TG Telegram Group & Channel
አንደበት | United States America (US)
Create: Update:

"ማርያም እኮ ሞተች"
ኤልያስ ሽታኹን

*           *         *         *        *            *       *

"የአብ ወዳጁ
የወልድ ደጁ
የቅዱስ መንፈስ እጁ፡፡"
                                ማርያም እኮ ሞተች፡፡


የአባጊዮረጊስ ዘጋስጫ
የማትወዳደር ምረጫ
የአባ ሕርያቆስ ቅዳሴው
የቅዱስ ኤፍሬም ውዳሴው
ዮሴፍ ሲገፍፍ የለበሳት
ያዕቆብ በልቡ ያነገሣት

                              ማርያም እኮ ሞተች፡፡
ገብርኤል ለብስራት
ወዴት ልላክ? ብሎ ጌታን ያልጠየቀው
የቱ ጋር ነች? ብሎ ጌታን ያልጠየቀው
እናትህ የቷ ናት? ብሎ ያልጠየቀው
በሚካኤል አክናፍ መልኳን ስለሚያውቀው፡፡
ሰማይን ያለባላ ያቆመ
ወንዳቺ ሆድ ያዘመመ
ጥንተ ናፍቆት
የመለኮት
ዓይንሽ የሰባቱ ሰማያት መስኮት፡፡
ያ ትሁት ገፅሽን
በክንፍ ላይ ስሎሽ መላእክት ያያሉ
ለምነውት ነበር ፍጠራት እያሉ፡፡
(ቶሎ በል እያሉ)

                                   ማርያም እኮ ሞተች፡፡

በመኑ በአምሳለ መኑ ናስተማስለኪ
ነፍሴ ወዴት ደረስሽ? ማርያምን ሳትነኪ
አንቲ ውዕቱ
እኔ ምዑቱ
አንቲ መሶበ ወርቅ
እኔ የበደል ጨርቅ
አንቺ እመአምላክ
የቱ መግነዝ ቻለሽ
ትንሳኤን ወልደሽው ሞትን ትቀምሻለሽ?
አንቺም? እመብርሃን

                                      ማርያምእኮ ሞተች፡፡

ሰማይና ምድር
ወይቦ መልካቸው ሀዘን እያማጡ
እስከዛሬ አሉ
መላእክት ሁሉ እንደደነገጡ፡ 
ለክልዔቱ ጊዜ እስራኤል ጨነቀው
ከስደት ጀምሮ ኮቴዋን የሚያውቀው፡፡
የዳዊት በገና
ብቻውን ያለቅሳል ራሱን በመግረፍ
ዳዊት አላወቀም የልጅ ልጁን ማረፍ፡፡
ክልዔቱ ጊዜ ጨነቀው እስራኤል
እንኳንና አርፋ
ሲከፋት አይችልም በእርሷ እኮ ሚካኤል::
ክልዔቱ ጊዜ
ሰማይ አለቀሰ የመረረ ከሀሞት
መላእክት አያውቁም ማርያም እንደምትሞት፡፡

                               

                                           ማርያም እኮ ሞተች፡፡

ስትሰማ ኖሯ በሆዷ ቅዳሴ
አረፈች ይሉኛል  ወዮ ነው ለራሴ፡፡
አንቺን እመብርሃን ሞት በምኑ ያዘሽ
አላየሽም እንዴ አምላኩን እንዳዘዝሽ፡፡
የቱ መልአክ ሞት ተላከ ወዳንቺ
ችሎ አይገባም ቤትሽ እሺ ብለሽ እንጂ፡፡
ፍትሃት የለም ለማርያም
የተፈታ የሚገባባት እርሷ ራሷ አርያም፡፡
ለማርያም አይቀደስላት
እርሷ ራሷ ቅዳሴ ናት፡፡

                                        ማርያም እኮ ሞተች፡፡



*       *        *         *        *         *

#ማስታወሻ
   * በነገረ - ማርያም
   * ስንክሳርም እንደተነገረን
እመቤታችን በ፷፬ አመቷ  በገዛ ፍቃዷ አርፋ፡፡
ሞትን ቀምሳለች፡፡ነሐሴ ፲፮  ከሞት ተነስታ ማረጓን ልብ ይሏል፡፡
"ሞትሰ ለመዋቲ ለመዋቲ ይደሉ
ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ"



