ኢትዮጵያ ወደ ታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል መላክ ጀመረች!
ኢትዮጵያ በኬንያ በኩል ወደ ታንዛኒያ ለመጀመሪያ ጊዜ የኤሌክትሪክ ኃይል በሙከራ ደረጃ መላክ መጀመሯ ተገለጸ።የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለፁት፤ የሁለቱ ሀገራት የኤሌክትሪክ አቅርቦት ስምምነቱ ከተፈረመ የተወሰኑ ወራት ተቆጥረዋል።
በዚህም መሰረት አሁን ላይ በኢትዮጵያ በኩል 200 ሺህ ሜጋ ዋት ድረስ የመሸከም አቅም ያለው የማስተላለፊያ መስመር ተሰርቷል ብለዋል።አሁን በመስመሩ እየተላለፈ ያለው 200 ሜጋ ዋት መሆኑን በመጥቅስ፤ መስመሩ ተጨማሪ ግንባታ ሳይከናወን ተጨማሪ ኃይል ማስተላለፍ እንደሚችል ተናግረዋል።
ሙከራው በሂደት ላይ ያለ ነው ያሉት አቶ ሞገስ፤ በይፋ የኤሌክትሪክ ሽያጭ እንዳልተጀመረ ተናግረዋል።የኃይል ልማት ትስስሩ ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ልማት ለሌሎች ሀገራት ጭምር ሞዴል የሚሆን ሥራ እየሰራች መሆኑን የሚያመለክት መሆኑን አንስተዋል።
ሀገሪቱ ያላትን ሀብት ለራሷ ብቻ ሳይሆን በዙሪያው ከሚገኙ ጎረቤቶቿ ጋር የጋራ ተጠቃሚነትን አረጋግጣ በጋራ የማልማት ፍላጎት ያላት ሀገር መሆኗን የሚያሳይ ነውም ብለዋል።
የኬንያ ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ኩባንያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዶክተር ኢንጂነር ጆን ማቲቮ ኤምቢኤስ በማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው እንዳስታወቁት፤ በሙከራው የኤሌክትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ በኬንያ በኩል ኤሌክትሪክ የማስተላለፊያ መስመር በተሳካ ሁኔታ ኤሌክትሪክ ማስተላለፍ መቻሉን ተናግረዋል።
Via Gazeta+
@YeneTube @FikerAssefa
>>Click here to continue<<
