“በአዲስ አበባ የትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ የዘፈቀደ እስራት እየተፈጸመ ነው” - ሂዩማን ራይት ፈርስት
ሂዩማን ራይትስ ፈርስት የተሰኘ የሃገር ውስጥ መብት ተሟጋች ድርጅት “በአዲስ አበባ የሚገኙ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ወጣቶች በከተማዋ ባለስለጣናት ኢላማ ተደርገው፣ ያለምንም መደበኛ ክስ እና ፍርድ ሂደት በማንነታቸው ምክንያት “የዘፈቀደ እስራት” እየተፈጸመባቸው ነው” ሲል ክስ አቀረበ።
በተመሳሳይ በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሰው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) ትላንት ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ነዋሪነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች በፀጥታ ሃይሎች በዘፈቀደ እየታፈሱ እና በህገወጥ መንገድ እየታሰሩ እንደሚገኙ ሪፖርት እንደደረሰው አስታውቋል።
ለእስር ተዳርገው በኋላ ላይ መፈታታቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ያስታወቁ አንድ በከተማዋ ነዋሪ የሆኑ የትግራይ ተወላጅ ለምን እንደታሰርን ስንጠይቃቸው ምንም አይነት ማብራሪያ አልሰጡንም ብለዋል፤ “ከበላይ አካል የመጣ ትዕዛዝ ነው” የሚል ምላሽ ነው የሰጡን፤ ክስ አልተመሰረተብንም፣ ፍርድ ቤትም አለቀረብንም” ብለዋል።
ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) እንዲሁም ሂዩማን ራይት ፈርስት “ዜጎችን ስማቸውን ወይም ብሄራቸውን መሰረት በማድረግ ለእስር መዳረግ ሀገር አቀፍ እና አለም አቀፍ ህግጋትን የሚጻረር እና መጣስ ነው” ሲል በመኮነን “ያለ ፍርድ ሂደት ለእስር የታዳረጉት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ” ሲሉ በተናጠል ባወጡት መግለጫ ጠይቀዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
>>Click here to continue<<
