#በሁለቶቹ በዓሎች መካከል ያላቸው ልዩነት የሚከተሉት ናቸው።
1/ #በዒደል_ፊጥር ቀን ማረድ ግዴታም ሱናም ተወዳጅም አይደለም‼️
#በዒደል_አድሐ ቀን ግን ለቻለ ሰው ማረድ ግዴታ ነው✅
2/ #በዒደል_ፊጥር ቀን ተክቢራ ሚጀመረው የፆሙ ጨረቃ ሲያበቃ ማታ ወይም የዒዱ ቀን ጧት ነው።
#የዒደል_አድሐ ቀን ግን ጨረቃው ከታዬ ጀምሮ እስከ_14 ቀን አካባቢ ተክቢራ ይደረጋል።
3/ #የዒደል_ፊጥር ቀን በእያንዳንዱ ሰው ላይ አራት እፍኝ ጥሬ እህል ለድሃዎች ከሶላት በፊት መስጠት ግዴታ ነው።
#የዒድል_አድሐ ቀን ግን ይህ ተግባር ግዴታም ተወዳጅም አይደለም።
4/ #የዒደል_ፊጥር ቀን ፈርድ(ግዴታ)ሶላት ከተሰገደ ቡሃላ ተክቢራ አይደረግም
#የዒደል_አድሐ ቀን ግን ከግዴታ ሶላት ከተሰገደ ቡሃላ ተክቢራ ይደረጋል ያውም ለቀናቶች ያክል
5/ #የዒደልል_ፊጥር ቀን ጧት ላይ ወደ መስገጃው ሜዳ ሲወጣ ቴምር በልቶ መውጣት ሱና ነው
#የዒደል_ አድሐ ቀን ግን እርድ ሚያርድ ሰው ከሆነ ሳይበላ እንድወጣ ነው የታዘዘው።
6/ #የዒደል_አድሐ ላይ ገና ጨረቃው ሲታይ ጀምሮ እርድ አርዳለሁ ብሎ የወሰነ ሰው ከፀጉሩ ከጥፍሩ ምንም ሊነካካ(ሊቆርጥ)አይፈቀድም
#የዒደል_ፊጥርን አስመልክቶ ግን ምንም ነገር የለበትም ማለት እንደፈለገ ጥፍሩንም ብብቻውን ማፅዳት ይችላል።
@abumuazhusenedris
@abumuazhusenedris
>>Click here to continue<<