TG Telegram Group & Channel
ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል | United States America (US)
Create: Update:

ታይዋንን ለመጠቅለል ከሰባ አምታት በላይ አድፍጣ የምታደባው ለታይዋን የሚሆን አቅም አጥታ አይደለም። ከታይዋን ጎን ከቆምችዋ አሜሪካ በኩል የሚመጣባትን ጣጣ ሽሽት እንጂ። ሙስሊሙ ዓለም አቅሙ ከቻይና በጣም ያነሰ ነው። ቻይና ለዚህ አላማ በሁሉም ዘርፍ አቅሟን ለማጎልበት ሌት ከቀን እየተጋች ነው። እኛጋ ደግሞ መካሪ ዑለማዎቹን እያብጠለጠለ፣ ከንቱ ቀረርቶ እያሰማ ደካማ ሃገራቱን ከጠላት ቀድሞ ያፈርሳል፤ እጁን በእጁ ይቆርጣል። ይህንን የተሳከረ አካሄዱንም ጀብድ አደርጎ ይኮፈስበታል።
እንደሚታወቀው የሙስሊም ዓለም መሳሪያ ሸማች እንጂ አምራች አይደለም። በገንዘቡ ለሚገዛውም ብዙ ቅድመ ሁኔታ ይቀመጥበታል። እንዲያውም ብዙዎቹ መሳሪያ መተኮስ፣ ሰራዊት ማዝመት ሳያስፈልግ ጠላት እነዚህን እንጭጮች በመጠቀም ሰላማቸውን ያናጋቸው ናቸው። እነዚህ ወፈፌዎች ግን ጉዳዩን ከሴትና ህፃናት መሃል አድፍጦ የአጭር ርቀት ሮኬቶችን በማስወንጨፍ የሚሞከር አድርገው ያስባሉ። በአጥፍቶ መጥፋትና በትንንሽ ሮኬቶች/ድሮኖች ጥቃት ጊዜያዊ ቡረቃ እንጂ ዘላቂ ድል አይመጣም። ይሄ ቅዠት ነው። ጠላትማ ምን ያድርግ? እነዚህ አሉ እንጂ ጠላት ወደ ሙስሊም ሃገራት እንዲገባ ተልእኮ ፈፃሚ የሆኑ ወልጋዶች!!
“ምሳርማ ምን ያርግ * የብረቶች ልጅ
ያ የኛ ወልጋዳ * አስጨረሰን እንጂ!!”
ዑለማዎች “ጂሃድ የኢማንም፣ የትጥቅም፣ የሰው ሃይልም ዝግጅት ይፈልጋል” ማለታቸውን በመቃረን “እነ ሶላሑዲን,… አሽዐሪዮች ነበሩ” ይላሉ። የኢማን ዝግጅት አያስፈልግም ለማለት ነው እንግዲህ ይሄ የሚቀርበው? “ተመጣጣኝ ወይም ተቀራራቢ አቅም መኖር ሸርጥ አይደለም። ሶሐቦቹም በቁጥር ትንሽ ሆነው ነው የተዋጉት” ይላሉ፣ እነዚህ የሚዲያ ላይ ነብሮች። በመጀመሪያ የዑለማዎቹን ንግግር ለትችት በሚመቻቸው መልኩ ነው አዛንፈው የሚያቀርቡት። ደግሞ’ኮ አብዛኞቹ ከሶሻል ሚዲያ ቀረርቶ ያለፈ ሙከራም የላቸውም። በተለይ ደግሞ የኛዎቹ። እስኪ ከነዚህ በያመቱ የፍልስጤምን ጉዳይ ለቡድናዊ ፕሮፓጋንዳ ከሚጠቀሙ አካላት ውስጥ ወደ እስራኤል የሚዘምት ጥቀሱ? እዚያው ፍልስጤም ውስጥ ከሚንደፋደፉ ደካማ ቡድኖች ውጭ እራሳቸውን ወደ ሰለፊያ የሚያስጠጉ ተውሳኮችን ጨምሮ፣ አይሲስ፣ አልቃዒዳ፣ ኢኽዋን፣ ቦኮ ሀራም፣ ... በፍልስጤም ጉዳይ ይነግዳሉ እንጂ እስራኤልን አይዋጉም። 
