#ወደ_ሮሜ_ሰዎች
ክፍል 56
ሮሜ 8: 35
ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?
ሐዋርያው የክርስቶስ ፍቅር ባመኑት ክርስቲያኖች ዘንድ ጥልቅ መሆኑን ነገረን።እነዚህ ሁሉ ዝቅታዎች ከሁሉ በላይ ከሆነው ከክርስቶስ ኢየሱስ ፍቅር ቸርነት እና ርህራሄ በታች ናቸውና
ሮሜ 8:36: ይህም እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው፦
“ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን።”
- መዝሙር 44:22 ስለ አንተ ሁልጊዜም ተገድለናል፥
እንደሚታረዱም በጎች ሆነናል።ሰው ክርስቶስን ሲቀበል ሲያምን ጠላት ብዙ መከራን ያመጣልና።
ሮሜ 8:37:
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
ምንም እንኳን መከራው ቢበዛ ኃያላን ኀይላቸውን ቢያበረቱ አሸናፊዎች የተባሉ ከጌታ ጋር ኅብረት የሌላቸው ጉልበተኞች ቢበረቱም ቅሉ ያመኑቱ ክርስቲያኖች ግን በጌታ ሁሉን ድል ያደርጋሉ።
- ሮሜ 8
38: ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥
39: ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።
የትኛውም ነገር ሰማያዊ ኃይላት ሆነ ምድራዊ ኃይላት ከክርስቶስ ቸርነት ፍቅር ወይም ክርስቲያኖች ከክርስቶስ ጋር ካላቸው ኅብረት የሚለያቸው ነገር አለመኖሩን ይህ የተወደደ ቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ ነገረን።
በረከቱ ይደርብን።
ይቀጥላል
@eotchntc
>>Click here to continue<<