TG Telegram Group Link
Channel: Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
Back to Bottom
• አላችሁ አይደል…? በዘህ ደግሞ እንቀጥል…?

"…ፐ ውበት ብሎ ዝም እኮ ነው። አዲስ አበባችን እንደስሟ አዲስ አበቤ ሆና የለም እንዴ? ሃኣ…?
"…አይኔን ተጠራጥሬ ፎቶውን አቅርቤ አፍጥጬ አየሁት… ምንም የተጻፈ ነገር አይታየኝም። እናንተስ የሚታያቸሁ ነገር አለ ወይስ ስታይል ነው…? 😂
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"…እሊህ አጋንንታሞችም ዐማራ ክልል ዘምተው ይሆን…? እንዲህ ዓይነቱ አጋንንት ግን በጩፋ ካራቴ ብቻ የሚወጣ አይመስለኝም። ደግሞ አይመስለኝም ነው ያልኩት።

• አጋንንታም…!
“…በከረጢትህ ውስጥ ታላቅና ታናሽ የሆነ ሁለት ዓይነት ሚዛን አይኑርልህ። በቤትህ ውስጥ ታላቅና ታናሽ የሆነ ሁለት ዓይነት መስፈሪያ አይኑርልህ። ይህን የሚያደርግ ሁሉ ክፋትንም የሚያደርግ ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ ይረዝም ዘንድ እውነተኛና ፍጹም ሚዛን ይሁንልህ፤ እውነተኛና ፍጹም መስፈሪያም ይሁንልህ። ዘዳ 25፥ 13-16

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
መልካም… እንደተለመደው ከምስጋና ቀጥሎ የምንሄደው ወደተለመደው ተናፋቂ ቃርያ በሚጥሚጣ ወደ ሆነችዋ ርዕሰ አንቀጻችን ይሆናል።

"…ትግራይ ውዝፍ ደሞዝ የለም። በደቡብ ለመምህራን የሚከፈል ደሞዝ ጠፍቶ መምህራን የቀን ሥራ ፍለጋ እየሮጡ የማስተማሩን ሥራ አቁመዋል። አንዳንድ መሥሪያ ቤቶች ደሞዝ አዘግይተው መክፈል ጀምረዋል። ዐማራ ክልል ለሠራተኛ ደሞዝ ለመክፈል "ነጠላ ዘርግቶ መለመን" ነው የቀረው። ባንኮች ለደንበኞች የሚከፍሉት ካሽ አጥሯቸው ተቸግረዋል። ብድር ማበደርም አቁመዋል። ሌሎች ክልሎች ደቅቀው ኦሮሚያን በሀብት ማንበሻበሹን ተያይዘዋል። ብሩ እነ በተለይ ጅማዎቹ እነ መንሱር ጀማል እጅ ሰተት ብሎ ገብቷል።

"…በኦሮሚያ ግን የኦቦ ሽመልስ ስንቄ ባንክ የካሽ እጥረት የለበትም። እንደ ጉድ ይታተማል። እንደ ጉድ ይበተናል። ህፃናት እጅ የወደቀች ሀገር እየማቀቀች ነው። ዶላር 120 ሲገባ ደግሞ አበቃ፣ አለቀልን።

"…ለማንኛውም የዛሬ ርዕሰ አንቀጼ ይሄ አይደለም። በሚታተመውና እንደ ጉድ ለኦሮሞ ስለተበተነው ገንዘብ አይደለም የማወራው። የዛሬው ርዕሰ አንቀጼም የእቡይ አሕመድን ቀጣይ ሴራ ማፍረሱ ላይ ነው የሚያውጠነጥነው። የዘገየሁትም ለዚያ ነው።

• አላችሁ አይደል ጉበዝ…?
"ርዕሰ አንቀጽ"