ደግሞስ የኢማን፣ እንዲሁም ከትጥቅና ከሰው ኃይል ደግሞ ምክንያታዊ የሆነ ዝግጅት ያስፈልጋል ማለት እንዴት ያስወቅሳል?! እና ጠላት ባካፋና በዶማ ነው የሚሸነፈው? ጠላት ባመረተው መሳሪያ እየተታኮስክ መሃል ላይ “አንዴ አቁሙ! ጥይት ጨርሻለሁ” ልትል ነው? ጂሃድን የህፃናት ጨዋታ አስመስሉት’ኮ! ፍልስጤሞችን ውሰዱ! ለፍልስጤማዊያን ተፈናቃዮች ከፍተኛውን እርዳታ የሚያቀርቡት እነማን ናቸው? አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት! ኤሌትሪክና የነዳጅ አቅርቦት እንኳ ከእስራኤል’ኮ ነው የሚገዙት። ከዚህ በላይ አቅመ ቢስነት አለ?! በዚህ አቅም ተሁኖ ነው ስለ ጂሃድ የሚወራው? እሱ በታንክ አንተ በድንጋይ ሆነህ ነው ድል የምትጠብቀው? እስካፍንጫው የታጠቀን ወታደር ቀይ ካርድ ስላሳየኸው የሚሟሟ ይመስለሃል? ጂሃድን በዚህ መልኩ ነው የምትረዳው? ሱብሓነ’ላ፞ህ!! መቼም የምፅፈው ለፍልስጤማውያን እንዳልሆነ ግልፅ ነው። የምፅፈው ይህን ክስተት እያስታከኩ ዑለማዎችን ስለሚያንቋሽሹ አካላት ነው። የሚገርመው ከነዚህ ዋልጌዎች ቅርሻት ስር የሚልከሰከሱ “ሰለፊ ነን” ባዮች መኖራቸው ነው። አንድ ሰው የሆነን ዓሊም አቋም ቢነቅፍ ወግ ነው፣ አቅሙ ካለው። በዚህ መልኩ ከዑለማዎች መርጦ ሰለፊዮቹን በጅምላ የሚዘረጥጥ፣ እልህን መንሃጁ ያደረገ፣ ከሰለፊዮች ጋር መፋጠጥን እንደ ጀብድ የሚቆጥር፣ ከዑለማእ ንግግር ውስጥ አቃቂር ማውጣትን፣ ‘ሰቀጧት’ መልቀምን ንቃት ያደረገ ከንቱ ፍጡር ማየት ነው የሚደንቀው።
ደግሞም የሰው ኃይል ቁጥርም ቢሆን እነዚህ ስሜት ያሰከራቸው አካላት እንደሚስሉት ሳይሆን በተጭባጭ ከግምት ይገባል። ይሄው ቁርኣናዊው ማስረጃው፦
يَـٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ حَرِّضِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ عَلَى ٱلۡقِتَالِۚ إِن يَكُن مِّنكُمۡ عِشۡرُونَ صَٰبِرُونَ يَغۡلِبُواْ مِاْئَتَيۡنِۚ وَإِن يَكُن مِّنكُم مِّاْئَةٞ يَغۡلِبُوٓاْ أَلۡفٗا مِّنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِأَنَّهُمۡ قَوۡمٞ لَّا يَفۡقَهُونَ
“አንተ ነቢዩ ሆይ! ምእምናንን በመዋጋት ላይ አነሳሳቸው፡፡ ከናንተ ውስጥ 20 ታጋሾች ቢኖሩ 200ን ያሸንፋሉ፡፡ ከናንተም 100 ቢኖሩ ከነዚያ ከካዱት እነሱ የማያውቁ ህዝቦች ስለሆኑ 1,000ን ያሸንፋሉ።” [አል አንፋል፡ 65]
አስተውሉ! ንፅፅሩ አንድ ለአስር ነው። ሊያውም ተዋጊን ከተዋጊ ጋር። አሰስ ገሰሱን ሁሉ ሂሳብ እንዳታስገባ!! ቀጠለ፦
