TG Telegram Group & Channel
YeneTube | United States America (US)
Create: Update:

በመዲናዋ 95 በመቶ የሚሆኑ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸው ተገለጸ!

በ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ከተፈተኑ 79 ሺሕ 34 ተማሪዎች መካከል 75 ሺሕ 85 ተማሪዎች ከ50 በመቶ በላይ ውጤት በማስመዝገብ ወደ ቀጣዩ ክፍል መሸጋገራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።የትምህርት ቢሮው የቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላት በዛሬው ዕለት ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በከተማ አስተዳደሩ ሥር ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 95 በመቶ የሚሆኑት የማለፊያ ነጥብ በማምጣት ወደ ቀጣይ ክፍል ማለፋቸውን ገልጸዋል።

አያይዘዉ የአካል ጉዳተኞች ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ከ45 በመቶ በላይ መሆኑን ተናግረዋል።ቢሮው ላለፉት ተከታታይ ሦስት ዓመታት የ6ኛ ክፍል ፈተና በመንግሥትና በግል ትምህርት ቤቶች በቀን እና በማታ የትምህርት መርሃግብር መስጠቱን ገልጸው፤ "የተያዘው ዓመት አፈጻጸም ከቀደሙት አንጻር ሲታይ ጥሩ የሚባል ነው" ብለዋል።

የትምህርት አሰጣጥ ስርአቱ ቴክኖሎጂን ጨማሮ ሬድዮ እና በቴሌቪዥንን በመጠቀም ሲሰጥ መቆየቱ ተማሪዎች ውጤታማነት እንዳገዘ ተገልጿል።የትምህርት ቢሮው የቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም አክለውም፤ ዘንድሮው በከተማ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች መካከል ከ1 እስከ 4 የሚሆኑት ከመንግሥት ትምህርት ቤቶች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ተፈታኝ ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉም በጋዜጣዊ መግለጫው ተጠቁሟል።

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa

23👍7😁6

>>Click here to continue<<

YeneTube

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)