TG Telegram Group & Channel
YeneTube | United States America (US)
Create: Update:

አውሮፕላኑ ምን ገጠመው

በሙምባይ የአስቸኳይ ጊዜ ማረፊያ ያደረገው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 787 አውሮፕላን 7 ተሳፋሪዎች ታመዋል ተባለ

ከዓለም ዓቀፍ መረጃዎች እንደተዘገበው ከሆነ ከዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም (June 28, 2025) ጀምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 787 አውሮፕላን ወደ ሙምባይ ሲበር በካቢን ውስጥ የነበረው ግፊት በመቀነሱ ምክንያት ድንገተኛ አደጋ አጋጥሞታል ተብሏል።

በዚህም ምክንያት ሰባት ተሳፋሪዎች መታመማቸው ተገልጿል።

አውሮፕላኑ በአየር ላይ እያለ የውስጥ ግፊቱ በመቀነሱ፣ ድንገተኛ ማረፊያ ለማድረግ ተገዷል ነው የተባለው።

በደረሰው የአየር ግፊት መቀነስ ሳቢያ የታመሙት ሰባት ተሳፋሪዎች ወደ ሙምባይ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሱ የህክምና እርዳታ ተደርጎላቸዋል።

ከመካከላቸውም አንዱ ሆስፒታል ገብቶ ህክምና እንደተደረገለት መረጃዎች ያመለክታሉ።

የአደጋው መንስኤ በምርመራ ላይ ሲሆን፣ የአየር መንገዱ ባለስልጣናት እስካሁን ዝርዝር መረጃዎችን አልሰጡም ተብሏል።

ይህ ክስተት ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በሌሎች አየር መንገዶች ላይ ከተከሰቱ ተመሳሳይ የአየር ግፊት መቀነስ ችግሮች ጋር የሚመሳሰል መሆኑ ተጠቁሟል።

@Yebetube @Fikerassefa

>>Click here to continue<<

YeneTube

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)