ٱلۡـَٰٔنَ خَفَّفَ ٱللَّهُ عَنكُمۡ وَعَلِمَ أَنَّ فِيكُمۡ ضَعۡفٗاۚ فَإِن يَكُن مِّنكُم مِّاْئَةٞ صَابِرَةٞ يَغۡلِبُواْ مِاْئَتَيۡنِۚ وَإِن يَكُن مِّنكُمۡ أَلۡفٞ يَغۡلِبُوٓاْ أَلۡفَيۡنِ بِإِذۡنِ ٱللَّهِۗ وَٱللَّهُ مَعَ ٱلصَّـٰبِرِينَ 
“አሁን አላህ ከእናንተ ላይ አቀለለላችሁ፡፡ በናንተ ውስጥም #ድክመት መኖሩን አወቀ፡፡ ስለዚህ ከናንተ 100 ታጋሾች ቢኖሩ 200ን ያሸንፋሉ፡፡ ከናንተም 1,000 ቢኖሩ በአላህ ፈቃድ 2,000ን ያሸንፋሉ፡፡ አላህም ከታጋሾቹ ጋር ነው፡፡” [አል አንፋል፡ 66]
ልብ በሉ! እዚህ ላይ ደግሞ አንድ ለሁለት ሆነ። ለማቃለሉ የቀረበው ምክንያት ሙስሊሞች ዘንድ ድክመት መኖሩ ነው። ዛሬስ ያለው ድክመት እዚህ ላይ ከተጠቀሰው የባሰ ነው ወይስ የተሻለ? እጅግ በርካታ ዓሊሞች ናቸው “የዛሬ ሙስሊሞች ከድክመታቸው አንፃር ሲታዩ የመካ ዘመን ምሳሌ ላይ ነው ያሉት” የሚሉት። የሙስሊሙ ቁጥር ከቢሊዮን በላይ መሆን ከጦርነት አንፃር ቁም ነገር ሆኖ የሚነሳ አይደለም። የጠላትን ዝግጅት በሚገዳደር መጠን ዘመኑን የዋጀ ለሌሎች የሚተርፍ የሰለጠነ ኃይል ሊሆን ቀርቶ ለራሱም መሆን አቅቶታል። በ1948ቱ የዐረብ እስራኤል ጦርነት ጊዜ ዮርዳኖስ ባይዘልቅም በጥቂት ሰራዊት ከሌሎቹ ዐረብ ሃገራት የተሻለ ድል አስመዝግባ ነበር። ለዚህም በቀዳሚነት የሚነሳው ምክንያት በእንግሊዝ የሰለጠኑ ጠንካራ ወታደሮች ስለነበሯት ነው። ከሰመመንህ ንቃ ወንድሜ! የፈለገ ብትደፈን ቴኳንዶ እንኳ ቁም ነገር ሆኖ ክትትል በሚደረግበት ሃገር እየኖርክ “በቂ የሰው ኃይል አለን” “ዋናው በቁጥር መብዛት አይደለም” እስከማለት አትጨፈን! አዎ! የቁጥር ብዛት ሸርጥ አይደለም። በአላህ ፈቃድ ስንት ትልቅ ጭፍራ ጠንካራ ኢማን ባለው ትንሽ ጭፍራ ተሸንፏል?! ከመሆኑም ጋር “የኢማንም፣ የቁስም ዝግጅት እስከምናደርግ እንታገስ። አሁን ባለንበት ሁኔታ ሙስሊሞችን መማገድ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያደላል” ማለታቸው በምን አግባብ ነው እንደ ፍርሃት የሚቀጠረው?
ደግሞም መሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ እየነገርኩህ እንጂ በፍርሃት ቆፈን እንድትንቀጠቀጥ እያስፈራራሁህ አይደለም!! አቅምን ማወቅ ብስለት እንጂ ፍርሃት አይደለም። አቅምህን ስታውቅ ነው ለተሻለ የምትዘጋጀው። ሰላም!!

>>Click here to continue<<

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)