➖➖➖➖➖➖❤️➖➖➖➖➖➖
እውነተኛ የፍቅር ታሪክ
💋 እጠብቅሀለሁ 💋
ያች የቀን ክፍተት :"
ለ እመብርሀን ፀሎት :"
ብርታት እንድትሆነኝ እሷን ልለምናት :"
ስሄድ ወደ አምላክ ቤት :"
እግሬን አደናቅፎኝ :"
ጫማው ተቆርጦብኝ :"
መሀል መንገድ ቆሜ መንገዱ ሳይጠፋኝ :"
የፀሀዩ ሙቀት እግሮቼን ሲያቃጥለኝ :"
አምላክ አንተን ሰቶኝ :"
ለጫማዬ ምትክ በየዋህነቱ ፍቅርህን አድሎኝ:"
ያች ቀን ነበረች ከቀን የተለዬች:"
አንተን በማግኘቴ ነብሴ የታደለች:"
የአላማዬ ስኬት መሰረት የሆነች:"
አወ ያኔ ......ነበር
በባዶ ከመሄድ እግሬ ከመሰበር:"
ሳላስበው መተህ የሰጠኽኝ ክብር:"
በዚህም ቀን......ነበር
መተዋወቃችን የዋለው ቁም ነገር:"
በፍቅር ባንድ ቤት አንድ አልጋ ተኝተን:"
ሀሳብ ተለዋውጠን:"
በእቅፍህ ገብቼ:"
ፍቅርህን ሸምቼ:"
ቀሪውን ዘመኔን ፍፁም ላልለይህ ላንተ ተገዝቼ:"
ይሄው እኖራለሁ ከ ሁሉም ከምንም አንተን አስበልጨ:"
አሁን ግን ...... ☹️
እውነት ነው ለስራ ሄደሀል:"
ከአጠገቤ እርቀሀል:"
ከእቅፌም ወተሀል:"
ከእይታዬም ጠፍተሀል:"
ግን ቃል አለኝ ላንተ ፍፁም እማላጥፈው:"
እስክትመጣ ድረስ አክብሬ እምይዘው:"
በማንም በምንም ፍፁም ማልቀይረው:"
አንተ ለኔ ከሆንክ ለመኖር ምሳሌ:"
እኔም እሆናለሁ ታማኝ ሴት ለቃሌ:"
አወ አብረን ኑረናል ሁለት ሶስት አመት:"
ተራርቀን ጭምር ይሄው ዛሬ ሞላን ድፍን አምስት አመት:"
ምንም ቢሆንብኝ አንተን መጠበቁ የማልችለው ክብደት:"
እንዴትስ አድርጌ አንተን ባየሁ አይኔ ሌላ ልቃኝበት:"
በሳምኩህ ከንፈሬስ ሌላ ልሳምበት:"
እንዴት ነው ሚቻለው ባስለመድከኝ ጣትስ ሌላ ምዳብስት:"
ስማኝ ልማልልህ ይሁንብኝ ቅጣት:"
ካንተ ውጭ ሌላ ወንድ ፍፁም አልመኝም እከተልሀለሁ በምትሄድበት:"
እጠብቅሀለሁ ቃሌ ይሁን ዘበት:"
ፍቅር ይሁን ውርደት....😧😧
┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄
❤️❤️❤️ #Share ❤️❤️❤️
😘😍@Yenefekir😘😍
💝@Yenefekir💝
>>Click here to continue<<