"…የጎንደር ፋኖዎችን ዕርቅና ወደ አንድ መምጣት፣ የሸዋዎቹ ፋኖዎች የእርቅ ሥርዓቱን ፈጽመው ነገር ግን ንብረትን በተመለከተ መቋጨት ያልቻሉበትን ጉዳይ በዚያም ምክንያት የሽምግልናው ጉዳይ ፍጻሜ ያለማግኘቱ አሁን የፈጠረውን ውጥረት፣ አጠቃላይ የሽምግልናውን ሂደት እና ውጣውረዱንም ሁሉ በተመለከተ እዚህና እዚያ የሚወራውን ሁሉ ለማጥራት የፊታችን እሁድ "ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር" በተሰኘው በመረጃ ቴሌቭዥን የቀጥታ ሥርጭት በሚተላለፈው መርሀ ግብሬ ላይ እነግራችኋለሁ። ከጎንደሮች መስማማት በኋላ  ቅር ያላቸው ጎንደሬዎች፣ የግንባሩም፣ የሠራዊቱም፣ የግንቦቴም ሰዎች እያየሁ ነው። አገዛዙም ከጎንደሮች አንድ መሆን በኋላ ያለ የሌለ ኃይሉን በማሰባሰብ ወደ ጎንደር በመላክ እየተፍጨረጨረ ይገኛል። ሁሉንም የፊታችን እሁድ በሰፊው እመጣበታለሁ።

"…ለዛሬ ግን አረመኔው የአቢይ አገዛዝ ቀጥሎ ስለሚያስበው ሴራና ቁጭ ብሎ ስለሚሸርበው፣ ስለሚጎነጉነው ትብታብ ቀኝ ትከሻዬን ስለሚሸክከኝ ቀጣይ እቅድ ለማውራት ልሞክር ነኝና በጥሞና አንብቡኝ። ተከታተሉኝ። የኦሮሙማው ብልፅግና ሁልጊዜ የሚያቅደው እለታዊ ዕቅድ ነው። ለሳምንት እንኳን የሚቆይ በመርህ፣ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ዕቅድ ማቀድ እንኳን አይችልም። ብቻ ዛሬን ሥልጣን ላይ አውሎ የሚያሳድረው ካገኘ፣ ለነገ ሌላ እቅድ አውጥቶ እግሩ ወደ መራው ሄዶ ወይ ሠርቶ፣ አልያም ሰርቆ፣ ወይ ደግሞ ለምኖ እንደሚበላ ምስኪን ሰው ነው የብልጽግናው ኑሮ። አምላኬ ሆይ የእለት አጀንዳዬን ስጠኝ። በዚህ ስሸነፍ የቱኛውን ካርድ ልምዘዝ እና ምን አልባት የማሸንፍበት አማራጭ ካለኝ ልሞክር ሲል ነው ሲቃዥ የሚያድረው።

"…በምሳሌ እንመልከተው። ለምሳሌ የአዲስ አበባው የእነ ፋኖ ናሁሰናይ ኦፕሬሽን ሲያስደነግጠው ብልፅግና ወዲያው የሚይዝ የሚጨብጠውን አጥቶ ህወሓት ላይ ሄዶ ነው የተለጠፈው። የህወሓት እና የኦሮሞ አክቲቪስቶች ሳይቀር የኦፕሬሽኑን ጀብድ አሟሙቀው ማውራት የምር አስደነገጠው። ህወሓት እንኳ ያልሞከረችውን ፋኖ እንዴት ሞከረው ብለው ማርገብገባቸው አቃጠለው። አስደነገጠውም። ለዚህ ነው ህወሓት በዐማራ ላይ ያላትን ነገር ስለሚያውቅ እያለከለከ ሂዶ የጠራት። ዐማራንም ያስወረራት። ደግሞ ጨነቀው። ህወሓት ከአላማጣ ራያ እንዳታልፍ፣ ከዐማራ ፋኖም ጋር ተጣምራ ወደፊት እንዳትገፋ ከመከላከያ እርዳታ ውጪ ወደፊት መግፋት እንደማትችል አሳይቶ ወደፊት እንዳትመጣ እዚያው አንቆ ያዛት። በዚህች እቅድ አሁን ተንፍሷል። ግን ደግሞ እንቅልፍ የለውም።

