TG Telegram Group & Channel
josi _ ጆሲ | United States America (US)
Create: Update:

አትሸፋፍኑት! ይገለጥ !!

Do not resist pain! Allow it to be there !
Ekhart Tolle

ህመምና ጉዳትህን አትቃወም ፤ ይኖር ዘንድ ፍቀድለት እንጂ!

ኤካርት ቶሌ

      ሕይወታችን እኛ ባሰብነውና በተመኘነው ልክ ሁሌም አትሄድም ። ደስ ይል  ነበር እኮ ምኞታችን ሁሉ ቢሰምር ፤ ያቀድነው ሁሉ ቢሳካ ፤ ውጥናችን ቢተገበር ፤ የወደድነውን ብናገባ ፤ በመረጥንበት ብንኖር ፤ የተማርነውን ብንተገብር ፤ ትምህርታችንን በማዕረግ ብንደመድም ፤ የፈለግነውን ሁሌም ብንከውን።

      በሕይወት ሁሌ መስከረም የለም ሐምሌና ነሐሴም ጭምር እንጂ ካሰብነው በተቃራኒው ልንኖር ፤ የከፈትነው ሊከስር ፤ የወደድነውን ልንድር ፤ የተመኘነውን ላንኖር ፤ የተማመንበት ላይኖር ፤ የተመረኮዝነው ሊሰበር ፤ ፈጽሞ ያልጠበቅነው ሊከሰት  ውጥናችን ላይሰምር ፤ ሀሳባችን ላይከወን ፤ አካላችን ሊጎድል ፤ ጤናችን ሊታወክ.... ይችላል። ይሄን ሁሉ ታዲያ እንደኮሶ ባይጥመንም ለመሻር የግዳችንን መቀበል እና መጎንጨት አለብን!!

     መታመም ደስ ባይልም ፤ መጎዳት ቢያስከፋም ፤ መክሰር ቅስም ቢሰብርም ፤ መውረድ አንገት ቢያስደፋም ፤ መከዳት አቅል ቢያስትም ፤ ማጣት ቢያስጠላም ፤ መናቅ ቢያምምምምምም ..... ያለን ብቸኛ አማራጭ መታገል ሳይሆን እንዲሆን መፍቀድ ነው። በቃ የሆነው ሁሉ ሊሆን ግድ ነው! ያለን አማራጭ መቀበልና አብሮ ከክስተቱ ጋር መኖር ብቻ ነው!

   ራሳችሁን ታዘቡ እስቲ ምን ያህል ከእውነታው እንደምንጣላ ፤ የቱን ያህል ስሜታችንን እንደምናፍነው ። ሌላው ቢቀር በቅጡ ለማልቀስ እንኳ እኮ ያልታደልን ነን 'እንዴት እኔ? ሰው ምን ይለኛል? ለማን ደስ ይበለው? ወንድ ልጅ አያለቅስም '.... እያልን በጊዜው ሊወገድ የሚገባው ሀዘን ፤ ቁጣና ብስጭት በራሳችን ላይ ግዙፍ አለት ሆኖ እስኪደድርና  ማንነታችን እስኪሆን እናደርሰዋለን። ይሄ ግን አይጠቅምም!

ሁሉም ነገር በጊዜና ወቅቱን ጠብቆ ሲሆን ደስ ይላል ። ለምን ሆነ ብለን የሆነውን ነገር ከምንቃወም መቀበልና የሚሰማን ስሜት እንዲወጣ ማድረጉ ፍቱን ነው!

🎀 በቸር ያቆየን!!🎀
@yetbeb

>>Click here to continue<<

josi _ ጆሲ

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)