በጋምቤላ ክልል ሰኞ የሚጀምረውን የ12ተኛ ክፍል ፈተና ለመውሰድ በጉዞ ላይ የነበሩ ሶስት ሴት ተማሪዎች መታገታቸው ተገለጸ!
በጋምቤላ ክልል፤ በመጪው ሰኞ የሚጀምረውን የ12ተኛ ክፍል ፈተና ለመውሰድ በጉዞ ላይ የነበሩ ሦስት ሴት ተማሪዎች እና አንዲት የ13 ዓመት ልጅ በሙርሌ ታጣቂዎች መታገታቸው ተገለጸ።አራቱ ሴቶች የታገቱት በአኝዋ ዞን ጎግ ወረዳ ከምትገኘው ቴዶ ቀበሌ ተነስተው ወደ ወረዳው ዋና ከተማ ፒኝውዶ በእግር እየተጓዙ በነበረበት ወቅት መሆኑ ተጠቁሟል።
ከ13 እስከ 22 ዕድሜ ያላቸው አራቱ ሴቶች በታጣቂዎች የታገቱት ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ አራት ሰዓት ገደማ መሆኑ ሁለት የጎግ ወረዳ የመንግሥት ኃላፊዎች እንደነገሩት ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል።ከአራቱ ሴቶች መካከል ሦስቱ የ12ተኛ ክፍል ተፈታኞች እንደሆኑ የወረዳው የካቢኔ ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አጃክ ኦኮንጎ ነግረውኛል ያለው ቢቢሲ ወደ ፒኝውዶ ከተማ እየተጓዙ የነበረው፤ ነገ ቅዳሜ ከሌሎች ተፈታኞች ጋር በመሆን ፈተናው ወደ ሚሰጥበት ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ለመሄድ ነበር ማለታቸውንም አስነብቧል።
የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንም ትላንት ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በፌስቡክ ገጹ ባጋራው መረጃ "በእግር በመጓዝ ላይ የነበሩ አራት ታዳጊ ልጆች" መታገታቸውን ሪፖርት እንደተደረገለት አስታውቋል፤ እገታው የተፈጸመው "በደቡብ ሱዳን ሙርሌ ዘራፊዎች" መሆኑን ገልጿል።የወረዳው አስተዳደር የፀጥታ ኃይሎችን በማሰማራት ከቀበሌው የሚነሱ ሌሎች ተማሪዎችን በእጀባ እንዳጓጓዘ የካቢኔ ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊው እንደነገሩት ዘገባው አካቷል።
Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
>>Click here to continue<<
