TG Telegram Group & Channel
YeneTube | United States America (US)
Create: Update:

"በአምስት ሰነፎች የተነሳ የትግራይ ሕዝብ ለጦርነት መማገድ መቆም አለበት" አቶ ጌታቸው ረዳ

'አንድ ፖርቲ ውስጥ ያሉ አምስት ሰነፎች' ሲሉ የጠሯቸው ግለሰቦች፤ የትግራይን የህልውና ችግር ውስጥ ከተውታል ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሰራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል፡፡አቶ ጌታቸው ይህንን ያሉት ሴንተር ፎር ሪስፖንሲብል ኤንድ ፒስፉል ፖለቲክስ የተሰኘ ድርጅት ባዘጋጀው ውይይት ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ነው።

ድርጅቱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ሰላም፣ ዲሞክራሲ እና ልማት በትግራይ እድሎች እና ፈተናዎቸ በሚል ርዕስ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።በዚህ የውይይት መድረክ ላይም አቶ ጌታቸው ረዳ እና የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መሀመድ እድሪስን ጨምሮ በርካታ የተለያዩ ፖለቲካዊ አቋም ያላቸዉ የትግራይ ፖለቲከኞችና ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች ተገኝተዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ጌታቸው ረዳ፤ "ፖለቲካ ውስጥ ከገባን ጀምሮ እንዲህ ያሉ ውይይቶች ሲካሄዱ ቆይተዋል" ብለዋል።"አሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ የትግራይ ሕዝብ ሰላም ያስፈልገዋል" ያሉም ሲሆን፤ "ሕዝቡ አሁን የህልውና አደጋ የተጋረጠበት ሆኗል" ሲሉ ገልጸዋል።

"አሁን የትግራይ ሕዝብ ልማት ይቆይለት" ያሉት አቶ ጌታቸው፤ "መልማት ችግር የለውም ግን ሕዝቡ የህልውና አደጋ ተጋርጦባታል" ብለዋል። "አምስት እና ሰባት የሆኑ ሰነፎች የትግራይ ህዝብንና ወጣቱን ወደ ጦርነት የሚማግዱበት ሁኔታ መቆሞ አለበት! ለዚህ ደግሞ ዲሞክራሲ የግድ ይላል" ሲሉም ተደምጠዋል።

ይህ መድረክ 'እነዚህ ጥቂት ሰነፎችን በቃችሁ የሚል አይነት ጠንካራ ወይይት የሚደረግበት የመጀመሪያ መደረክ ይሆናል' የሚል ተስፋ እንዳላቸውም ገልጸዋል።በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ሌላው የሰላም ሚኒስትሩ አቶ መሀመድ እድሪስ ናቸው።

በንግግራቸውም "በትግራይ ፖለቲካም ሆነ በሀገሪቱ ያሉ የፖለቲካ ሂደት ላይ በአብዛኛው ከፊት ወጣቶች አይመጡም" ያሉ ሲሆን፤ ይህ ዓይነቱ ውይይት ግን ወጣቶችን ወደ ፊት ለማምጣት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። "በትግራይ ፖለቲካ ውስጥ ይህ የዛሬው ወይይት ታሪካዊ የሆነ ውይይት እንደሚሆን አልጠራጠርም" ሲሉም ተናግረዋል።

"ጦርነት ይበቃ ለማለት ድፍረት ይጠይቃል" ያሉት ሚኒስትሩ፤ "ሰላም ማለት ድፍረት ይጠይቃል፤ ከጦርነት የሚያተርፍ ሕዝብ የለም" ሲሉ ገልጸዋል።መድረኩም በተለያዩ መነሻ ፅሁፎች መነሻነት ሰፋ ያለ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa

27😁15👍2🔥1

>>Click here to continue<<

YeneTube

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)