TG Telegram Group & Channel
YeneTube | United States America (US)
Create: Update:

የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ 400 ሺሕ ዶላር ድጋፍ አደረገ!

የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ ለማጠናከር የ400 ሺሕ ዶላር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል።ይህ ድጋፍ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን ለማስፋፋት፣ የዋስትና ልውውጦችን እና የምርት አቅርቦቶችን ለማብዛት እንዲሁም አቅምን ለማጠናከር ይውላል።

ገንዘቡ የሚገኘው በአፍሪካ ልማት ባንክ ከሚተዳደረው የካፒታል ገበያ ልማት ትረስት ፈንድ ሲሆን፣ የተለያዩ ለጋሾች ድጋፍ ያደርጉለታል። የገንዘብ ድጋፉ ባለስልጣኑ ለባለሀብቶች፣ ለአክሲዮን ባለቤቶች እና ለሌሎች የገበያ ተዋናዮች ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ለማሰራጨት የሚያስችል የሕዝብ ይፋዊ መድረክ እንዲቋቋም ይረዳል ተብሏል።

በተጨማሪም፣ የምንዛሪ ፈንዶችን፣ “ሱኩክ” የተሰኘውን ከወለድ ነጻ የቦንድ ሽያጭ አገልግሎት እና አረንጓዴ ቦንዶችን ጨምሮ አዳዲስ አገልግሎቶችን ለማስፋፋት ይጠቅማል።ይህ ፕሮጀክት የአፍሪካ ልማት ባንክ በኢትዮጵያ እያደረገው ያለው የመጀመሪያው የካፒታል ገበያ ልማት ድጋፍ ሲሆን፣ ኢትዮጵያም በዚህ የካፒታል ገበያ ልማት ትረስት ፈንድ ተጠቃሚ የሆነች የመጀመሪያዋ የምስራቅ አፍሪካ ሀገር ሆናለች።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa

16🔥2😁1😭1

>>Click here to continue<<

YeneTube

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)