TG Telegram Group Link
Channel: ጥብዓተ አይሁዳውያን
Back to Bottom
አሁንም ሳይህ ያገረሽብኛል እቀፊው እቀፊው አውሪው አውሪው ይለኛል

ጥንዶች ባየው ነገዬን ባለምኩ ቁጥር ፊትህ ይታየኛል ………………😞

ግን አንድ ነገር አውቃለው አንተ ትላንቴ ነህ💔
እየሞትኩም ቢሆን እኖራለው እንጂ መቼም ወዳንተ አልመለስም…
በጣም ያማል
❤️ በንፁህ ልብ የምትወደው ሰው
ሁለተኛ ምርጫ አድርጎ ሲይዝህ
ከማየት የከፋ ነገር የለም ...
💔 እራስህን 2ተኛ ምርጫ አታድርግ
እንዲያደርግህም ለማንም አትፍቀድ
አንደኛ ሁን ወይም ይቅርብህ ።
አንዳንዴ መተው የሌለብንን ሰው ትተናል ምክንያቱም ከሱጋር የምናደርገው ነገር ውስን ስለሆነ💔
ከመጀመርያው የልብሽ ስብራት ካልተማርሽ
አንድ አይነት ሰው በተለያየ ሰውነት እየመጣ ልብሽን ይሰባብረዋል!

💔
❣️ ❣️ ❣️

​​የይሁዳ ፍቅር ይቅር
━━━━❤️━━━━

❤️ ፍቅር ❤️ በከንፈር መሳም ብቻ ከሆነ የይሁዳ ፍቅር ይቅርብን። ስትወደኝ በከንፈሯ የሳመችኝ ስትጠላኝ በእጇ አሳልፋ ትሰጠኛለች። ፍቅር 💵 ገንዘብ💵 ከሆነ ነጋዴ ፍቅረኛ አያስፈልግም። ተከፍሎኝ የምወደድ...💰 ወርቅ 💰.. አይደለሁም። ስጠላም የምሸጥ 👕 ሰልቫጅ 👕 አይደለሁም። ፍቅር እውር ከሆነ በስሜት ጨለማ መፈቀር አልፈልግም። ፍቅር ውበት ነው። ውበት ደግሞ የልዩነት ውህደት ነው። ጠንካራ ፍቅር በልዩነት የሚሳል ስዕል ነው። ድክመት የጥንካሬ ሸራ ሲሆን በፍቅር ይሸፈናል። አውቆ የተሸፈነ ሲገለጥ አያስጠላም፡፡ ተደብቆ የተሸፈነ ሲገለጥ ያስደነግጣል። መወደድ የምፈልገው በጥንካሬዬ አይደለም። በድክመቴም የምትወደኝ እሷ የፍቅር ውበት ናት። ዛሬ በጥንካሬህ የወደደህ ነገ ስትደክም ይነሳብሀል። ድክመትህን ሸፍነህ ለፍቅር ከቀረብክ ያለ ምሽግ እንደ ሚታኮስ ወታደር ነህ። ድክመትህ ሲጋለጥ ተመተህ ትወድቃለህ። ለመፈቀር ብለህ አታስ መስል። አስመ ስለህ በቀረብከው ተወደህ ከምትጠላ ራስህን ሆነህ ብትኖር የሆንከውን የምትወድልህን አታጣም። በዚህ ግዜ ፍቅር ውበት ሆኖ ያሥደስትሀል።
💔ሰላም አጥቶ ህመሙን እየቻለ ህይወቱን በስቃይ በሚያሳልፈው ላይ ሰላም ይስፈን!😔
😰አማላጅ ማን ይሆን ማንን ልላክብህ
ጭንቀቴ ቢገባህ ቢራራልኝ ልብህ😰
የሚያምረው ምስልሽ ልቤ ላይ ተሰንቅሮ
ልፍቀው አልቻልኩም አይወታም ከአይምሮ
ያኔ ስደነግጥ አይዞሽ አንዳላልከኝ
ዛሬ አይን ላፈር ብለህ ተለየከኝ
አልገባኝም እኔ ምንድነው ሚስጢሩ
ልብህ ከኔ ርቆ ወዲያ መሻገሩ
ክረምቱም በረታ ቀዘቀዘ ቤቱ
የናፈቀ ልቤ በረደው በብርቱ
እሳት ዳር ብቀመጥ ገላዬን ላሞቀው
የናፈቀሽ ልቤ አለ እንደበረደው😔😔
ክረምቱም በረታ ቀዘቀዘ ቤቱ
የናፈቀ ልቤ በረደው በብርቱ
እሳት ዳር ብቀመጥ ገላዬን ላሞቀው
የናፈቀሽ ልቤ አለ እንደበረደው😔😔
👉ጥንዶች ልታነቡት ግድ ይላል፡፡

