TG Telegram Group & Channel
YeneTube | United States America (US)
Create: Update:

ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የአንድ ቢሊየን ዶላር የፋይናንስ ስምምነት ተፈራረሙ!

ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የአንድ ቢሊየን ዶላር የፋይናንስ ስምምነት ተፈራርመዋል።ስምምነቱ ሀገሪቱ እያካሄደች ላለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና ሁሉን አቀፍ እድገትን ለመደገፍ የተደረገ ነው ተብሏል።

ስምምነቱ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያን የሪፎርም አጀንዳ ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።የድጋፍ ስምምነቱ የኢትዮጵያን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና አካታች የኢኮኖሚ እድገትን ለማገዝ እንደሚውል ተገልጿል፡፡

ስምምነቱ የፋይናንስ ሴክተሩ መረጋጋትን ለማረጋገጥ፣ የንግድ ተወዳዳሪነትን ለማጎልበት፣ የሀገር ውስጥ ሃብት ማሰባሰብን ለማጠናከር፣ ግልፅ እና ውጤታማ የመንግስት ሴክተር አስተዳደርን ለማስፈን እና የማህበራዊ አገልግሎቶችን ዘላቂነት ለማረጋገጥ እንደሚያግዝ ተነግሯል።

@YeneTube @FikerAssefa

👎4927👍1

>>Click here to continue<<

YeneTube

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)