TG Telegram Group & Channel
ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል | United States America (US)
Create: Update:

🔷 ዘካተል ፊጥር ምንድን ነው🔹

🕰 ፈትዋ ቁጥር : 268

📮 #ጥያቄ↶

⭕️ ዘካተል ፊጥር ምንድን ነው? ለምንድን ነው የተደነገገው? ቢብራራልን

#መልስ↶

☑️ ዘካተል ፊጥር በሙስሊሞች ላይ ግዴታ ከሆኑ ዘካዎች መካከል አንዱ ሲሆን ከዒደልፊጥር ሶላት #በፊት ወይም ረመዷን ከመጠናቀቁ በፊት የሚሰጥ ነው። ይህ ዘካ አቅም ባለው ሁሉ ላይ #ግዴታ ነው። ዘካተል ፊጥርም ሶደቀተል ፊጥርም ተብሎ ይጠራል። ስያሜው ወደ ፊጥራ የተጠጋበትም ምክንያት ግዴታ የተደረገበት ምክንያት ስለሆነ ነው። ማለትም ዘካተል ፊጥር #ከረመዳን ወር ፆም መጠናቀቅ ጋር በተያያዘ ግዴታ የሚሆን የዘካ አይነት ነው፡፡

☑️ ከሌሎች ዘካዎች የሚለየውም በገንዘብ ላይ ሳይሆን #በግለሰብ ላይ ግዴታ የሚሆን መሆኑ ነው። ማለትም ይህ ዘካ ግዴታ የተደረገው የፆመኞችን ነፍስ #ለማጥራት እንጅ ልክ እንደ ትልቁ ዘካ ገንዘብን ለማጥራት አይደለም።

📚 ኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ አንሁ እንዲህ ይላል: " ‹‹የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ከተምር ወይም ከገብስ አንድ ‹‹ሷዕ›› (ሷዕ የመስፈሪያ አይነት ሲሆን በዘመናዊ መለኪያ አንድ‹‹ሷዕ›› 2.04-2.5 ኪ.ግ ይመዝናል፡፡) በእያንዳንዱ ሙስሊም፤ ባሪያ፣ ጨዋ (ባሪያ ያልሆነ)፣ሴት፣ ህፃን፣ አዋቂ ላይ ግዴታ አድርገዋል፡፡ እንዲሁም ሰዎች ወደ (ዒድ) ሰላት ከመውጣታቸው በፊት ለሚገባቸው ሰዎች እንዲደርስ #አዘዋል፡፡›› (ቡኻሪና [1503] ሙስሊም [984] ዘግበውታል)

☑️ የተደነገገበት #ጥበብ ድሆች በባዕሉ (ዒድ) እለት ሰዎችን ከመለመን #እንዲድኑና የእለቱ ደስታ ተካፋይ እንዲሆኑ ማድረግ እንዲሁም በፆም ወቅት ተከስተው ላለፉ አንዳንድ ጉድለቶች (ግድፈቶች) #ማሟያ እንዲሆን ነው፡፡ ይህን አስመልክቶ ዐብደላህ ኢብን አባስ እንዲህ ይላሉ፡፡

📚 ‹‹የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ዘካተል ፊጥርን ለፆመኛ ለ ‘ለግዉ’ (ጥቅም ለሌላቸው ውድቅ ንግግሮችና ተግባሮች) እና ለ ‘ራፈስ’ (ፆታዊ ስሜትን ቀስቃሽ ለሆኑ ንግግሮች) #ማፅጃ፤ ለምስኪኖች (ድሆች) #መብል ሲሆን በግዴታ መልኩ ደንግገውታል፡፡ ስለዚህም ከኢድ ሰላት #በፊት (ዘካውን በመስጠት ግዴታውን የተወጣ) ተቀባይነት ያለው ዘካን ሰጥቷል፤ ከኢድ ሰላት #በኋላ ዘካውን የሰጠ ከሌላ ግዴታ ያልሆነ ሰደቃ አንዱ እንደሆነ ይታሰብለታል፡፡›› (አቡዳውድ [1609] እና ኢብኑ ማጃህ [1827] ዘግበውታል)

•┈┈•◈◉❒❒◉◈•┈┈•

🗂 #ምንጭ↶

📘 መጅሙዑል ፈታዊ ለኢብኑ ባዝ ፣ 14/32 ፣ 14/197 ፣ 📕መጅሙዑል ፈታዊ ለኢብኑ ዑሰይሚን ፣ 18/258

◈•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•◈
https://hottg.com/yeilmkazna

>>Click here to continue<<

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)