@yourpoim
@yourpoim

"ማርያም እኮ ሞተች"
ኤልያስ ሽታኹን

*           *         *         *        *            *       *

"የአብ ወዳጁ
የወልድ ደጁ
የቅዱስ መንፈስ እጁ፡፡"
                                ማርያም እኮ ሞተች፡፡


የአባጊዮረጊስ ዘጋስጫ
የማትወዳደር ምረጫ
የአባ ሕርያቆስ ቅዳሴው
የቅዱስ ኤፍሬም ውዳሴው
ዮሴፍ ሲገፍፍ የለበሳት
ያዕቆብ በልቡ ያነገሣት

                              ማርያም እኮ ሞተች፡፡
ገብርኤል ለብስራት
ወዴት ልላክ? ብሎ ጌታን ያልጠየቀው
የቱ ጋር ነች? ብሎ ጌታን ያልጠየቀው
እናትህ የቷ ናት? ብሎ ያልጠየቀው
በሚካኤል አክናፍ መልኳን ስለሚያውቀው፡፡
ሰማይን ያለባላ ያቆመ
ወንዳቺ ሆድ ያዘመመ
ጥንተ ናፍቆት
የመለኮት
ዓይንሽ የሰባቱ ሰማያት መስኮት፡፡
ያ ትሁት ገፅሽን
በክንፍ ላይ ስሎሽ መላእክት ያያሉ
ለምነውት ነበር ፍጠራት እያሉ፡፡
(ቶሎ በል እያሉ)

                                   ማርያም እኮ ሞተች፡፡

በመኑ በአምሳለ መኑ ናስተማስለኪ
ነፍሴ ወዴት ደረስሽ? ማርያምን ሳትነኪ
አንቲ ውዕቱ
እኔ ምዑቱ
አንቲ መሶበ ወርቅ
እኔ የበደል ጨርቅ
አንቺ እመአምላክ
የቱ መግነዝ ቻለሽ
ትንሳኤን ወልደሽው ሞትን ትቀምሻለሽ?
አንቺም? እመብርሃን

                                      ማርያምእኮ ሞተች፡፡

ሰማይና ምድር
ወይቦ መልካቸው ሀዘን እያማጡ
እስከዛሬ አሉ
መላእክት ሁሉ እንደደነገጡ፡ 
ለክልዔቱ ጊዜ እስራኤል ጨነቀው
ከስደት ጀምሮ ኮቴዋን የሚያውቀው፡፡
የዳዊት በገና
ብቻውን ያለቅሳል ራሱን በመግረፍ
ዳዊት አላወቀም የልጅ ልጁን ማረፍ፡፡
ክልዔቱ ጊዜ ጨነቀው እስራኤል
እንኳንና አርፋ
ሲከፋት አይችልም በእርሷ እኮ ሚካኤል::
ክልዔቱ ጊዜ
ሰማይ አለቀሰ የመረረ ከሀሞት
መላእክት አያውቁም ማርያም እንደምትሞት፡፡

                               

                                           ማርያም እኮ ሞተች፡፡

ስትሰማ ኖሯ በሆዷ ቅዳሴ
አረፈች ይሉኛል  ወዮ ነው ለራሴ፡፡
አንቺን እመብርሃን ሞት በምኑ ያዘሽ
አላየሽም እንዴ አምላኩን እንዳዘዝሽ፡፡
የቱ መልአክ ሞት ተላከ ወዳንቺ
ችሎ አይገባም ቤትሽ እሺ ብለሽ እንጂ፡፡
ፍትሃት የለም ለማርያም
የተፈታ የሚገባባት እርሷ ራሷ አርያም፡፡
ለማርያም አይቀደስላት
እርሷ ራሷ ቅዳሴ ናት፡፡

                                        ማርያም እኮ ሞተች፡፡



*       *        *         *        *         *

#ማስታወሻ
   * በነገረ - ማርያም
   * ስንክሳርም እንደተነገረን
እመቤታችን በ፷፬ አመቷ  በገዛ ፍቃዷ አርፋ፡፡
ሞትን ቀምሳለች፡፡ነሐሴ ፲፮  ከሞት ተነስታ ማረጓን ልብ ይሏል፡፡
"ሞትሰ ለመዋቲ ለመዋቲ ይደሉ
ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ"



@yourpoim
@yourpoim


>>Click here to continue<<

አንደበት




Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)