በብዛት በአንድ የፍቅር አጋር እስከ መጨረሻው መዝለቅ እና በፍቅር አጋር ላይ ሌላ ካልተጀነጀነ ወይም በሌላ ወንድ ካልተጀነጀነች እንደ ፋርነት😏 የሚታይበት ጊዜ ላይ ነው፡፡ ያለነው ይህ ደሞ በያዝነው ነገር አለመርካታችንን ነው የሚያሳየው፡፡ አጠገባችን ያለው ፍቅረኛ ተራ ይሆንብናል ሌላ ሰው ስናይ ወይም ሌላ ሰው ሲቀርበን እሱ ጋር አዲስ ነገር ያለ ይመስለን እና እምነታችንን በልተን በድብቅ ግንኙነት እንጀምራለን፡፡ሴት ከሆነች የፍቅር አጋሯ ላይ እንደድሮ ፍቅር እንክብካቤ መስጠት ትቀንስበታለች ፍቅረኛዋ ከሌላ ወንድ ጋር እያወዳደረችው መሆኑን እና መዋሸቱን ሲያውቅ😢 መለያየት ይፈጠራል፡፡ፀብ መፈጠሩ ለሷ ምንም አይመስላትም ምክንያቱም ለጊዜው ለሷ ከዛኛው የተሻለ ወንድ ያገኘች ስለሚመስላት የዛኛው ጥቅሙ ሚታወቃት ጥሩ ሰው መስሎ የበግ ቆዳ ለብሶ የቀረባትን ተኩላ ባህሪው እያደር ሲቀየርባት ያኔ የዛኛው ጥቅም በደንብ ይገባታል፡፡

ጥንዶች አትሳሳቱ አጠገባቹ ያለው ሰው በፍቅር ህይወታቹ ውስጥ ምርጥ እና ምርጥ የፍቅር አጋራቹ ነው ወይም ናት፡፡እሱ በቂሽ ነው እሷም በቂክ ናት😍ፀባይ አለው/አላት? ፍቅር አለው/ አላት? ታማኝ ነው እሷም ናት ? መልስህ አዎ ከሆነ እና ከዚህ በላይ ምን ትፈልጋለህ አንቺስ ከዚህ በላይ ምን ትፈልጊያለሽ? መቼም ቢሆን ይህን አይነቱን የፍቅር አጋራቹን ከሌላ ሰው ጋር እንዳታወዳድሩት፡፡ ዳግመኛ ብትፈጠር እንደሷ አይነት ልጅ ላታገኝ ትችላለክ አንቺም ዳግመኛ እንደሱ የሚሆንልሽን ወንድ ላታገኚ ትቺያለሽ፡፡ታማኝ ሰው በማይገኝበት ዘመን ታማኝ ሰው ማግኘት እድለኝነት ነው😇ምን አልባት ፈጣሪ በህይወትሽ የሰጠሽ ታማኝ እና እውነተኛ ሰው እሱ ሊሆን ይችላል ላንተም እንደዛው፡፡ ስለዚህ እዚም እዛም መመልከቱን ተዉና የያዛቹትን የፍቅር ግንኙነት ያለ መሰላቸት ጠበቅ አርጉት፡፡
"የሚወዱት ሁሉ ራሱ እንጂ መታሰቢያው አያስፈልግም "
"የሚወዱት ሁሉ ራሱ አብሮ ሲኖር ደስታ ይሰጣል ለሁልጊዜ ሲለይ ግን መታሰቢያው ያው የሚወዱት ሰው ራሱ ቢኖር ኖሮ የሚሰጠውን ነገር ግን ባለመኖሩ የቀረውን ደስታ ስለሚያስታውስ ለልብ ስቃይ ከመሆን በቀር ጥቅም የለውም"።
"የምትወደውን ለሁልጊዜ ሲለይህ የሚያስረሳህ እንጂ የሚያስታውስህ ነገር አትፈልግ ያለዚያ ህይወትህ የስቃይ ህይወት ይሆናል"
ያው እንግዲህ ጎህ ቀደደ ...ታሪክ ሆነ የሌት ጣሙ ፣
አሎሎ እንደሚገፋ ጉንዳን... ሊባዝን ነው አለሙ ፣
የማለዳው ሰማይ ቢያምር... ቢማርክም በቀለሙ ፣
ሲያዩት ደማቅ ቢመስልም ...የቀንበር ያክል ነው ሸክሙ ።
አትኩሮትህን በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ አድርገው። ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።
በህይወትህ ብዙ የሚያስከፉ ነገሮች አጋጥመውህ ሊሆን ይችላል ነገር ግን

ከምትወዳት ልጅ እንደ ወንድሜ ነው የማይህ የሚል ነገር እንደመስማት የሚያስከፋ ነገር የለም😔😔😢
በህይወት ውስጥ የሆነ ቀን…🍃

ቢኖረኝ ያልከው ይኖርሀል…ማሳካት የፈለከው ነገር ይሳካል…ዋናው ነገር ያን ነገር ምን ያህል ትፈልገዋለህ ነው…ለማገኝትስ ምን ያህል ትደክማለህ ነው…ከልብ የፈለግነው ነገር ይሳካል…
ይቅርታ ማለት የታላቅነት ምልክት ነው ስላሉኝ ይቅርታ አልኩሽ ግን እውነት ወድጀሽ አደለም ደሞም አልጠላሽም .....
ማውራት ፈልገህ ነገር ግን ማውራት እንደሌለብህ አውቀህ ዝምታን ከመረጥክ እመነኝ የመኖር ትርጉም ገብቶሀል።
አንዳንድ ልቦች ቅያሬ ሲያገኙ
ቆንጆ ነገሮችን ያስተባብላሉ
አንዳንድ ልቦች ደግሞ ያገኙት
ነገር የቱንም ያክል ቆንጆ ቢሆን
ለመጀመያው ሰው ሲሉ ቆንጆውን ይተውታል፡፡
HTML Embed Code:
2024/04/30 05:01:13
Back to Top