የኬንያው ተቃውሞ "የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ" እንደሆነ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናገሩ!
የኬንያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ረቡዕ ፣ሰኔ 18/ 2017 ዓ.ም በመላ አገሪቱ የተካሄደውን ተቃውሞ "ሰላማዊ መስሎ የታየ የሽብር ተግባር" እና "የመንግሥት ለውጥ ለማድረግ የተደረገ ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ሙከራ" ነው አሉ።
ሚኒስትሩ ቢያንስ 10 ሰዎች በተገደሉበት ተቃውሞ ፖሊስ ከፍተኛ ኃይል ተጠቅሟል መባሉንም አስተባብለዋል።ኪፕቹምባ ሙርኮሜን የጸጥታ ተቋማት ከፍተኛ የሆነ "ትንኮሳ ቢገጥማቸውም ላሳዩት አስደናቂ ትዕግስት" እና የተካሄደውን "የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በማክሸፍ" ላደረጉት እገዛ አመስግነዋል።
ረቡዕ ዕለት በተካሄደው ተቃውሞ ከተገደሉት 10 ሰዎች በተጨማሪ 300 የፖሊስ አባላትን ጨምሮ ከ400 በላይ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ሚኒስትሩ ገልጸዋል።" በሰላማዊ ተቃውሞ ስም የተካሄደውን ጥቃቶች ፣ ዘረፋዎች፣ ወሲባዊ ጥቃቶች እንዲሁም ውድመት የተፈፀመበትን ጭካኔ የተሞላበት ወንጀል እናወግዛለን" ብለዋል ሚኒስትሩ።
@YeneTube @FikerAssefa
>>Click here to continue<<