"…የአቢይ ብልፅግና በዚህም አያቆምም። ሌላ አጀንዳ ይከፍታል። ከሱማሌ ጋር ንትርክ ውስጥ ይገባል። አምባሳደር ያባርራል፣ አምባሳደሩም ይባረራል። እሱ ሱማሌን ለሁለት ቆርጦ ካርታ ሠርቷል። ሱማሌዎቹም አሁን በሚዘገንን መልኩ ከኢትዮጵያ ቆርሰው አዲስ ካርታ ሠርተው ለቅቀዋል። ይሄን አስመልክቶም የኦሮሞ ሰዎች በተደፈርን ስሜት መንጫጫት ጀምረዋል። ቀጥሎ ሱማሌ የኢትዮጲያ ኤንባሲ ህንጻ ላይ የቦንብ ጥቃት ፈጸመች፣ አልሸባብ እና ሱማሌ አንድ ላይ ተጣምረዉ ኢትዮጵያን ለመውጋት ተስማሙ፣ ሱማሌ የኢትዮጵያን መሬት ይሄንን ያህል ኪሜ ገብታ ያዘች በማለት ማስጮህ ይጀምራል። ምን አልባት ከዚህ ከፍ ያለ የራሱን ሸኔ ፊታቸውን ሸፋፍኖ አልሸባብንም አስመስሎ በባሌ አካባቢ ክርስቲያኖችን ይገድል እና የእምነት ጦርነት የማስነሳት ሴራም ሊሠራ ሁሉ ይችላል።

"…አልሸባብ በኢትዮጵያ ገብቶ በባሌ ውስጥ እንዳለ ያስወሩት የኦሮሞ አክቲቪስቶች ናቸው። አልሸባብን እንደ ሃይማኖት ስላዩት የኦሮሞ እስላሞችም የባሌውን አልሸባብ በገፍ በመቀላቀላቸው ክርስቲያኖቹ እነ ጉማ ሳቀታ ጭምር አደገኛ አዝማሚያ በማለት ሲቃወሙት ታስታውሳላችሁ። እናም ያ አልሸባብ የተባለው ራሱ ኦነግ ሽሜ ሊሆን ሁላ ይችላል። ስለዚህ የእለት አጀንዳ ፈጥሮ ትኩረት ለማስቀየስም መንደፋደፉ ስለማይቀር ሁሉም ሰው ሊነቃበት ይገባል። የአቢይ ብልፅግና እስኪወገድ ድረስ ዘግናኝ ጭፍጨፋዎች ያሉበት አዳዲስ አጀንዳዎች እየፈበረከ ሊያከፋፍል ስለሚችል ሊያስደነግጥ አይገባም።

"…ሌላው ዐማራው በጀመረው በራስ አቅም በመተማመን መንገድ መዝለቅ ነው ያለበት። ዐማራው የትግሬን አክቲቪስቶች ሙገሳና መደነቅ እየሰማ መደንዘዝ የለበትም። የትግሬና የኦሮሞ አክትቪስቶች ውሎአቸውን ማየቱ ብቻ በቂ ነው። በዩቱዩባቸው ሲወያዩ፣ ሲደሰኩሩ የሚውሉት በሙሉ የዐማራ ጠላቶች፣ የትግሬና የኦሮሞ ነፃ አውጪ ነን ባዮች መሆናቸውን ስታይ መጠርጠር አለብህ። ሁለቱ ለጋራ ዓላማ ይደማመጣሉ፣ ዋና ታርጌት ጠላታቸው ይታወቃል። ዐማራው ነው። ድንገት እግር ጥሎ ላያቸው መንግሥትን ይወቅሳሉ። ነገር ግን ደግሞ ሸኔን ይደግፋሉ። ትግሬዎቹ ዐማራን የማሸነፊያ ዋነኛ መንገድ አድርገው የሚጠቀሙት በለመዱት ማታለል፣ ተለሳልሶ በመጠጋት የለዘቡ ቃላቶችን በመጠቀም፣ በማዘናጋት ውዳሴ በስሱ በማቅረብ ማጃጃልን ነው። በአዝማሪ ግጥም ሲኮፈስ የሚውል ዐማራን በማማለል ማደንዘዝ ይፈልጋሉ። እውነታው ግን ሌላ ነው። መርዞች ናቸው።

