/Cast agent/ መቅጠር ለፊልማችሁ ገፀባህርይ ፍጹም የሆነውን ተዋንያን ለማግኘት እድልን ያሰፋሎታል።
ልምምድ፣ልምምድ፣ልምምድ /Rehearse, Rehearse, Rehearse/

አንዳንድ ጊዜ የሚፈልጉትን እና ለገፀባህሪዎ ፍፁም የተስማማ ተዋንያንን ማግኘት የፊልም ሰሪዉን በራስ መተማመንን ከፍ ሊያደርግ ይችላል፣ ይህ በራስ መተማመን ደግሞ ይበልጥ መተማመን እንዲኖራቸው እና በገፀባህርያቸው ላይ በጣም ብዙ ሃላፊነት እንዲጥሉ ያደርጋቸዋል። ተዋናዮች ልክ እንደ ሌሎች ሙያተኞች ዳይሬክተራቸውን ይፈልጋሉ፣ እና ከእነሱ ጋር አንድ ለአንድ ሆኖ መናበብ እና መስራት እንዲሁም ጠቅለል ባለ ሁኔታ ከአጠቃላይ ገፀባህርያት ጋር በአንድ ስብስብ መስራት የቅድመ-ምርት ሂደቱ አስፈላጊ የስራ አካል ነው።

የቀረፃ እቅድ ከመያዙ ከሳምንታት በፊት ተዋናዬቹ እና ዳይሬክተሩ በመሆን ከፍተኛ የልምምድ ጊዜ አስፈላጊ ነው እና ሌላው የሚለማመዱበት ጊዜ ደግሞ ካሜራው ለቀረፃ ዝግጁ በሚሆንበት ጊዜ የቅድመ ቀረፃ የመጨረሺያ ልምምድ ያደርጋሉ(ይህ እንግዲህ ተዋንያን ከግል አሰልጣኞቻቸው እና በግል ራሳቸው ከሚሰሩት የልምምድ ጊዜ ውጪ የሚደረገውን ልምምድ ሳያካትት ማለት ነው) ይህ ከቀረፃው በፊት በስተመጨረሺያ የሚደረገው ልምምድ ደግሞ ተዋናዬቹ እርስበርስ የሚኖራቸውን መናበብ እና እውነተኛ ኬሚስትሪ እንዲያዳብሩ እና እንዲያዋህዱ የሚረዳቸው ይሆናል።

እንግዲህ ይህ የቅድመ–ምርት የስራ ሂደት ውስብስብ ፣ ዘርፈ ብዙ ሂደቶች ያሉት ሲሆን ዋና ዋናዊቹ ግን እነዚህን ይመስላሉ ። ነገር ግን በአንድ የፊልም ስራ ሂደት ውስጥ ይህ የስራ ክፈል ወሳኙ እና በጥንቃቄ ሊሰራው የሚገባ መሆኑን ደጋግማችሁ ማስታወስ አለባችሁ።

ይቀጥላል…
#የፊልም ኮንፈረንስ ተሳተፉ!
ይህ Global Film Expression conference ከ10–12 ዲሴንበር የሚዘጋጅ ሲሆን ከ10 እስከ 12 ፊልም ሰሪዎችን እየሰሩ ባሉት ፕሮጀክት ላይ በመመርኮዝ ከአለምአቀፍ እውቅ ሙያተኞች ለጋር በማገናኘት ለ3 ቀን የሚቆይ የአንድ ለአንድ እና የቡድን ሙያዊ ውይይቶች ማስተር ክላስ፣ የልምምድ ልውውጥ የሚሰረግበት መድረክ ሲሆን አለምአቀፍ ኮኔክሽንና እንደያዛችሁት ፕሮጀክት አለምአቀፍ ግንኙነት እና የፋይናስ እገዛ ለማግኘት ጥሩ እድል ነው። ስለዚህ ያላችሁን ፕሮጀክት በየትኛውም ደረጃ ላይ ቢሆን ከ500 ቃላት ባልበለጠ አፅመታሪኩን/ሲንኦፕሲሱን/ ፕሮጀክቱ ምን እንደሚያስፈልገው በተለይ ስለስክሪፕት ዴቨሎፕመንት እና ፋይናስ ፍለጋ ላይ ከሆነ በመፃፍ አስከ ኦክቶበር 16 በምስሉ ላይ በተጠቀሰው አድራሻ አስገቡ! ተሳተፉ! መልካም እድል!
HTML Embed Code:
2024/04/29 10:37:59
Back to Top