🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆
. 12 ኛ ዙር ግጥም ውድድር
👨⚕️ ደም እለግሳለሁ 💉
ሰው ለሰው ከሆነ ~ የህመም መዳኛው፤
በጎነት ለራስ ነው ~ ኅሊና ነው ዳኛው።
ደስተኛ ለመሆን ~ እንድታገኝ ሰላም፤
በደስታው ተደሰት ~ በሕማሙ ታመም።
በደም መፍሰስ ምክንያት ~ አትሞትም እናቴ፤
እስትንፋሴ እያለ ~ ሳለሁ በሕይወቴ።
ለአእምሮዬ እረፍት ~ ለኅሊና እርካታ፤
ሰው ሆኘ እገኛለሁ ~ ከሰውነት ተርታ።
የችግር ቀን ደራሽ ከምንጊዜም ፈጥኖ፤
ሰው ለመርዳትኮ...
በቂ ነው ወዳጄ ~ መፈጠር ሰው ሆኖ።
ቀን ሳለኝ ሳልደክም ~ ደም እለግሳለሁ፤
በሕይወት እየኖርኩ ~ ሕይወት አተርፋለሁ።
የኔ ደም መለገስ ~ ሕይወት ካተረፈ፤
ውስጤ ሰላም ሆነ ~ እፎይ ብሎ አረፈ።
✍ 𝕟𝕒𝕙𝕠𝕞
ግጥሙን ከወደዳችሁለት ላይክ እና ሼር ተባበሩት
🏆🏆🏆
ለመቀላቀል
👇👇👇
hottg.com/zemaritnsae
🏆🏆🏆🏆🏆
ግጥም ለመላክ
. 👇👇👇
. @Tins7
>>Click here to continue<<