"…የዐማራን ፋኖ ሲያወድስ የምታየው ስታሊን የዐማራ ፋኖን በጠላትነት ፈርጆ ከአገዛዙ እኩል ሊዋጋው የሚፍጨረጨረውን ኦነግ ሽሜን ሲደግፉት፣ ሲያወድሱት፣ ሲሟገቱለት ታያለህ። ይሄ የትግሬ አክቲቪስት ፍጥጥ ያለ ስግጥና የሚታይበት እባብነታቸው ነው። በእነርሱ ብቻ እባብነቱ ቢቀር መልካም ነበር። የትግሬዎቹ አክቲቪስቶች ይሄንኑ እባብነት፣ መርዝ በጉንጭ ደብቆ መንቀሳቀስን እንደ ምርጥ የትግል ስልት ቆጥረው የኦሮሞቹንም አክቲቪስቶች በማሰለሰጠን በተመረጡ ቃላት ለነሱ በሚመች መንገድ ፋኖን እንዲያደንቁ ሲያስደርጉ ታያላችሁ። ይታያችሁ ኦነግ ሽሜ ፋኖን ሲያደንቅ።

"…የጠላት ምክር አይጠቅምም። አጥፊህም ነው። ይህን በተመለከተም መጽሐ ሲራክ እንዲህ ይለናል። "…መካር ሁሉ ይመክራል፤ ነገር ግን ራሱን ይጠቅም ዘንድ የሚመክር አለ። ከሚመክርህ ሰው ልቦናህን ጠብቅ። ስለ ራሱ ይመክርሃልና፤ ይወድድህም ዘንድ አስቀድመህ ፍላጎቱን ዕወቅበት። ገንዘብህን የሚያጠፋብህን ነገር ያመጣብሃል፥ በጎ ነገር አደረግህ ይልሃል፤ በተቸገርህም ጊዜ አይቶ ይስቅብሃል። ከሚጠባበቅህ ሰው ጋር አትማከር፤ ለሚመቀኝህም ሰው ነገርህን ሰውር።" ይልሃል። ለእኔ የወያኔና የኦነግ ምክር ለዐማራ ፋኖ አጥፊው ነው ባይ ነኝ። የኦነግና የወያኔ ብቻ ሳይሆን ራሱ በዐማራው ትግል ውስጥ የተሰገሰጉቱ ክፉ መካሪዎች ሁሉ አይጠቅሙትም እና ከውስጥም ከውጭም ጠላት በማራቅ ይጠበቅ።

"…ዐማራ "ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ የእናትህንም ሕግ አትተው፤ ለራስህ የሞገስ ዘውድ ለአንገትህም ድሪ ይሆንልሃልና።" ምሳ 1፥8። የተባለው የባዕድ፣ የጠላት ሳይሆን የወዳጅ፣ የእናትና የአባቱን ምክር እንዲሰማ ነው። እንዲህ ዓይነቱ ምክር ከእግዚአብሔር ነው። "የጥበብ፥ የማስተዋል፥ የምክር፥ የኃይል፥ የዕውቀትና የእውነት መንፈስ ከእግዚአብሔር ነውና። ኢሳ 11፥2። የሚገርመው ነገር እግዚአብሔር የሽማግሌዎችን ምክር ያውቃል። ኢዮ ፲2፥20። ብዙ ጊዜ በሐሰት፣ በተንኮል የተሸረበ፣ የተመከረ ምክር ፈራሽ ነው። "የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህ ምክር አይጸናምና አይሆንም፤» እንዲል፦ የማይጸናውንም ምክር እርሱ ያውቃል። ኢሳ 7፥7 …👇 ከታች ይቀጥላል…
👆ከላይኛው የቀጠለ "…በቀደም እለት በጎንደሮች የሽምግልና መድረክ ላይ የታላቁ ደብር የቅዱስ ላሊበላ አስተዳዳሪ የነበሩት እና አሁን በአሜሪካ የሚገኙት አባ ጽጌ ሥላሴ ምክርን በተመለከተ ያስተላለፉትን ግሩም ቃል እዚህ ጋር ልጥቀስ። አባ ምክር ሲባል ከራስ ጥቅም አንፃር ብቻ የሚመክርም ስላለ እሱን ተመካሪው ማመዛዘን እንዳለበት መክረው ይኽንን ከመጽሐፍ ቅዱስ ኩሲን እና አኪጦፌልን ጠቅሰው እንደነዚህ ዓይነት ብዙ ሰዎች አሉና ተጠንቀቁ በማለት ያስተላለፉት መልእክት ሊያዝ ይገባል። "…አኪጦፌል የንጉሥ ዳዊት አማካሪ ነበር። ነገር ግን ልጁ አቤሴሎም አባቱን ንጉሥ ዳዊትን ባሳደደው ጊዜ፦ ከአቤሴሎም ጋር ሆኖ ክፉ ምክር ይመክረው ነበር። 2ኛ ሳሙ 15፥12፤ 17፥1-23 ያንብቡ። በሌላ በኩል ደግሞ የተሻለ መካሪም ሲመሰከርለት እናያለን። “…አቤሴሎምና የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ። የአርካዊው የኩሲ ምክር ከአኪጦፌል ምክር ይሻላል አሉ። እግዚአብሔርም በአቤሴሎም ላይ ክፉ ያመጣ ዘንድ እግዚአብሔር መልካሚቱን የአኪጦፌልን ምክር እንዲበትን አዘዘ።” 2ኛ ሳሙ 17፥14። አይደለም የወያኔና የኦነግ አክቲቪስቶች ምክር እናትም፣ ሚስትም ክፉ መካሪ ሊሆኑ እንደሚችሉ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። "…የሃያ ሁለት ዓመት ልጅ አካዝያስም በነገሠ ጊዜ፦ ጎቶልያ የተባለች እናቱ ብዙ ጊዜ ክፉ እንዲያደርግ ትመክረው ነበር። 2ኛ ዜና 22፥1። ንጉሥ አክዓብ ናቡቴን አስገድሎ ርስቱን የነጠቀው በሚስቱ ምክር ነው። 1ኛ ነገ 2፥1-16። ስለዚህ ፋኖ ከክፉ መካሪዎች ሁሉ ራሱን ሊጠብቅ ይገባል።

