ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ በ25 ከተሞች አዲስ የባንክ አካውንት ለመክፈት የፋይዳ መታወቂያ አስገዳጅ ሊሆን ነው!
ከሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በ25 የክልል ከተሞች በሚገኙ ባንኮች አዲስ የባንክ ሂሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እንደ ቅድመ ሁኔታ ተግባራዊ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታወቀ።በአዲስ አበባ በሚገኙ ሁሉም ባንኮች ከታህሳስ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የፋይዳ መታወቂያ አስገዳጅ ሆኖ በመተግበር ላይ መሆኑን ይታወቃል።
ከሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የፋይዳ መታወቂያ አስገዳጅ የሚሆንባቸው ከተሞች፡-
በባህር ዳር፣ ደሴ፣ ጎንደር፣ ደብረ ብርሃን፣ ኮምቦልቻ፣ ሸገር፣ አዳማ፣ ሻሸመኔ፣ ቢሾፍቱ፣ ጅማ፣ ባቱ፣ ሆሳዕና፣ አምቦ፣ ወልቂጤ እና ሐዋሳ ከተሞች አዲስ የባንክ ደብተር ለመክፈት እንደ መጀመሪያ ቅድመ ሁኔታ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።
በተጨማሪም በሀረር፣ ወላይታ ሶዶ፣ መቀሌ፣ ወራቤ፣ አዲግራት፣ ድሬዳዋ፣ አርባምንጭ፣ ጅግጅጋ፣ አክሱም እና ቡታጅራ ከተሞች ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል።
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዲጂታል መታወቂያውን ለማስፋፋት ከ3 ሺህ በላይ የምዝገባ መሳሪያዎች ገዝቶ አገልግሎት ላይ ማዋሉን እና ከ1 ሺህ በላይ የምዝገባ ጣቢያዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
[KGEthiopia]
@YeneTube @FikerAssefa
>>Click here to continue<<
