የውጭ ሀገር ዜጎች በትንሹ 150 ሺህ ዶላር በመውጣት የማይንቀሳቀስ የመኖሪያ ቤት ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅደው አዋጅ ፀደቀ!
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ሀገር ዜጎች የማይንቀሳቀስ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የመሆን መብት አዋጅን አጸደቀ። ከአዲስ አበባ ውጪ መስራት ቢፈልጉ በወጣው መመሪያ መሰረት ክልሎች ተፈፃሚ እንደሚያደርጉም ተገልጿል።የውጭ ሀገር ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በመኖሪያ ቤት ባለቤትነት ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የተቀመጠው አነስተኛ የገንዘብ መጠን 150 ሺህ ዶላር ነው ተብሏል።
“አንድ የውጭ ሀገር ዜጋ የሊዝ ዋጋውን ጨምሮ ለአንድ መኖሪያ ቤት ግንባታ ሙሉ ዋጋ ወይንም ለመኖሪያ ቤት ግዢ የሚመድበው አነስተኛ የገንዘብ መጠን ከ150 ሺ ዶላር ያነሰ ሊሆን አይችልም” ተብሏል።150 ሺህ ዶላር ሁኖ የተቀመጠው አነስተኛ የገንዘብ መጠን በጊዜ ሂደት እየተሻሻለ እንደሚሄድም ተመላክቷል።
"ማንኛው የውጭ ዜጋ በማናቸውም ጊዜ፣ በአንድ ግዜ የሚኖረው የመኖሪያ ቤት ቁጥር አንድ ብቻ" መሆኑ የተቆመ ሲሆን ሚኒስቴሩ "ከአገር ጥቅም አንጻር አስፈላጊ ሁኖ ሲያገኘው ይህን ቁጥር በመመሪያ ማሻሻል ይችላል" ተብሏል።የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሆነ የውጭ ሀገር ዜጋ “ለግለሰብ ወይም ለቤተሰብ የማከራየት መብቱ እንደተጠበቀ ሁኖ መኖሪያ ቤቱን ለንግድ አላማ ማዋል የተከለከለ መሆኑ” በአዋጁ ተቀምጧል።
ይህ የተገለጸው በምክር ቤቱ የከተማ፣ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአዋጁ ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡለት ጥያቄ ምላሽ እና ማብራሪያ በሰጠበት ወቅት ነው።መሬት የመንግስት እና የህዝብ እንደመሆኑ ለኢንቨስትመንት የሚመጡ ዜጎች መሬቱን የመሸጥ እና የመለወጥ መብት የላቸውም ተብሏል።
የውጭ ሀገር ዜጎች በመኖሪያ ቤት ባለቤትነት ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የቀረበው የገንዘብ መጠን ዝቅተኛ በመሆኑ ወደ ኢትዮጵያ በብዛት ሊገቡ ስለሚችሉ የሰው ቁጥሩ በሀገራችን እንዲጨምር ሊያደርግ ይችላል የሚል ጥያቄ ከአባላቱ ተነስቷል።
@YeneTube @FikerAssefa
>>Click here to continue<<