TG Telegram Group & Channel
የሜሪ አጫጭር ተረኮች | United States America (US)
Create: Update:

አዲስ አበባ እንደአደግኩበት ክፍለሀገር በጉልበቴ ብቻ የምከበርበት ሀገር አለመሆኑን ከረፈደም ቢሆን አውቄያለሁ። ከኛ ሰፈር የአባቴ ገዳዮች ሰፈር እኩዮቼን አጅቤ ሄጄ ጠላቴን አደባይቼ ልምጣ ብዬ እንደማቅደው የስልጣን ሽልማታቸውን የሚያጣጥሙ ያባቴን ገዳዮች በር አንኳኩቼ እንደማልገድላቸው አውቄያለሁ። ሁሉም ነገር ከባድ እንደሆነ ያወቅኩት እንኳን እኔ ቀርቶ ገጠር ሲመጣ <ሚንስትር ሙሉሰው ዘመዴ ነው! እኛ ቤት ይመጣል> እያለ የሚበጠረቀው የካራቴ አሰልጣኛችን እንኳን የሚንስትሩ ቤት ሰማይ ይሁን ምድር ካለማወቁ ቤተሰቦቹ እንኳን ያለምክንያት የማያገኙት ሩቅ ሰው መሆኑን ስረዳ ነው። ከሀገሬ ስወጣ እገድላቸዋለሁ ብዬ ስም ዝርዝራቸውን የፃፍኳቸው እና ስማቸውን ማወቅ ሳልችል በምልክት ጭንቅላቴ ውስጥ የመዘገብኳቸው ሰዎች ዋና ዋናዎቹ እዚሁ አዲስአበባ ተሿሹመው ሲኖሩ የተቀሩት የት እንዳሉ አላውቅም!!!! ብቻ ማናቸውንም ማግኘት ትንሽዬ ማስታወሻዬ ላይ ስማቸውን ፅፎ እንደመያዝ ቀላል እንዳልሆነ ገብቶኛል። በየቀኑ ግን ወደቤቴ ስገባ ያቺን በመተሻሸት ብዛት ቀለሟን የቀየረች ማስታወሻ ደብተር ገልጬ በኑሮ ደፋ ቀና ጠላቶቼን እንዳልረሳ አስታውስባታለሁ። ቀኑ እንጂ የሚረዝመው እስከእድሜዬ ማለቂያ ድረስም ቢዘገይ እነርሱን ሳላገኝ እንደማልሞት ለራሴ በየቀኑ እነግረዋለሁ።

ህልሜን ለማሳካት (በቀልን ህልም ማለቴ አይግረማችሁ!! ያው ለማሳካት እስከምንም ጥግ የምትደክሙለት ዓላማ መግደልም ቢሆን ህልም አይደል?) አዲስአበባ ላይ ጎበዝ አላሚ ተኳሽ እና እንደንፋስ የፈጠንኩ ካራቲስት መሆን ብቻውን እንደማይበቃኝ አውቄያለሁ። አዲስ አበባ ላይ ከምንም ነገር በላይ እነዚህ ሶስቱ ወይም ከሶስቱ አንዱ ያለው አቅም አለው። ሀብት ፤ ስልጣን እና ዝና!! ከሶስቱ በጥቂቱም ቢሆን ተስፋ ያለኝ ሀብት የሚለው ላይ ቢሆንም እንዴት? የሚለውን ግን እስክደርስበት ድረስ እቅዱ አልነበረኝም። ምንም ዓይነት የቅብጠት ምኞት ስላልነበረኝ የማገኘውን ገንዘብ ለኪዳን ያስፈልገዋል የምለውን ነገር ከማሟላት የተረፈኝን አስቀምጣለሁ። ጎን ለጎን መኪና መንዳት መማር እና ከሰባተኛ ክፍል የተውኩት ትምህርት አማርኛ ከማንበብ እና መሰረታዊ የሂሳብ ስሌት ከመስራት የማያሻግር በመሆኑ ቢያንስ መሰረታዊ የቴክኖሎጂ ትሩፋቶችን መጠቀም የሚያስችለኝ እውቀት ለመገብየት ሰውየውን ተከትዬ ሆቴል እና ጭፈራ ቤት ደጅ በምገተርባቸው ቀናት እየቀረሁም ቢሆን የማታ ትምህርት ቤት ገባሁ። ውሉ ሲጠፋብኝ ኪዳን እቤት እቤት ያስጠናኛል።