"…የአቢይ አማካሪዎች ከኦርቶዶክስ ዳንኤል ክብረት፣ ከጴንጤ እነ ምህረት ደበበ፣ ከእስላሞችም ነፍ ኡስታዞች ናቸው። የሕዝቡን ሥነ ልቦና የሚያውቁ፣ ጠንቅቀው የተረዱ ናቸው። የሃይማኖት ሰባኪ አማካሪ ሲሆን ስለ ፖሊሲ፣ ስለ ቴክኖሎጂ አይደለም የሚያማክረው። የጎንደር፣ የሸዋ፣ የወሎ፣ የትግራይ፣ የጎጃም፣ የወለጋ፣ የአፋር፣ የአሩሲ፣ የባሌ፣ የሱማሌ፣ የጋምቤላ፣ የጉራጌ፣ የወላይታ፣ የሲዳማ፣ የከንባታ፣ የሐረሪ ወዘተ ሰው ምን ቢያደርገው፣ ምን ቢሰብከው ልቡ ወከክ እንደሚል ነው። ለዚህ ነው አቢይ አሕመድ በየክልሉ በሄደ ቁጥር የክልሉ ነዋሪ ብቻ መስማት የሚፈልገውን እየነገረ ሲያስጨበጭብ፣ ጮቤ ሲያስረግጥ የሚታየው። ዐማራን እንዲህ፣ ትግሬን እንዲያ፣ ኦሮሞን እንዲህ ካልከው፣ ከሸነገልከው በቃ ይገዛልሃል ብለው ነው የሚሰብኩት። አቢይም የእነሱን ምክር ይዞ ነው ትግሬን ሞተር፣ ዐማራን ጎማ፣ ኦሮሞን መሪ፣ ሱማሌን ማርሽ፣ ደቡብን ስኮፒዮ ወዘተ እያለ ጮቤ የሚያስረግጠው። ሕዝብ ደግሞ የተነገረውን አይረሳም። አቢይ "ነዳጅ ተገኝቷል። ከነገ ጀምሮ ለውጭ ገበያ ይቀርባል" ብሎ ዐውጆ እስከአሁን ወፍ የለም። ለጉራጌ ሆስፒታል እሠራለሁ ብሎ ይኸው 6 ዓመት ሆነው የውኃ ሽታ ነው የሆነው። ለዐማራማ የገባው ቃል አይቆጠርም። ልክ እንደ ብአዴን መሰረት ድንጋይ የትየለሌ ነው።

