#ወደ_ሮሜ_ሰዎች
ምእራፍ 9
ክፍል 57
መግቢያ:-በዚህ ምእራፍ ውስጥ
ከ ቁጥር 1-6 ቅዱሱ ሐዋርያ ጳውሎስ ለወገኖቹ እስራኤል ስለመጸለዩ
ከ ቁጥር 7-13 ብሉይ ኪዳን ለእስራኤል ተስፋ ስለመነገሩ
ከ ቁጥር 14-24እግዚአብሔር በምህረትም ሆነ በመዓት ላይ ስልጣን ያለው መሆኑን
ከቁጥር 25-26አሕዛብ የእግዚአብሔር ልጅ ስለመባላቸው
ከ ቁጥር 25-33 ከእስራኤል ብዙዎች ኦንደማይጸድቁ ስለመነገሩ
ሮሜ 9
1-2: ብዙ ኀዘን የማያቋርጥም ጭንቀት በልቤ አለብኝ ስል በክርስቶስ ሆኜ እውነትን እናገራለሁ፤ አልዋሽምም፤ ሕሊናዬም በመንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል።
ሐዋርያው ከማያቋርጥ ሀዘን ወይንም ከከፋ ሀዘን የተነሳ ጭንቀት ውስጥ መጨነቁን ያሳየናል።ይህ ሀዘን የሚመነጨው በሥጋ ዘመዶቹ የሆኑ እስራኤል በክርስቶስ ካለማመናቸው የተነሳ ይኸውም ለማያቋርጥ ስቃይ እንደሚጠብቃቸው ከማሰቡ ነው።ይህንንም ሀዘን ለቅዱሱ ሐዋርያ ሁሉን የሚመረምረው መንፈስ ቅዱስ ብቻ የሚያውቀው ነው።
ሮሜ 9 :3 በሥጋ ዘመዶቼ ስለ ሆኑ ስለ ወንድሞቼ ከክርስቶስ ተለይቼ እኔ ራሴ የተረገምሁ እንድሆን እጸልይ ነበርና።
ጳውሎስ ወገኖቹ እንዲያምኑ በብዙ ከመፈለጉ የተነሳ ራሱን ቤዛ እስከማድረግ ጸሎትን ይጸልይ ነበር።
ሮሜ 9:4 እነርሱ እስራኤላውያን ናቸውና፥ ልጅነትና ክብር ኪዳንም የሕግም መሰጠት የመቅደስም ሥርዓት የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና፤
እነሱ እስራኤላውያን ናቸው ማለቱ ሕዝበ እግዚአብሔር መሆናቸውን ሲናገር ነው።
ልጅነት ሲል እስራኤል የእግዚአብሔር ልጅ መሆናቸውን ሲነግረን ነው ከልጅም የበኩር ።ይህም ከመጽሐፍ ቅዱስ
ዘጸአት 4:22 ፈርዖንንም፦ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እስራኤል የበኵር ልጄ ነው፤
ኪዳን ማለቱ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ኪዳን መግባቱን ሲያመለክት ነው።
ዘፍጥረት 17: 7:ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘላለም ኪዳን አቆማለሁ፥ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።.......... ይቀጥላል።
@eotchntc
>>Click here to continue<<