#ወደ_ነው።
_ሰዎች
ክፍል 55 ሐ
ዕብራውያን 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ ይህም እንደዚህ ተዘጋጅቶ ሳለ፥ ካህናት አገልግሎታቸውን እየፈጸሙ ዘወትር በፊተኛይቱ ድንኳን ይገቡባታል፤
⁷ በሁለተኛይቱ ግን ሊቀ ካህናት ብቻውን በዓመት አንድ ጊዜ ይገባባታል፥ እርሱም ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ ስሕተት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም፤
⁸ ፊተኛይቱም ድንኳን በዚህ ገና ቆማ ሳለች፥ ወደ ቅድስት የሚወስደው መንገድ ገና እንዳልተገለጠ መንፈስ ቅዱስ ያሳያል።
ይህም የሚቀርበው ደም ካህኑ(ሊቀ ካህኑ) ስለ ራሱ ሆነ ስለ ህዝቡ ኃጢአት የሚለምንበት ወይም የሚያስተሰርይበት ማስተሰረያ ነው።
በብሉይ ኪዳን መሰውያውም አብዛኛው የቤተመቅደስ ዕቃ በ እንስሳት ደም ይረጭ ዘንድ
ግድ ነበር።
“እንደ ሕጉም ከጥቂቶች በቀር ነገር ሁሉ በደም ይነጻል፥ ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም።”
— ዕብራውያን 9፥22
በመሆኑም ካህኑ ደሙን ይረጭ ዘንድ ይገባዋል።
“ሊቀ ካህናትም በየዓመቱ የሌላውን ደም ይዞ ወደ ቅድስት እንደሚገባ፥ ራሱን ብዙ ጊዜ ሊያቀርብ አልገባም፤”
— ዕብራውያን 9፥25
ማስተዋል ያለብን ይህ ደም የጥጆችና የጊደሮች ላም ነው።የነዚህ ላሞች በቀደመው ኪዳን ነገሮችን የህዝቡን ኃጢአት ለማንጻት የዚህን ያክል ስልጣን ካላቸው።
የጌታችን ደም ደግሞ እንዴት ያነጻን ይሆን
ዕብራውያን 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ የኮርማዎችና የፍየሎች ደም በረከሱትም ላይ የተረጨ የጊደር አመድ ሥጋን ለማንጻት የሚቀድሱ ከሆኑ፥
¹⁴ ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን?
የክርስቶስ ደም ሰዎችን ከኃጢአት የዋጀ የሚዋጅ ንጹህና ከብር ከወርቅ የሚበልጥ ክቡር ነው።
“ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 1፥18-19
በቀደመው ኪዳን የእንስሳትን ደም የሚሰዋው ካህን
1.ሰው ብቻ የሆነ
2.ልመናን የሚያቀርብ እንጂ ልመናን የማይሰማ
3.በኃጢአት ብሎም በሞት የሚሸነፍ
4.ስለ ራሱ ኃጢአት መሰዋት ያለበት የሚሰዋው ደም ከራሱ ያልሆነ ነው።
ወደ ጌታችን ስንመጣ
1.ሰው ብቻ ያልሆነ ይህም ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ የሆነ(perfect God perfect Human)
ሰው በመሆኑ ይጸልያል
ማቴዎስ 26
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴⁴ ደግሞም ትቶአቸው ሄደ፥ ሦስተኛም ያንኑ ቃል ደግሞ ጸለየ።
⁴⁵ ከዚያ ወዲያ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጥቶ፦ እንግዲህስ ተኙ ዕረፉም፤ እነሆ፥ ሰዓቲቱ ቀርባለች የሰው ልጅም በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ይሰጣል።
አምላክ በመሆኑ ጸሎትን ይቀበላል ይሰማል።
“የናዝሬቱ ኢየሱስም እንደ ሆነ በሰማ ጊዜ፦ የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ማረኝ እያለ ይጮኽ ጀመር።”
— ማርቆስ 10፥47
2.ራሱን በመስቀል ላይ የተወደደ መስዋዕት አድርጎ ያቀረበ ነው
“ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ።”
— ኤፌሶን 5፥2
መስዋዕት አቅራቢ ደግሞ ራሱ ነው
“እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፥”
— ዕብራውያን 10፥12
እግዚአብሔር እንደመሆኑ እንደ እግዚአብሔርነቱ መስዋዕትን ተቀባይ ነው።
ክርስቶስ በግ ለተባሉ ልጆቹ በመስቀል በዕለተ አርብ ደሙን ያፈሰሰ የእግዚአብሔር ቅዱሱ ነው።
".......ለበጎቹ ቤዛ የተሰቀለ የናዝሬቱ ኢየሱስ አምላካዊ ደም እንጂ" እንዲል አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በ መጽሐፈ አርጋኖን 2:10
3.እንደ ብሉዩ ካህን በኀጢአት የማይሸነፍ ንጹሐ ባህሪ ነው።
“ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም።”
— ዕብራውያን 4፥15
ሞትን በፈቃዱ ቢሞትም በግርማና በኃይል በእግዚአብሔርነቱ ስልጣን ድል አድርጎ የተነሳ ነው።
“ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።”
— ሮሜ 1፥3-4
በነዚህ እና በሌሎች ምክንያቶች የክርስቶስ ደም ካህኑ በብሉይ ኪዳን ይሰራቸው የነበረውን የማንጻት ስራን ቢሰራም የቀደመው ደም ደካማ የሆነ ሲሆን ሁለተኛው ግን የክርስቶስ የሆነ ነው። ደሙ ይናገራል ሲባል ክርስቲያኖችን ከኀጢአት ለማንጻት የማይታክት ትኩስና የማይደርቅ ነው። በዚህም ሐዋርያው
የሚማልደው ማለቱ የደሙን አይቀሬ የሆኑ የማንጻት ሥራ ሲገልጽ ነው።
ይቀጥላል .....
@eotchntc
>>Click here to continue<<