"…ቀድሞ መንቃት። ሱማሌና አፋር ጦር ከመማዘዛቸው በፊት ቆም ብለው ማሰብ፣ መመካከር። ደቡብ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ ላይ የአቢይን አገዛዝ አጀንዳ ይዞ ከመዳከር፣ ከመፈሳፈስ፣ ደምም ከመፋሰስ አስቀድሞ ቆም ብሎ መመካከር። የኦነግና የወያኔን ምክር አለመስማት፣ አለመቀበል። መጀመሪያ ትግሬ ደቅቋል፣ ቀጥሎ ዐማራ እየተናነቀ ነው። ከዐማራ ቀጥሎ አዲስ አበባ እየፈረሰ እየጸዳም ነው። አፋርና ሱማሌ እያረፉ እየተጠዛጠዙ ነው። ሐረሪ በኦሮሞ ተውጧል። ድሬደዋ ከሱማሌ እየጸዳ ነው። ጉራጌ ብዙ ወረዳዎቹ በኦነግ ሽሜ ተይዘዋል። ሲዳማ በኦነግ ሸኔ እየተቀጠቀጠ ነው። ጋምቤላም በሸኔ እንዲያዝ ተደርጓል። ቤኒሻንጉል ውጥረት ላይ ነው። ዐማራ ከትግሬ በፈለጋቸው ጊዜ እንዲጋደሉ ድግስ ተደግሷል። ከኤርትራም፣ ከሱማሌም አይቀርልንም ብልፅግና ሲያናክሰን። ሁለቱም ሱዳኖች አይሞክሩንም አይባልም። አሁንም ቢሆን መሬታችንን ኦሮሙማው አስወስዷል።

"…ብስል፣ ሙክክ በሉ። ጥሬ አትሁኑ። ንቁ ሁኑ። ቆፍጣና፣ ተጠራጣሪም ሁኑ። ዥሎች አትሁኑ። ዥልጥ፣ ፋራ፣ ሰገጤ አትሁኑ። የክፍለ ሀገር ልጆች ከበሻሻና ከማሻ፣ ከደንበጫ፣ ጃናሞራ እና ከመተሃራ፣ ከመቄት እና ከዋጀራት፣ ከሞላሌና ከባሌ፣ ከሰላሌ፣ ከደምቢዶሎና ከከክልአተ አውላሎ ከጊንጪና ከወንጪ መጥተው 4 ኪሎም ገብተው አንተ አራዳ ነኝ፣ ብልጥ ነኝ ባዩን አናትህ ላይ ጥሬ ካካቸውን እንዲዘፈልሉ አትፍቀድ። አናትህንና ቅርሶችህን፣ ትዝታህን ሲያፈርሱት እያየህ አትብሰልሰል። ሴራቸውን ቀድመህ አንተም አፍርስ። የሸኔን እገታ ፈርተህ ላይቀር መሞት ታሪክህን አታልከስክስ። ሰምተሃል የአቢይ ብልፅግናን ሴራ ከወዲሁ አፍርስ። ያኔ እኮ ዘመዴ ተናግረህ ነበር እያልክ በኋላ ላይ መሃረብ ይዘህ አታልቅስ። አታስለቅስ።

• ፋኖ ይልቅ ክረምት ሳይገባ አዲስ አበባን ጎብኛት።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው ከራየን ወንዝ ማዶ…!
መልካም… አሁን ደግሞ ተራው የእናንተ አስተያየት የሚነበብበት ሰዓት ነው።
🔥 መረጫጨት ልጀምር ነው…

• ላምጪው ይከፈል ዘንድ ሕግ ያስገድዳል።

"…አሁን በሸዋም፣ በጎጃምም፣ በጎንደርም፣ በወሎም ላሉት ፋኖዎች ለመከፋፈላቸው ትልቁን ምክያትና ዋነኛውን ነቀርሳ ወደ መዋጋቱ ለመግባት እገደዳለሁ። አቶ ሽመልስ ለገሰ አድራሽ ፈረስ ነው። ከዚያ የዘለለ ሙያም፣ ብቃትም፣ አቅምም የለውም። እኔ ከሽመልስ ጋር አይደለም አፌን የምካፈተው። እኔ ከዋነኞቹ የሽመልስ ጋላቢዎች ጋር ነው የምጠዛጠዘው።

