የሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ለአርቲስት አንዱአለም ጎሳ ሰጥቶት የነበረውን ሽልማት ሰረዘ፤ ይቅርታም ጠይቋል!
የሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ስሞኑን በተካሄደው አራተኛው የሀጫሉ ሁንዴሳ የሽልማት ፕሮግራም ላይ ለአርቲስት አንዱአለም ጎሳ ሽልማት መስጠቱ "ስህተት" እንደሆነ ገልፆ ሽልማቱን በይፋ መሰረዙን አስታወቀ።
በእጮኛው ቃናኒ አዱኛ ሞት ጋር በተያያዘ ተጠርጥሮ ለሶስት ወራት ታስሮ ከቆየ በኃላ በዋስ የተለቀቀው አርቲስት አንዱአለም ጎሳ ሰሞኑን የሀጫሉ ሁንዴሳ ሽልማት መሸለሙን ተከትለው የተለያዩ አካላት በማህበራዊ ሚድያ ተቃውሞዋቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል።
በተለይም ከሽልማት ፕሮግራሙ በኃላ በቀኔኒ አዱኛ ላይ የደረሱ አካላዊ ጉዳቶችን የሚያሳዩ ምስሎች በማህበራዊ ሚድያ በስፋት መሰራጨታቸውን ተከትሎ ፋውንዴሽኑ የሰጠውን ሽልማት እንዲሰርዝ የማህበራዊ ሚድያ ዘመቻ ሲደረግ ነበር።
ይህንን ተከትሎ የሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ዛሬ ሰኔ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ሽልማቱን ከማበርከቱ በፊት ጉዳዩን ሲከታተል መቆየቱን ገልፆ፤ ሽልማቱ ምርመራ እያደረገ ካለው የሚመለከተው አካል ባገኘው ደብዳቤ ላይ በመመስረት የተበረከተ መሆኑን ገልጿል።
ይሁን እንጂ "ሽልማቱን ተከትሎ ከህዝብ በደረሰን ሀሳብ እና ቅሬታ ላይ በመመስረት ውሳኔያችን ስህተት እንደ ነበር በፋውንዴሽኑ ቦርድ ተረጋግጧል "ብሏል። ፋውንዴሽኑ ለተፈጠረው ስህተት ህዝቡን ይቅርታ እየጠየቀ ለአርቲስት አንዱአለም ጎሳ ተሰጥቶ የነበረው ሽልማት መሰረዙን ገልጿል። ፋውንዴሽኑ የሰውን ልጅ መብት ከሚጥሱ እና ፍትህ ከሚያዛቡ አካላት ጋር አብሮ እንደማይቆም አረጋግጧል።
@YeneTube @FikerAssefa
>>Click here to continue<<