ለዓመት ከ6 ወር ደላላው እንዳለው ሰውየው በአጀብ ከመሄድ ልክፍቱ ውጪ ሀገር ውስጥ በነበረበት ጊዜ አንድም አይደለም ሊያጠቃው ጮክ ብሎ የተናገረው ሰው አልሰማሁም። ከዚህ በኋላ የሆነ ቀን ዱባይ ትልቅ ስብሰባ መኖሩን እና እዛ ሲሄድ ሀብትና ጉልበቱን ማሳየት ስለሚፈልግ ሁላችንንም አስከትሎ እንደሚሄድ ተነገረን። ፓስፖርት እንኳን ስላልነበረኝ በሰውየው ጉዳይ አስፈፃሚዎች በኩል ያለቀጠሮ ፓስፖርቴ አልቆ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰውየው የግል አውሮፕላን ተሳፈርኩ። ይሄን ጊዜ የግድ ቀሚስ መልበስ እንዳለብኝ ሲነገረኝ ከሀገር የመውጣት ጉጉቱ ስለበለጠብኝ ተስማማሁ!! ለመጀመሪያ ጊዜ ለረዥም ቀናት ከኪዳን ተለይቼ የቆየሁበት ጊዜ ስለነበር ትቼው መሄዱ ሀሳቤን ለመቀየር እስኪፈታተነኝ ከብዶኝ ነበር። የሚከፈለኝ ብር ብዙ ማድረግ የሚያስችለኝ በመሆኑ ከኪዳን ጋር ተነጋግረን እቤት የምታግዘው ሰራተኛ ቀጥሬለት ሄድኩኝ። እስከዛ ሰዓት ድረስ ሰውየው ምን ይስራ፣ ምን ይኑረው፣ ለምን ኢትዮጵያ ይኖራል? የማወቅ ፍላጎት ኖሮኝም አያውቅም!! የግሉ አውሮፕላን እንዳለው ሳውቅ ግን የገቢ ምንጩን የማወቅ ፍላጎት ኖረኝ። ዱባይ ስንደርስ የአንድ ምግባቸው ዋጋ የእኔን የወር ደመወዝ የሚሆን ሆቴል ብቻውን የያዘው እስኪመስል አንድ ፍሎር ላይ ሰፈርን። አስተናጋጆቹ መሬት በግንባራቸው ሊነኩ እስኪቀራቸው ሰግደው ነው ሰላምታ የሚያቀርቡት።

ሰውየው በሀብቱ የተፈራ እና የተከበረ ልጥጥ ነው። የተለያዩ ሀገራት ላይ ለቁጥር የታከቱ ንብረቶች እና ኢንቨስትመንቶች ባለቤት ነው። በአረብ ሀገራት ውስጥ ታላቅ የተባለ የነዳጅ ካምፓኒ ውስጥ ትልቅ ስቶክ ያለው ባለስልጣኖቹ ሁሉ የሚሽቆጠቆጡለት ሰው መሆኑን ስብሰባው አዳራሽ ሲገባ አስተዋልኩ። አዲስአበባ የሚኖረው ሀገሪቷ ላይ ኢንቨስት ማድረግ ፈልጎ የኢትዮጵያ መንግስት መንገዱን ስላላቀለለለት እግረመንገዱን በሴቶቻችን እየተዝናና ነው ገባ ወጣ የሚለው።

የዛን ቀን ማታ አንደኛውን አቅም (ሀብት) መገንባት እንደምችል እርግጠኛ ሆንኩ። ስብሰባውም ላይ እኔ ከውጭ ጠባቂ ነበርኩ። የተቀመሱት ናቸው አብረውት አዳራሽ የገቡት። የዛን ቀን የሚዘገንነኝን ሴትነቴን ለማሰብ በትንሹ ገርበብ ያለ ልብ ኖረኝ። ቢሆንም ሀሳቡን ለመፈፀም እሩቅ እንደሆነ እያሰብኩ በሚቀጥለው ማታ እድል ወይ አጋጣሚ ብቻ ክስተት ሆነ። ሰውየው የሁለተኛውን ቀን ስብሰባ ጨርሶ ሆቴሉ ካረፈ በኋላ ወክ ካልወጣው ብሎ ቀበጠ። እኔን ጨምሮ ስምንት ሴት እና ሁለት ጠብደል ወንድ አስከትሎ የተቀሩት ምን እንዲጠብቁ እንደሆነ ባላውቅም ሆቴል ውስጥ ሲጠብቁ እንዲቆዩ አስደርጎ ወጣ!! ከስር ከስሩ ጡል ጡል የሚል ትዕዛዙን የሚቀበል እና የሚያቀብል አንድ ሲያዩት ግዙፍ የሚመስል ሲሽለጠለጥ ቡችላ የሚያክል ሰውዬ ከስር ከስሩ አይለየውም። ከፊት አራት ሁለት ከጎን የተቀረነው ከኋላ ሆነን ከሆቴሉ ወጥተን ትንሽ እንደሄድን (እኔ መጨረሻ ላይ ነኝ) ሰው በበዛበት ጎዳና ሚኒባስ ከሚመስል ዝግ መኪና ውስጥ አንድ እንደእርሱ የለበሰ ባለሀብት የሚመስል ጥቁር ሰውዬ የሰማይ ስባሪ በሚያካክሉ ስድስት በኋላ ላይ ናይጄሪያውያን መሆናቸውን ያወቅኳቸው ወንዶች ታጅቦ ወረደ። የኛውን ሰውዬ ያጀብነው እኔን ጨምሮ ወደሽጉጣችን እጃችንን ላክን ……. ግማሾቻችንም ሰዎቹ ላይ ደቀንን!! የኛው ሰውዬ እንድንረጋጋ ምልክት ሰጥቶን ከሰውየው ጋር በወዳጅነት ሰላም ተባብለው የሰውየውም ጠባቂዎች ከኛ ጋር ተደባልቀው ሁለቱ እያወሩ መጓዝ ያዙ።

>>Click here to continue<<

የሜሪ አጫጭር ተረኮች

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)