"…ኤልያስ ክፍሌ በሀብታሙ አያሌው፣ በኢየሩሳሌምና በሽመልስ ተፈራ፣ በኢትዮ 360፣ በግምባሩና በሕዝባዊ ሠራዊቱ አይደለም ሊሰደብ ሊዋረድ ቀርቶ በክፉ አይን የሚታይ ሰው አልነበረም። ኤልያስ ክፍሌን የማውቀው ከፌስቡክ እና ከዩቲዩብ ተባርሬ ቴሌግራም ላይ ብቻ በነበርኩበት ጊዜ ለምን ቴሌቭዥን ላይ አላወጣህም ብሎ የአየር ሰዓት የሰጠኝ ጊዜ ነው። በአካልም ሁለት ቀን ነው መልኩን እንኳ ያየሁት። ከልጅነቴ ጀምሮ ግን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ የነበረውን ተጽእኖ ሳነብ ነው የኖርኩት። ስለብዙ ነገር ኤልያስን በማግኘቴም ፈጣሪዬን አመስግናለሁም። በዚህ አጋጣሚ በሁሉ ሰው ፊት እጅግ አክባሪው እንደሆንኩም መግለጽ እፈልጋለሁ።

"…መረጃ ቲቪን በነፃ እየተጠቀሙበት ቆይተው መረጃ ቲቪን ለማፍረስ እነ ሀብታሙ አያሌው የሄዱበትን ርቀት የሚያውቅ ያውቀዋል። በፋኖ እና በዐማራ ስም በሚሰበሰብ ዶላር ኑሮውን የመሠረተ አቀንጭራ ሁላ የተለየ አደረጃጀት መጥቶበት በአጭር ቀን ልዩነቱ ሲታይ ደንግጦ መንበጫበጭ አያዋጣም። አያዛልቅም።

"…ሰው እንዴት ጎንደሮች ታረቁ ብሎ ይበሳጫል? እንዴት ደም ያስመልሰዋል? ሰው ሸዋዎች ወደ አንድ እንዳይመጡ በዚህ ልክ እንዴት ይደክማል? ሰው ጎጃምን፣ ጎንደርን የዐማራ ጋዜጠኛ፣ አክቲቪስት መስሎ እንዴት ይከፋፍላል? ወንድሞች ቢገዳደሉስ ምንድነው ጥቅሙ?

• ማርያምን አልፋታችሁም…!
"…ገና በሽታውማ አትስከሩ…!

"…ሲጀመር ገና ምኑንም አልተናገርኩም። አላወራሁም። አላሳየሁም። ነገር ግን ወዴት እንደምሄድ የገባው ፀረ ዐማራ፣ ፌክ ኢትዮጵያኒስት ምድረ ግንቦቴ ሁላ መስቀል እንዳየ ፀበም እንደነካው አጋንንት እምቧእሪቁቀምበጭ ማለት ጀምሯል። ምኑ ተያዘና ነው የምትለፈልፈው።

"…በእርቁ ሰዓት ዋነኛው የፋኖዎች ችግር የነበረው ሁሉ በድምጽ የተቀዳ፣ ሽማግሌዎቹ ሁሉ ያዘኑበት፣ በመሬት ላይ ያለው ፋኖ የሚያደርገው የሚሠራው የጠፋበት፣ በእስክንድር በኩል ተጠግተው የመጡት ፌክ ኢትዮጵያኒስቶች ገና ለገና ብልፅግና መውደቁ አይቀርምና እኛ ከአሁኑ የራሳችንን ፋኖ ገዝተን አዘጋጅተን ቦታ ሥልጣን መያዝ አለብን በማለት በማወክ ፋኖን በጋዜጠኝነት ስም አሸማቀው መድረሻ ለማሳጣት የተኬደበትን ርቀት ይፋ አወጣዋለሁ።

"…ለሽምግልና የተጠራን ሽማግሌዎች በምንችለው ሁሉ ፋኖዎችን ተማጽነን በስግብግቦች ሴራ ምክንያት ደም እንዳይፋሰሱ አድርገናል።

"…እኔ እዳ የለብኝም። በኋላ ከተጠያቂነት ለመዳን አሁኑኑ የችግሩን ሰንኮፍ ውልቅ አድርጎ ማውጣት ያስፈልጋል። ሽመልስ ለገሰን እጅግ አድርጌ አመሰግነዋለሁ። ተናግሮ እንድናገር ስላደረገኝ አመሰግነዋለሁ።

