TG Telegram Group & Channel
YeneTube | United States America (US)
Create: Update:

ቻይና በሰው አልባ ሠራተኞች የሚተዳደር የኤ.አይ. (AI) አውራ ጎዳና ዳግም ግንባታ አከናወነች

ቻይና 158 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን የቤጂንግ-ሆንግ ኮንግ-ማካዎ አውራ ጎዳና (Beijing-Hong Kong-Macao Expressway) አንድም ሰው ሳይጠቀም ዳግም መገንባቷ ተገልጿል፡፡

በሰው ሰራሽ ብልህነት (AI) የሚቆጣጠሩ ድሮኖች፣ ራሳቸውን የሚያሽከረክሩ የመንገድ አስፋልት ማሽኖች እና ሮቦቲክ ሮለሮች መላውን የሥራ ሂደት መርተዋል ነው የተባለው፡፡

ይህ የኤ.አይ. ስኬት ፕሮጀክቱን በእጅጉ ያፋጠነው ሲሆን፣ ወጪዎችን በመቀነስ እና የሰው ልጅ ለሥራ ሲጋለጥ የሚደርስበትን አደጋ አስቀርቷል ተብሎለታል፡፡

ይህ ስኬት የመንገድ ግንባታ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ከመሆኑ በላይ፣ ለወደፊት የመንገድ ግንባታዎች የሥራ ማስኬጃ ዘዴን የሚያሳይ ፍኖተ ካርታ ሆኗል።

በሥራ ቦታ የሚታዩ የራስ ቁር የለበሱ ሠራተኞች ቁጥር እየቀነሰ፣ ብልህ ማሽኖች ግን እየበዙ ይሄዳሉ ማለት ነው የተባለው፡፡

ይህ መሰል የስራ ልምድ የሰው ልጅ የሥራ ባህሪን ከሥሩ ሊቀይሩት የሚችሉ ሲሆን፣ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ከመፍጠር ባሻገር ሰዎች ይበልጥ ውስብስብና የፈጠራ ሥራዎች ላይ እንዲያተኩሩ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ቢጠቀስም፤ የሥነ ምግባር ጉዳዮች፣ የሥራ መፈናቀል እና የደህንነት ስጋቶች ሊታሰብባቸው የሚገቡ ጉዳዮች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa

>>Click here to continue<<

YeneTube

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)