TG Telegram Group & Channel
YeneTube | United States America (US)
Create: Update:

የጋምቤላ ክልል 2017 በጀት ዓመት የወርቅ ምርት መጠን ከአምስት ሺህ ኪሎግራም በላይ መድረሱ ተገለጸ!

-በ2016 የተመረተው 650 ኪሎግራም ብቻ ነበር ተብሏል

በጋምቤላ ክልል በ2017 በጀት ዓመት ዓመታዊ የወርቅ ምርት ከስምንት እጥፍ በላይ ማደጉን የጋምቤላ ክልል የማዕድን ሀብት ልማት አስታወቀ።ዘንድሮ ክልሉ በ12 ወራት አምስት ሺህ 295 በላይ ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ተደርጓል ሲሉ የክልሉ የማዕድን ሀብት ቢሮ ሃላፊ አቶ ኡጁሉ ጊሎ ኡጁሉ ገልጸዋል።

በክልሉ በ2016 በጀት ዓመት የተመረተው የወርቅ መጠን 650 ኪሎ ግራም እንደነበር ቁመዋል፤ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ስምንት እጥፍ የወርቅ ምርት መገኘቱን ያሳያል ብለዋል።በክልሉ በዘንድሮው በጀት ዓመት 2 ሺህ 850 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ለማስገባት መታቀዱን አስታውሰው፣ እስከ ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ አምስት ሺህ 295 ነጥብ 87 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ መግባቱን ተናግረዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በክልሉ የወርቅ ምርት ላይ ከፍተኛ እድገት ማስመዝገቡን ገልጸው፤ ወርቅ አምራቾች የወርቅ ምርታቸውን በቀላሉ ወደ ብሔራዊ ባንክ በማስገባት ተጠቃሚ የሚሆኑበት ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ማለታቸውን ከፕሬስ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።በክልሉ ቀደም ሲል በወርቅ ማዕድን ማውጣት ላይ የተሰማሩት በጸጥታ ስጋት ምክንያት ከአቅም በታች ሲያመርቱ እንደነበር አውስተው፤ በአሁኑ ጊዜ ሰላም በመስፈኑ ወርቅ አምራቾች በሙሉ አቅማቸው ወደ ማምረት እንዲገቡ አድርጓል ብለዋል።በተያዘው የበጀት አመት ስምንት ወራት መንግስት 22 ነጥብ 5 ቶን (22 ሺህ 500 ኪሎግራም) ወርቅ ለውጪ ገበያ መቅረቡ ማስታወቁን መዘገባችን ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa

>>Click here to continue<<

YeneTube

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)