__
የሆነ ቀን ሌሊት
ገላየ እንቅልፍ አጥቶ
ከሆነ ሕልሙ ጋር የትዝታ ጠረን
በልቡ ያሸታል ፣
ከወዲያ ጫፍ ደግሞ ፣ «ጥላሁን» ተከፍቷል ፣
.
ፍቅር ለብቻየ
የሚል እንጉርጉሮ
.
ከዚህ ዘፈን በታች
Pablo Neruda
''Every Day You play the light of the Universe '' !
እያለ ይወርዳል ፣
ከማን ጋር ልስማማ
ትዝታ አቅም ኑሮት ፣ ማንን ይጋርዳል ?
.
ዮሐንስ አድማሱን
በድሉ ዋቅጅራን
ቸርነት ወ/ገብሬልን
ወይ ደግሞ ኤፍሬምን
«ፍቅር እዚህ ቦታ ፈገግ ብሎ ነበር» ያለሽን ልቀፈው ፣
ከሁሉም ለመሸሽ
እንደምን ? እንደምን ? ፣ ይኼን ቀን ልለፈው ?
.
አሁን ለምሳሌ
የአምስት ግጥም ዕድሜ
ከሚለው መጽሐፍ ላይ
.
ከወዝ መጋራት ጋር
የሚመሽ አንድ ቀን
ይነጋል እያለ
የጻፈላት ግጥም ፣ መንጋቱን ሸረፈው ፣
ወቅትን እንደ ኩታ ፣ ዘቅዝቆ አነጠፈው ።
.
ታዲያ በዚህ መሃል
ናፍቆት ግፉን ትቶ ፣ ሲሄድ እያየሽው ፣
ፍቅር ለብቻየን ፣ ለምን ነበር ያልሽው ?
እንጃ ።
ብቻ ግን አንዳንዴ !
.
ሰትዮዋ እንዴት ናት ?
የሚል ግጥም ጽፎ
አቦል የፍቅር ወዝ ፣ መድፋት ስለሚቻል ፣
የኖሩት እያለ ፣ የሚመጣው ነገ እንዴት ይሰለቻል ?
ቢሆንስ
ቢሆንስ
.
አሁን በዚህ ሰዓት
ሴትዮዋ እንዴት ናት ?
.
በነገራችን ላይ
ከዚህ ሁሉ ኋላ
የጥላሁን ዘፈን
ሥራውን እርስቶ ፣
መዳፌ ላይ ያለ ፣ መጽሐፍ አንቺን ትቶ ፣
.
ፍቅር እዚህ ቦታ
ብለው የሰቀሉት ፣ ግጥም የለም ጠፍቷል ፣
ገጣሚው እንደ እግዜር ፣ ብቸኝነት ፈርቷል ።
.
በእርግጥ !
.
የሆነውን ሁሉ
አሁን የለም ብለው ፣ ሲገፉት እንዳሻው ፣
ከሁሉም መሸሽ ነው ፣ የሰው መጨረሻው ፣
_____
ሶሎሞን ሽፈራው
JOIN
@yourpoim
>>Click here to continue<<