በኢትዮጵያ በአንድ ማዕከል ብቻ 7 ሺህ 500 የሚሆኑ የልብ ህሙማን ወረፋ እየጠበቁ እንደሚገኙ ተገለጸ!
የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል 7 ሺህ 500 የሚሆኑ የልብ ህሙማን ወረፋ እየጠበቁ እንደሚገኙ አስታወቀ።ወረፋ እየጠበቁ ከሚገኙት ውስጥ ከ2 ሺህ በላይ የሚሆኑት ከተወለዱ ጀምሮ በሚከሰት የልብ ህመም ተጠቂ ህፃናት መሆናቸውን የማዕከሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ኤልኤዘር ሃይሌ ገልጸዋል።
የልብ ህሙማኑን ለመርዳት ለማዕከሉ የሚበረከቱ ግብአቶች ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወቱ አስታውቀው፤ ለማዕከሉ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች ሙሉ በሙሉ ከውጪ የሚገቡ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡በተለይ አላቂ የህክምና ግብዓቶች በየህፃናቱ የክብደት መጠን ልክ እንደሚገዙ የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ በድጋሚ መጠቀም የማይቻሉ ግብዓቶች በመሆናቸው የህክምናውን ሂደት አደገኛ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። ግብአቶቹ ዋጋቸው እጅግ በጣም ውድ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
የልብ ቫልቮች፣ ልዩ ልዩ ማሽኖች፣ ልዩ ልዩ መድሀኒቶች እንዲሁም ልብን በማቆም ለሚሰሩ ቀዶ ጥገናዎች የሚውሉ የተለያዩ ግብአቶች ለማዕከሉ ወሳኝ መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ ሰዎች 6710ን በመጠቀም፤ በግልም ሆነ በቡድን ታማሚዎችን በመጎብኘት፣ ታማሚዎችን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ስፖንሰር በማድረግ እንዲሁም ከማዕከሉ በሚያገኙት ዝርዝር መሰረት በግብዓት አቅርቦት መደገፍ እንደሚችሉ መጠቆማቸውን ከፕሬስ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
>>Click here to continue<<