"…በተረፈ ቀንተህ ነው፣ ምናምን ለእኔ አይሠራም። በምኑ ነው የምቀናው? የዐማራ ፋኖን መከራና ሙጀሌ ግን በመረጃ እና በማስረጃ ሰንኮፉን ነቅለን እናወጣዋለን።

"…ሺ ሆነህ ና፣ ተደራጅተህ ና፣ ተሰባስበህ ና እኔ ዘመዴ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር ዱቄት ነው የማደርግህ። ምድረ መኒ ላውንደሪ፣ ገንዘብ አጠባ ላይ የተሰማራህ የደም ነጋዴ የዶላር ቀበኛ ሁላ አሁን ነው የሚለይልን።

"…እኔ አንድም አጋዥ ሰው አልፈልግም። ግንቦቴዎች ልትሞግቱኝ ትችላላችሁ የሰው አይን የሚያቆሽሽ የተለመደ ነውረኛ ስድባችሁ ግን ያስቀስፋችኋል።

• ሰምተሃል…!
ማስታወቂያ…!

"…ይህ አዲሱ የኢትዮ 360 የሳታላይት ቴሌቭዥን ጣቢያን የምታገኙበት ማስታወቂያ ነው። ተከታተሉት።

"…ምንሊክ የሚለውን ብቻ ምኒልክ በሚለው አስተካክሉት እንጂ ሌላው ልክ ነው። የሐረርጌ ቆቱ ነገር ለዐማሮች አማርኛ ላስተምር ብዬ እኮ መከራዬን በላሁ። ዐማራ ተሁኖ፣ ለዐማራ እየታገሉ ቢረሳ ቢረሳ የታላቁን ንጉሠ ነገሥት የእምዬ ምኒልክን ስም አስተካክሎ ያለ መጻፍ ልክ አይሆንም።

"…ይሄን ማስታወቂያ ደጋግሜ በፔጄ አስተዋውቀዋለሁ። ይሄ አይደለም ቁም ነገሩ። ቁምነገሩ ምድር ላይ ያሉትን ፋኖዎች ከፋፍሎ ማጋደሉን ማስቆሙ ላይ ነው። እገሌ ስር ካልገባችሁ በቴሌቭዥን ድራሽ አባታችሁን ነው የማጠፋው ማለትን ነው ማስቆም።

"…የሸዋም፣ የጎንደር የጎጃሞችም፣ የወሎም ፋኖዎች የሁሉም ችግር እርሱ ነው። በጥቂት የሥልጣን ጥመኞች ክፉ ሴራ ምክንያት በቅርቡ የሺዎች ፋኖዎች ደም በከንቱ ሲፈስ፣ እርስ በእርስ ሲጨራረሱ ታያላችሁ። አቅም ያላችሁ ሸዋዎች መሃል በቶሎ ግቡ። ጎንደር ትናንት ታርቀው በመታረቃቸው የተናደዱ ዛሬ ሲያታኩሱአቸው ነው የዋሉት።

"…ግንቦት 7፣ ግንባሩ፣ ሠራዊቱ፣ በግል ወንድሜ ጋዜጠኛ ሀብታሙ አያሌው ከፋኖዎች መሃል ውጣ በሉት። እኔ የምመክረው ይመራችኋል ነገር ግን ደም እንባ ነው የምታለቅሱት። ተናግሬአለሁ። ያገባኛል የምትሉ በቶሎ ጣልቃ ግቡ።

"…ባይገርምላችሁ እህተ ማርያም(ስንዱም) ሆነች የዓለም ብርሃኖች የራሳቸው ጦር አላቸው ብላችሁስ። ስንዱ እንግሊዛዊ ናት አንዱን ትነግሳለህ ብላ ቀብታ አስቀምጣዋለች። 😂። ደብረ ኤልያስ መሽገው የነበሩት ደግሞ አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ እገሌ ነው መንገሥ ያለበት ብለዋል ብለው ፋኖ ሁሉ ለዚያ ሰው ይንበርከክ ይታዘዝ ብለው ጉድ አፍልተዋል። ይሄ ሁላ ቅዠት ግን ያልፋል። ዐማራም አሳምሮ ድብን አድርጎ ያሸንፋል።

• እየኮመታችሁ…!
HTML Embed Code:
2024/04/27 02:15:16
Back to Top