TG Telegram Group & Channel
YeneTube | United States America (US)
Create: Update:

የህወሓት ክፍፍልን ተከትሎ ለሁለት የተከፈሉት የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ወደ እርስ በርስ ግጭት ሊያመሩ ነዉ የሚል ከፍተኛ ስጋት መፈጠሩን በትግራይ በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሰው «ሳልሳይ ወያነ ትግራይ» አሳሰበ።

ሊፈጠር የሚችለዉን ቀውስ ለማስቀረትም በትግራይ ሁሉን አካታች ብሔራዊ ውይይት እንዲደረግ ፓርቲው ጥሪ አቅርቧል።የትግራይ ሐይሎች ወታደራዊ መኮንኖች ባለፈው ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም «ለአንዱ የህወሓት ክንፍ ያጋደለ» የተባለለትን የአቋም መግለጫ በማንፀባረቃቸው፣ በትግራይ ሐይሎች መካከል መከፋፈሎች መፈጠራቸው ይነሳል።

ይህ ደግሞ የትግራይ ሐይሎች ከፍተኛ አዛዦች ያሉበት ሌላ ታጣቂ ሐይል እንዲፈጠር ምክንያት መሆኑ ተነግሯል። በአፋር እና ትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች ለወራት የቆየው ይህ አዲስ ሐይል ወደ ትግራይ ክልል መንቀሳቀሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።አዲሱ ታይል እዚያዉ ትግራይ ከሚገኘዉ ነባሩ ኃይል ጋር የእርስ በርስ ግጭት እንዳይገጥም የሚል ስጋት በበርካቶች ዘንድ ተፈጥሯል ሲል የዘገበው ዶይቼ ቬለ ነው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa

17👍3🔥3👀3😁2

>>Click here to continue<<

YeneTube

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)