እንጦጦ ላይ ያሉ ባህር ዛፎች ሙሉ በሙሉ ይነሳሉ ተባለ!
በአዲስ አበባ ተራራማ ቦታ በእንጦጦ ላይ የሚገኙት ባህር ዛፎች በቀጣይ ሦስት ዓመታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንደሚነሱ እና በሀገር በቀል ዛፎች እንደሚተኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ ሰይፉ ገልጸዋል።
ባህር ዛፍ ውሃ የመምጠጥ አቅሙ ከፍተኛ ስለሆነ እና መዲናዋ የከርሰ ምድርን ውሃ በአግባቡ ለመጠቀም እየሠራች በመሆኑ ዛፎቹን መተካት አንዱ መፍትሔ መሆኑን ቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል።
ባህር ዛፎቹ ሲነሱ ግን በእጥፍ በሀገር በቀል ዛፎች እና ስነ ምህዳሩን ለማስተካከል በሚችሉ ዛፎች እየተተኩ መሆኑንም መገረለጻቸውን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል፡፡
የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ከተጀመረ ወዲህ ከእንጦጦ ተነስተው ወደ መሀል ከተማ የሚፈሱት ወንዞች የውሃ መጠን መጨመሩንም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡በእንጦጦ ፓርክ ከሚገኙ የዛፍ አይነትቶች ባህር ዛፍ አብዛሃኛው ቦታ ይሸፍናል።
ይህ ደግሞ ለሥነ-ምህዳር ተስማሚ እንዳልሆነ በብዙ ሳይንሳዊ ጥናቶች የተረጋገጠ በመሆኑ፤ በአሁኑ ሰዓት በከተማዋ እየተካሄደ ካለው የወንዞች መልሶ ማቋቋም ፕሮጀክት ትግበራ ጋር ተሳስሮ ባህር ዛፍን በአገር በቀል ዝርያዎች ለመተካት እየተሰራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን አስታውቋል።በዚህም መሠረት በፖርኩ የሀበሻ ጽድ፣ ዝግባ፣ ወይራ የመሳሰሉት አገር በቀል ዛፎች ባህር ዛፍን እንዲተኩ እንደሚደረግ ተነግሯል።
Via AMN
@YeneTube @FikerAssefa
>>Click here to continue<<
