የኤርትራ መንግስት ኢትዮጵያ “ግጭት ለመቀስቀስና ምክንያታዊ ለማስመሰል” ዲፕሎማሲ መልዕክቶችን እየተጠቀመች ነው ስትል ከሰሰች!
የኢትዮጵያ መንግስት ኤርትራ “በኢትዮጵያ ላይ ትንኮሳ በመፈጸም “ እና “ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነትን በመጣስ” ለመክሰስ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ እና ለበርካታ ሀገራት መንግስታት ዲፕሎማሲያዊ መልዕክቶችን ልካለች ስትል ኤርትራ ቅሬታ አቀረበች። ይህም "ግጭት ለመቀስቀስ እና ምክንያታዊ ለማስመሰል የሚደረግ ጥረት አካል ነው" ስትል ከሳለች።
የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ትናንት ሰኔ 19 ባወጣው መግለጫ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ባለፉት ቀናት “የዲፕሎማሲያዊ ዘመቻዎችን አጠናክሯል” ሲል ገልጾ፤ መልዕክቶቹ፤ “እያየለ በመጣው የጦርነት አጀንዳው ላይ ድጋፍ ለማግኘት የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማሳመን ያለመ ግልፅ ዘዴ ነው” ብሏል።
እንደ ሚኒስቴሩ ገለጻ፤ የኢትዮጵያ መንግስት "በርካታ የጦር መሳሪያ ግዥዎች " እና "መንግስትን የማዳከም በርካታ ጥረቶች” ላይ መሳተፏን ገልጿል። “ምንም እንኳን እነዚህ ድርጊቶች ለኤርትራ ሉዓላዊነትና ግዛታዊ አንድነት እንዲሁም ለቀጠናው መረጋጋት ከባድ ስጋት ቢጥሉም፤ ኤርትራ በትዕግስት አልፋለች” ብሏል።
የኤርትራ መንግስት መግለጫውን ያወጣው፤ ትክክለኛነቱ ያለተረጋገጠ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደብዳቤ በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያ መሰራጨቱን ተከትሎ ነው።
ተጨማሪ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8256
@YeneTube @FikerAssefa
>>Click here to continue<<
