ክልሎች ለወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር በሚል፤ ህግ ወጥ ኬላዎችን እንደሚያቋቁሙ ሁለት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በጋራ ያስጠኑት ጥናት አመላከተ!
በኢትዮጵያ በክልል ፖሊሶች፣ የሚሊሻ መዋቅሮችና ለወጣቶች የስራ እድል በሚል 237 ህገወጥ ኬላዎች መቋቋማቸውን የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶቹ ጥናት አመላከተ።ንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ከትራንስፖርት እና ሎጂስቲከስ ሚኒስቴር በጋራ በመሆን በሚያዚያ ወር 2017 ዓ.ም ባጠናቀቁት ጥናት መሰረት በሀገሪቱ 237 ህገ ወጥ ኬላዎች መኖራቸው መረጋገጡ ተገለጸ።
ክልሎች ለወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር በሚል፤ ህግ ወጥ ኬላዎችን እንደሚያቋቁሙ በጥናቱ መረጋገጡም የጉምሩክ ኮሚሽን ጠቁሟል።የጉምሩክ ኮሚሽን ይህን የተናገረው የ11 ወር የስራ ክንውን ሪፖርቱን ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት መሆኑ ተገልጿል።
ባለፉት 11 ወራት 19 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን የተናገረው የጉምሩክ ኮሚሽን፤ በየክልሎች ገመድ እየተወጠረ ገቢ የሚሰበስብባቸው ህገ ወጥ ኬላዎች በሀገሪቱ ንግድ ሥርዓት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደሩ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ኬላዎችን ዘርግተው ግብር የሚሰበስቡት የክልለ ፖሊሶች፣ የሚሊሻ መዋቅሮች እንዳንድ ቦታ ደግሞ ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ እና በወረዳ ግብረ ሃይል ተብሎም ጭምር የተቋቋሙ ኬላዎች እንዳሉ ምክትል ኮሚሽነሩ አቶ አዘዘው ጫኔ መናገራቸውን ከሸገር ሬድዮ ያገኘነው መረጃ ያሰያል።
@YeneTube @FikerAssefa
>>Click here to continue<<
